በነ ወርቅነህ አገኘሁ መዝገብ ብይን ለመስጠት የተያዘው  ቀጠሮ ተራዘመ

ጥቅምት (ሃያ አ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ በመሰረተባቸው አቶ ዘላለም ወርቅነህ፣  ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሽዋስ አሰፋና በሌሎች 5 ተካሳሾች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ አራዘመ።

ፍርድ ቤቱ የሁሉም ጠበቆች ተዘጋጅተው ባለመቅረባቸው ውሳኔውን ለህዳር 2 ፣ 2007 ማራዘሙን አስታውቋል። እስረኞቹ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለወራት በእስር እየተሰቃዩ ሲሆን፣ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች ክሱን ፖለቲካዊ ነው ይሉታል።

በሽብርተኝነት የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት እንደማይሰጠው የህግ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።