ሚያዝያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከሚገኙት ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መካከል ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድና ፍቅረማርያም አስማማው የረሃብ አድማ ጀምረዋል። የረሃብ አድማው መንስኤ ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው በቤተሰቦቿ የመጎብኘት ፈቃድ በመከልከሏ፣ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ለብቻዋ ታስራ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባት በመሆኑ፣ ድርጊቱን ለመቃወም ነው። ወጣት ብርሃኑና ፍቅረማርያም በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ...
Read More »Author Archives: Central
የጋምቤላ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ጥምረት ንቅናቄ የኢትዮጵያ መንግስት ለደቡብ ሱዳን አማጽያን የሚሰጠውን ድጋፍ ተቃወመ
ሚያዝያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥምረቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የሳልቫኪርን መንግስት ለሚቃወሙት ለደቡብ ሱዳን አማጽያን ድጋፍ እየሰጠ፣ በሌላ በኩል የሰላም ስምምነት አደራዳሪ ሆኖ መቅረቡ ትክክል አይደለም ብሎአል። የአዲስ አበባው መንግስት የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሃይሎችን ለመሸምገል ገለልተኛ አይደለም የሚለው መግለጫው፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለተቃዋሚዎች ወታደራዊ ስልጠና፣ የሎጅስቲክስና ወታደራዊ ድጋፍ እያደረገላቸው ነው ብሎአል። ድርጊቱ የአካባቢውን ሰላም የሚያናጋና አለመረጋጋትን የሚፈጥር ...
Read More »የስቅለት በዓል በመላው ዓለም በተለመደው ሃይማኖታዊ ስርዓት ተከብሮ ዋለ።
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ 2000 ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም -ቀራኒዮ ተራራ ላይ የተሰቀለበት እለት በመላው ዓለም በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ሲከበር ውሏል። ስቅለት፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የክርስቶስን ህማምና ስቃይ በሚያስታውስ መልኩ በተለየ ሀይማኖታዊ ሥር ዓት የሚከበር ታላቅ በዓል ሲሆን፤ እለቱን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን ...
Read More »ኢትዮጵያኖችን ከየመን ወደ አገራቸው ለመመለስ የበረራ ፈቃድ እየጠበቀ መሆኑን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእንግሊዝኛ IOM በመባል የሚታወቀው ድርጅት ባወጣው ዘገባ በሚቀጥሉት ቀናት ከየመን ሰንአ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ካርቱም ተከታታይ በረራዎችን ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ የበረራ ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ነው። አይ ኦ ኤም የበረራ ፈቃዱን የሚጠይቀው ከማን እንደሆን አላስታወቀም። ምን ያክል ኢትዮጵያውያን ለመመለስ ፈቃደኛ መሆናቸውንም አላስታወቀም። ይሁን እንጅ በየመን የሚገኙ ስደተኞች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል። ድርጅቱ ...
Read More »የጦር መሳሪያ ሽያጭ መጧጧፉ ተሰማ
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጧጡፎ በመሸጥ ላይ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። በአለፋ ፣ ጣቁሳ፣ መተማ፣ አርማጭሆ፣ ቋራና በሌሎችም በርካታ ወረዳዎች አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ45 ሺ እስከ 60 ሺ ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጦር መሳሪያዎችን በብዛት የሚገዙት አርሶ አደሮች ናቸው። በርካታ ቁጥር ያለው የኢህአዴግ ወታደር በጠረፍ ከተሞች ...
Read More »በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን ለማጥናት 2 ኩባንያዎች ተመረጡ
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በቅርቡ በአባይ ውሃ አጠቃቀምና በአባይ ግድብ ዙሪያ የስምምነት መርሆዎችን በተፈራረሙት መሰረት የግድቡን ውሃ አሞላል እንዲሁም ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ ስለሚያስከትለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖ ጥናት የሚያደርግ ገለልተኛ ኩባንያ ለመምረጥ በተስማሙት መሰረት የፈረንሳይ እና የሆላንድ ኩባንያዎች መመረጣቸው ታውቋል። የፈረንሳዩ ቢአር ኤል ኢንጂነሪንግ የውሃ አሞላሉን የግድቡን ኢንጂሪንግ ስራዎች ሲያጠና የሆላንዱ ዴልታ ራይስ ...
Read More »በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ወክባ እየተፈጸመ ነው ተባለ።
ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ እንደገለጸው፤ቀደም ካለ ጊዜ አንስቶ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እስረኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽም የቆየው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ሰሞኑን ደግሞ በከሰዓቱ የእስረኞች መጠየቂያ ክፍለ ጊዜ ጠያቂ እንዳይገባላቸው እገዳ ጥሏል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ይህን እገዳ የጣለው ከኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወላጅ እናት ማረፍ ጋር በተያያዘ በርካታ ህዝብ ሀዘኑን ለመግለጽና ለማፅናናት ወደ እስር ...
Read More »በአዲስአበባ የኤሌክትሪክና ውሃ መቆራረጥ ተባብሶ ቀጥሎአል
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና የመጠጥ ውሃ መጥፋት ባሳለፍነው ሁለት ሳምንታት ተባብሶ መቀጠሉ ህብረተሰቡን ለተለያዩ ወጪዎችና እንግልት እየዳረገ መሆኑንና በዚህ ጉዳይ መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ ማመን የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በተለይ ባለፈው ሳምንት እና በያዝነው ሳምንት የኤሌክትሪክ ኃይል ለረጀም ሰዓታት እንደሚጠፋ ተናግረዋል፡፡ በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጡ በአንድ ጊዜ ...
Read More »በዞን 9 ጸሃፊዎች ላይ ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም ተባለ
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ ዞን 9 በመባል በሚጠሩት ወጣት ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የመንግስት አቃቢ ህግ ጠንካራ ማስረጃ ለማቅረብ አለመቻሉን ጠበቃውን አቶ አምሃ መኮንንን በመጥቀስ ዘግቧል። በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 6 የዞን ዘጠኝ እና 3 ጋዜጠኞች ላለፉት 10 ወራት በእስር ላይ ከቆዩ በሁዋላ፣ ፍርድ ቤቱ በቅርቡ ምስክሮችን የመስማት ሂደቱን ጀምሯል። ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው ሂደት የቀረቡት ምስክሮች ጸሃፊዎችና ...
Read More »የዘይት ክፍፍል ስሌቱ በወር ለአንድ ሰው ሩብ ሌትር ነው ተባለ
ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችንን ሰሞኑን ለአማራ ክልል የሚሰጠውን የዘይት ክፍፍል መሰረት አድርጎ በላከው ዘገባ ለ20 ሚሊዮን ህዝብ በወር የተመደበው ዘይት 4 ሚሊዮን 800 ሺ ሊትር ነው። ለክልሎች የሚከፋፈለው ዘይት በህዝብ ቁጥር ልክ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አጠቃላይ ስሌቱ ለአንድ ሰው በወር ሩብ ሊትር ዘይት መሆኑን ጠቅሷል። የክፍፍሉ መጠን ዘይት ባለበት ጊዜ የተሰላ ሲሆን፣ የዘይት አቅርቦት በማይኖርበት ጊዜ ...
Read More »