Author Archives: Central

በአፋርና በኢሳ ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) በአፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ በአፋርና በኢሳ ሶማሊ ጎሳዎች መካከ ግጭት ተቀስቅሶ በግንሹ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ሰዎችም ለጉዳት መዳረጋቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሰኞ ገለጠ። በወረዳው አስጊታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት አንድ የአፋር ተወላጅ ወጣት በኢሳ ሶማሊ ጎሳ መገደሉ ተከትሎ እንደሆነ የድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ገሃስ መሃመድ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። ...

Read More »

በአፋር በድርቅ የተጎዱ ነዋሪዎች ድጋፍ ባለማግኘታቸው ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) በአፋር ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ባለማግኘታቸው ምክንያት ለከፋ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ታውቋል። በተለይ ለከፋ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ህጻናትና በእርግዝና ላይ ያሉ እናቶች በምግብ እጥረቱ ክፉኛ ጉዳይ እየደረሰባቸው መሆኑን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ገልጿል። በክልሉ በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች ውስጥ የሚጠበቀው የበልግ ዝናብ መዝነብ ካልጀመረም የሰውና የእንስሳት ሞት ሊከሰት እንደሚችል የድርጅቱ ሃላፊ አቶ ገሃስ መሃመድ ...

Read More »

የሶስት ኢትዮጵያውያን ንብረት ነው የተባለ 356 ሺ ዶላር በቻይና የጉአንግዙ መገኘቱን የቻይና መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) በቻይና የጉአንግዙ ግዛት በሚገኝ አንድ አለም-አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ የሶስት ኢትዮጵያውያን ንብረት ነው የተባለ 356 ሺ ጥሬ ዶላር መገኘቱን የቻይና መገናኛ ብዙሃን ሰኞ ዘገቡ። በአንድ ሻንጣ ተሞልቶ የነበረው ይኸው ከፍተኛ ገንዘብ በአየር መንገዱ መሳፈሪያ አካባቢ ለጉዞ በነበሩ ሁለት የኮንስትራክሽን ሰራተኞች መገኘቱንና የንብረቱ ባለቤት ናቸው ለተባሉት ሶስቱ ኢትዮጵያውያን መሰጠቱ ታውቋል። 356ሺ ጥሬ ዶላር ገንዘብን የያዘው አነስተኛ ሻንጣ ...

Read More »

የኦነግ የወጣቶች ክንፍ በማደራጀት ውጊያ ሊያካሄዱ ነበር የተባሉ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የወጣቶች ክንፍን በማደራጀት ከመንግስት ጋር ውጊያን ሊያካሄዱ ነበር የተባሉ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው ተዘገበ። ተጠርጣሪዎቹ በተለምዶ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት የእምነት ስነስርዓት የሚያካሄዱ በመምሰል ለወጣቶች ክንፍ አባላት ሲመለምሉና ሲያደራጁ መቆየታቸውን ከሳሽ አቃቤ ህግ በክሱ አቅርቧል ሲል ሪፖርተር ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ መንግስት ...

Read More »

ብሪታኒይ ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ድጋፍ ላይ ተቃውሞ መጀመሩን የዜና አውታሮች እየዘገቡ ነው

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) የብሪታንያ መንግስት ለኢትዮጵያ በሚሰጠው የደህንነትና የጸጥታ ድጋፍ ዙሪያ አዲስ ተቃውሞ መቅረብ መጀመሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ሃገሪቱ ዜጋዋን አስሮ ለሚገኝ ሃገር በአየመቱ ወደ አንድ ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ በመመደብ የጸጥታ ሃይሎች ልዩ ስልጠናን እንዲያገኙ ማድረጓ የብሪታኒያ የተለያዩ አካላት በመቃወም ላይ መሆናቸውን ዴይሊ ሜይል የተሰኘ ጋዜጣ በሳምንቱ መገባደጃ ባወጣው ሪፖርት አስነብቧል። የብሪታኒያ መንግስት አጋር አድርጎ ድጋፍ ከሚሰጣቸው ...

