የደቡብ ሱዳን መንግስት ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ የተላከውን መሳሪያ አገደ

ጥቅምት (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ የደህንነቶች ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 4 መኪኖችን አስቁመዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱጃሪክ እንደገለጹት የደህንነት ሰራተኞች መሳሪያዎቹ ለአንድ ተቃዋሚ ሃይል ሊሰጥ ነው በሚል እንደያዙትና በሹፌሮቹ ላይ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ መኪኖቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል።