ኢሳት (ሃምሌ 25 ፥ 2008) በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት ከስልጣን እንዲወገድ የሚጠይቅ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል ሲሉ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሰኞ ዘገቡ። ቢቢሲ እና ኣዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ሰልፉን ከዘገቡት ውስጥ ይጠቀሳሉ። ነዋሪነታቸው በከተማዋ እና አካባቢዋ የሆነ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የተለያዩ መፈክሮችን በማስተጋባት በሃገሪቱ ኢፍትሃዊነት መንገሱን በተቃውሞ ሲያሰሙ መዋላቸውን አፍሪካ ኒውስ የተሰኘ ...
Read More »Author Archives: Central
በጎንደርና እስቴ ከተሞች ከፍተኛ ህዝባዊ ትዕይንት ተካሄደ
ኢሳት (ሃምሌ 25 ፥ 2008) የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ በነሱ የኮሚቴ አባላት ላይ የተወሰደው እርምጃ በመቃወም እንዲሁም የወልቃይት ህዝብ የአማራነት ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ በመጠየቅ ዕሁድ ሃምሌ 24 ፥ 2008 በጎንደር የተካሄደው ህዝባዊ ትዕይንት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ። መሰል ተቃውሞ ሰልፍ በደቡብ ጎንደር እስቴ የተካሄደ ሲሆን፣ ህዝቡ ህዝባዊ ጥያቄዎችን ሲያሰማ ማርፈዱ ተመልክቷል። የወልቃይትን ህዝብ የማንነት ጥያቄ ከማስተጋባት ባሻገር በኢትዮጵያ በተለያየ መንገድ በደል ...
Read More »ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ በዳለስ ዓለም አቀፍ አውሮፓላን ማረፊያ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው
ኢሳት (ሃምሌ 25 ፥ 2008) ይህ በእንዲህ እንዳለም የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ያነሱ የኮሚቴ አባላትን በማሳደድና በማሰር ላይ የሚገኘው የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ በዋሽንግተን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው። ዕሁድ ሃምሌ 24 ፥ 2008 ዋሽንግተን ዳለስ ዓለም አቀፍ አውሮፓላን ማረፊያ ሲደርሱ እንግዳ መቆየ ስፍራ ላይ ተቃውሞ የጠበቃቸውን ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ በሁኔታው ሲደናገጡ ታይተዋል። በዕለቱ ዋሽንግተን እንደሚገቡ መረጃ የደረሰው ...
Read More »የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ለሶስት ኢትዮጵያውያን የክብር ዕውቅና ሰጠ
ኢሳት (ሃምሌ 25 ፥ 2008) ስድስተኛውን አመታዊ ፌስቲባል በዋሽንግተን ዲሲ ጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ ያካሄደው “የኢትዮጵያውያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ” እውቅናውን የሰጠው በአርአያነት ተምሳሌት ለሆኑ እና ከራስ በላይ ለህዝብ መስዋዕት የሆኑትን በመምረጥ እንደሆነ አዘጋጁ ኮሚቴው አሳውቋል። በተምሳሌታዊ አርዓያነት የክብር ዕውቅና የተሰጣቸው ዶ/ር ብሩክ ተድላ ከልጅነት እስከ እውቀት ለትምህርታቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የላቀ ውጤት በማስመዝገባቸው የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል። ዶክትሬታቸውን በፊዚክስ እና ...
Read More »ራሳቸውን ባቃጠሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ድርጊት ማዘኑን የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 25 ፥ 2008) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የካይሮ ቢሮ ሰሞኑን ራሳቸውን ባቃጠሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ድርጊት ማዘኑን ገለጸ። በተባበሩት መንግስታት የስደኞች ኮሚሽን የካይሮ ቢሮ የህዝብ መረጃና ኮሚውኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት ታሪክ ኣርጋዝ፣ በሁለቱ ኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጠረው ሁኔታ እጅግ አዝነናል ሲሉ ዴይሊ ኒውስ ኢጂይፕት ለተባለ ጋዜጣ ገልጸዋል። ሰዎቹ ራሳቸውን በእሳት ባቃጠሉበት ጊዜ ሶስት ሰዎች ተጎድተው እንደነበርና አንድ ሴት ሌላው ሰው ...