Read More »

የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) የአንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ሃያሲ፣ ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ የመታሰቢያ ፕሮግራም ባሳለፍነው ቅዳሜ ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ዓም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ዋለ። አዘጋጅ ኮሚቴው እንደገለጸው ከሆነ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት ዘመኑ ለሃገርና ለህዝብ ላበረከተው አስተዋፅዖ ለማመስገንና ህያው ስራዎቹ ለመዘከር በማሰብ የተዘጋጀ ፕሮግራም ሲሆን፣ ዝግጅቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ስኬታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁ ለኢሳት ገልጸዋል። የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ...

Read More »

በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የታሰበው የዕርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ መንግስት ትዕዛዝ ሰጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) ኢትዮጵያውያን የድርቅ ተጠቂዎችን ለመታደግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) ከሌሎች ለጋሾች ጋር ያስተባበረው የዕርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ መንግስት ትዕዛዝ ሰጠ። የኢሳት ምንጮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ለአዲስ አበባው የኦቻ (OCHA) ተጠሪ ማሰባሰቢያውን የሰጡት የጠ/ሚኒስትሩ ልዩ መልዕከተኛ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ናቸው። 10.2 ሚሊዮን በቀጥታ በድርቁ ተጠቂ በመሆናቸው ሌሎች 8 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ በሶፍትኔት ...

Read More »

ለህዳሴ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠሩ ስብሰባዎች በተቃውሞ ተበተኑ

ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2008) ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብና ለኮንዶሚኒየም በሚል በአሜሪካና በአውሮፓ ከተሞች የተንቀሳቀሰው የመንግስት ተወካዮች ተቃውሞ ቀረበባቸው። ስብሰባዎችም በተቃውሞ ተበተኑ። በአሜሪካ ፔንስልቬንያ ግዛት የፊላዴልፊያ ከተማ እንዲሁም በጣሊያን ቱርኒ በሳምንቱ መጨረሻ የተጠሩት ስብሰባዎች ያለውጤት በተቃውሞ መበተናቸውን ለኢሳት በቪድዮ የደረሰው ዜና ያስረዳል። በኢትዮጵያ የተከሰተውን ርሃብ እንዲሁም በኦሮሚያ የቀጠለውን ግድያና እስራት እያነሱ ተቃውሞ ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን፣ የአንድ ብሄር የበላይነት በሃገሪቱ አለ ሲሉም ...

Read More »

በቶሪኖ የተጠራው የመንግስት ስብሰባ በተቃውሞ ተበተነ

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ሚያዚያ 3፣ 2008 ዓም በጣሊያኑዋ የቶሪኖ ከተማ መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ለመጨጥ እንዲሁም አወዛጋቢ የሆነውን የኮንዶሚኒየም ሽያጭ ለማከናወን እና የውጭ ምንዛሬ ለመሰብሰብ የጠራው ስብሰባ በከተማዋ በሚገኙ ኢትጵያውያን ተቃውሞ እንዲሰረዝ ተደርጎአል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ገና ከመነሻው ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ መሰረታዊ የሚባሉ የመብት፣ የእኩልነትና የኢኮኖሚ አስተዳደር ጥያቄዎችን አንስተው ተቃውአቸውን አሰምተዋል፡፡ አንድ አራተኛው የኢትዮጵያ ...

Read More »

የወልቃይት ጠገዴና ፀለምት ተወላጆች በኒዉዚላንድ ኦክላንድ የጠሩት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኒዉዚላንድ ኦክላንድ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያዉያኖች አጋርነታቸዉንና ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም በሚለዉ የማንነት ጥያቄ ከወልቃይት ጠገዴና ፀለምት ሕዝብ ጋር መሆናቸዉንና ድጋፋቸዉን ለመስጠት ያላቸዉን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡ ስብሰባዉንም በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት አቶ አረፈዐይኔ መኮንን በአገር ዉስጥ የወልቃይት ጠገዴና ፀለምት የማንነት ሕዝብ ጥያቄ ሕገመንግስቱ በሚፈቅደዉ መሰረት የማንነታቸዉን ጥያቄ 50 ሺ የሚሆኑ አባወራ አስፈርመዉ ...

Read More »