(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011) የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተቃውሞ ቀሰቀሰ። ትላንት በክብር ተሸኝተዋል የተባሉት የቀድሞ የፓርቲው አመራሮች በፈጠሩት ጫና የለውጥ ሃይል በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እንዳይገባ ከጥቆማ አንስቶ ጫና በመፍጠር ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በማዕከላዊ ኮሚቴው ምርጫ አብዛኞቹ የአቶ ስዩም አወል አመራር ደጋፊዎች በዕጩነት መቅረባቸው ታውቋል። የአፋር ወጣቶች ከወዲሁ የማዕከላዊ ኮሚቴውን ምርጫ በመቃወም ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ...
Read More »Author Archives: Central
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ጅቡቲን ሊጎበኙ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 27/2011) የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጅቡቲን ሊጎበኙ ነው። የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትላንት እንዳታስታወቁት የኤርትራው መሪ በቅርቡ ጅቡቲን የሚጎበኙ ሲሆን የጅቡቲውም ፕሬዝዳንት በተመሳሳይ ኤርትራን እንዲጎበኙ መርሃ ግብር መዘጋጀቱም ተመልክቷል። ላለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ከድንበር ጋር በተያያዘ ሲወዛገቡ የነበሩትና መጠነኛ ወታደራዊ ግጭትም ያደረጉት ኤርትራና ጅቡቲ ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ግኑኝነታቸው እየተሻሻለ መቷል። የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስተር ...
Read More »በሲዳማ ዞን መምህራን አድማ መቱ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011) በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች መምህራን አድማ መቱ። መምህራኑ አድማውን የመቱት ለህዳሴው ግድብ የሚቆረጠው ደሞዛቸው እንዲቆም በመጠየቅ ነው። እስካሁንም ሲቆረጥ የነበረው እንዲመለስላቸው መምህራኑ አድማ በመምታት ጠይቀዋል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ እስኪሰጣቸውም ወደ ስራ ገበታቸው እንደማይመለሱ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ መምህራን ለህዳሴው ግድብ ከደሞዛቸው የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲቆም በመጠየቅ ከአንድ ሳምንት በላይ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ቱኒዚያን ...
Read More »በአማራ ክልል ሶስት ቀበሌዎች ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥባቸው ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011) በአማራ ክልል ሶስት ቀበሌዎች ላለፉት አራት ዓመታት ከመንግስት መዋቅር ውጪ እንዲሆኑ ተደርገው ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥባቸው እንደነበር የክልሉ የጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ገለጹ። ሃላፊው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ለአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ድርጅት በሰጡት መግለጫ የቅማንትን ጥያቄ አስታከው የተነሱ ሃይሎች ሶስቱን ቀበሌዎች ወታደራዊ ማሰልጠኛ አድርገው በክልሉ ሰሜን ክፍል በርካታ የሰው ህይወት የጠፋባቸውና ንብረት የወደመባቸውን ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል። ...
Read More »ከእስር የተፈቱት አብራሪዎች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011)ከስራ ገበታቸው ተይዘው በግፍ የታሰሩትና በለውጡ ሳቢያ የተፈቱት አብራሪዎች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ማህበር ጠየቀ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ “አዲሱ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዕጣ ፈንታ ያገባናል” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ለውጡን እንደሚደግፍና የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ለማጠናከር በሚሰሩ ስራዎች ሁሉ ለመተባበር ዝግጁ መሆኑንም አመልክቷል። ሆኖም በግፍ ተይዘው በስቃይ ላይ የቆዩት የበረባ ባለሙያዎች እስከአሁን ወደ ...
Read More »ሕወሃት የለውጡ አደናቃፊ ሳይሆን የለውጡ መሪ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011) ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ የለውጡ አደናቃፊ ሳይሆን የለውጡ መሪ ነው ሲሉ የፓርላማው የመንግስት ተጠሪ ገለጹ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ የሆኑትና የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ከትግራይ ክልል ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለውጡ በትክክል እየተተገበረ ያለውም በትግራይ ክልል ነው ብለዋል። ለውጡ ማለት ሰላም ነው፣ ለውጥ ማለት የሕግ የበላይነት ነው ...
Read More »የተከሰተው መፈናቀል ከየትኛውም የአለም ሀገራት የበለጠ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011) በኢትዮጵያ ባለፉት 11 ወራት ውስጥ የተከሰተው መፈናቀል ከየትኛውም የአለም ሀገር የበለጠ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በግጭት እንዲሁም በድርቅና ጎርፍ ሳቢያ በምዕራባውያኑ 2018 የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ መሆኑም ተመልክቷል። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት /ኦቻ/ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሰረት በአጠቃላይ የተፈናቃይ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ...
Read More »የቀድሞ የአሶሳ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ 5 ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011)በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ የቀድሞ የአሶሳ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ 5 ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የፌደራል ፖሊስ ግብረሃይል በአካባቢው ባካሄደው ዘመቻ በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለልጣናት ሰኔ 17/2010 በአሶሳ በተከሰተው ግጭት እንዲሁም በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ወሰን ላይ በነበረው ግጭት የችግሩ ጠንሳሾች በመሆናቸው ነው ተብሏል። በመንግስታዊዎቹ መገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 5 ባለስልጣናት ውስጥ ከቀድሞው የአሶሳ ...
Read More »በሶማሌ ክልል ለመፍጠር ታስቦ የነበረው የሽብር ጥቃት ከሸፈ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011) የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በክልሉ ሽብር ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ። በዚህ የሽብር ጥቃት ሙከራ ኢላማ የተደረጉት የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ፣ መብራት ሃይል፣ ኢምግሬሽን፣ ባንኮችና ህዝብ የሚበዛባቸው አካባቢዎች እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል። የክልሉ የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ አብዲ አቢ ለኢሳት እንደገለጹት የተሸረበው የሽብር ጥቃት በቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት በአቶ አብዲ ኢሌ በተሰጠ ትዕዛዝ በአጎታቸው አማካኝነት የሚፈጸም እንደነበር እና አጎታቸው እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ...
Read More »በጭልጋ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 25/2011) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። ከቅማንት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሳው በዚሁ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 8 ሰዎች መቁሰላቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ገልጸዋል። በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም ዝርፊያ መፈጸሙንም አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። ጥቃቱን በቅማንት ስም በስውር የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች የፈጸሙት እንደሆነ ተመልክቷል። በተያያዘ ዜና በማዕከላዊ የጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ...
Read More »