Read More »በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ ተቃውሞች እየተካሄዱ ነው
የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የድምጻችን ይሰማ ተከትሎ የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ኦሮምያ ተሸጋግሮ የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ፣ ተቃውሞው ወደ ሰሜን በማምራት በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ተካሂዷል። በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ላይ የተጀመረው ተቃውሞ አገራዊ ቅርጽ እየያዘ መምጣቱንና በመሃል አዲስ አበባም በቅርቡ ህዝባዊ ተቃውሞች ሊደረጉ ይችላሉ የሚል ግምገማ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ማድረጉን መኖሩን ምንጮች ገልጸዋል። ትናንት በጎንደር ከተማ በ100 ሺዎች የሚቆጠር ...
Read More »በአወዳይ በርካታ ዜጎች ተገደሉ
የጎንደር ህዝብ ህዝባዊ ተቃውሞ በሚያደርግበት እለት ተመሳሳይ ተቃውሞ ያደረጉት የአወዳይ ከተማ ነዋሪዎች በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች ተጨፍጭፈዋል። እስካሁን ባለው መረጃ 6 ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ሲግለጽ፣ አንዳንድ ነዋሪዎች ግን የሟቾቹ ቁጥር በርካታ ነው ይላሉ። ከ20 በላይ ሰዎችም ቆስለዋል። ከትናንት ጀምሮ መንገዶች ተዘጋግተው የዋሉ ሲሆን፣ ዛሬ አወዳይ ሙሉ በሙሉ ጭር ብላ መዋሉዋንና ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በወታደሮች ቁጥጥር ስር መግባቷን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ...
Read More »በደቡብ ጎንደር የጦር መሳሪያ መጋዝን ተሰብሮ ተዘረፈ
በ ምስራቅ በለሳ ወረዳ አምቦ በር ( እብናት) አካባቢ የጎንደር ከተማ ሰልፍ ከመካሄዱ ከሰአታት በፊት የፖሊስ ጣቢያ መጋዝን ተሰብሮ ከ12 በላይ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ፣ የፖሊስ ልብሶችና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ተዘርፈዋል። ይህን ተከትሎ የከተማው የፖሊስ አዛዥ ትናንት አሰሳ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪ የተቃውሞ ሰልፍ ሲወጣ ታግዷል። ጥቃቱን የፈጸሙት ሃይሎች እነማን እንደሆኑ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ በዚህ አካባቢ ከወር በፊት ...
Read More »የቀድሞ የኤሳዋን ሃላፊዎች በድርጊታቸው ተጸጽተው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንና (ESFNA) የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ
(ሃምሌ 22 ፥2008) ከኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) ተለይተው የራሳቸውን ድርጅት ካቋቋሙት የቀድሞውን ፕሬዚደንት ጨምሮ ሁለቱ በድርጊታቸው ተጸጽተው ፌዴሬሽኑን እንዲሁም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ። ኤሳዋን የተባለውና በእነርሱ ጎራ ያቋቋሙት ድርጅት ውስጥ የተፈጠረውን የገንዘብ ብክነት በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ትክክል እንደነበርም አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴለቪዥን አገልግሎት ስለ “ኤሳዋን” የደረሰውን የውስጥ መረጃ ለህዝብ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተጨማሪ ማስረጃዎች አሉን በማለት ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ላደረሱት ጥፋት ምርመራ ለማካሄድ ፈቃደኛ አይደለም ተባለ
(ሃምሌ 22 ፥2008) የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ የደረሰውን የሰው ሞትና የንብረት ጉዳት አስመልክቶ ግልጽነት የተሞላበት ምርመራ ለማካሄድ ፈቃደኛ አይደለም ወይም በጸጥታ ሃይሎቹ ባህርይ ላይ ምርመራ ለማካሄድ አልቻለም ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ወቀሰ። ጉዳዩ አለም አቀፍ ጣልቃገብነት እንደሚያስፈልገውም ጠይቋል። በኦሮሚያ ክልል ከ400 ዜጎች መገደል በሁዋላ እንኳን በመንግስት የተወሰዱ ምንም አይነት ምርመራዎች አለመደረጋቸውን የገለጸው ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ሰላማዊ ...
Read More »