ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የጸረሙስና አውደጥናት ላይ እንደተገለጸው የአማራ ክልል ጸረሙስና ኮሚሽን ስራውን በአግባቡ ከመስራት ይልቅ በርካታ ሙሰኞችን ስራ በመደባበቅ ላይ መሆኑን ተሳታፊዎች አጋልጠዋል፡፡ “ለልማት፣ ለሰላምና ለደህንነት በሙስና ላይ የተባበረ ክንድን ማንሳት!!” በሚል መሪ ቃል ለ12ኛ ጊዜ በሚከበረው የጸረሙስና ቀን ጥናት አቅራቢው እንደተናገሩት በአማራ ክልል ከሚገኙ መንግስታዊ መስሪያቤቶች ውስጥ በፌደራል ደረጃ ...
Read More »Author Archives: Central
የሃዋሳ ፔፕሲ ኮላ እና የድሬደዋ ኮካ ኮላ ፋብሪካዎች እንዲዘጉ ተደረገ
ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃዋሳው ፔፕሲ ኮላ እና የድሬደዋ ኮካ ኮላ ፋብሪካዎች ተዘግተው ለሽያጭ የተስራጩት ምርቶቻቸው እንዲሰበሰቡ ሲል ንግድ ሚንስቴር የእገዳ ትእዛዝ መመሪያ አውጥቷል። የሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ንብረት የሆነው የሃዋሳ ፔፕሲ ፋብሪካ እና የምስራቅ አፍሪካ ቦትሊንግ ንብረት የሆነው የድሬዳዋው ኮካ ኮላ ምርቶቻቸው የጥራት ደረጃቸውን ሳይጠብቁ ለተጠቃሚው ለገበያ መቅረባቸውን ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። የሃዋሳ ሚሊኒየም ፔፕሲ ፋብሪካ ...
Read More »ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የዕዳ ክምችት ካለባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ናት ተባለ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በአፍሪካ አስደንጋጭ ነው የተባለው የውጭ ዕዳ ክምችት ካለባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ሆና ተፈረጀች። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2015 አም የሃገሪቱ የዕዳ ክምችት ይፋ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ መጽሄት የሃገሪቱ የዕዳ ክምችት 22 ቢሊዮን አካባቢ እንደነበር በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት አስፍሯል። ይሁንና በተያዘው የፈረንጆች 2016 አም ይኸው የዕዳ ክምችት ወደ 36 ቢሊዮን ዶላር ኣካባቢ መድረሱ ሲገለጽ ...
Read More »የአትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ፍትሃተ ጸሎት በካናዳ ቤተክርስቲያን ተካሄደ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ጀግና አትሌት ሻንበል ምሩፅ ይፍጠር ፍትሃተ ጸሎት በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ተከናወነ። በዚህ ሳምንት አስከሬን ወደ ትውልደ ሃገሩ ኢትዮጵያ እንደሚሄድም ለማወቅ ተችሏል። ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ታህሳስ 13, 2009 ምሽት ካናዳ ቶሮንቶ ህይወቱ ያለፈው ታላቅ አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር በርካታ ኢትዮጵያውያን በታደሙበት እጅግ ደማቅና ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ማክሰኞ ታህሳስ 18 2009 ጸሎተ ፍትሃቱ የተካሄደ ሲሆን፣ ...
Read More »የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላት ላይ በአዲስ አበባ የተመሰረተው ክስ ለሁለተኛ ጊዜ ታየ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) በኮ/ል ደመቀ ዘውዱና በሌሎች የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላት ላይ በአዲስ አበባ የተመሰረተው ክስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ማክሰኞች እለት የታየ ቢሆንም፣ ኮ/ል ደመቀ አሁንም በጎንደር ወህኒ ቤት ይገኛሉ። አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አቶ አለነ ሻማ፣ አቶ ጌታቸው አደመ፣ እንዲሁም ነጋ ባንቲሁን፣ ማክሰኞ ታህሳስ 18, 2009 ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ተለዋጭ ቀጠሮ ለጥር 4 ፥ 2009 ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ እንዲደረግ ለትውልደ-ኢትዮጵያውያኑ ጥሪ ቀረበ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፥ 2009) በውጭ ሃገር ያሉ የኢትዮጵያ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ለ3 ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሃገር የመላክ ማዕቀብ ጥሪን አስተላለፉ። 17 የሚሆኑት የሲቪልና የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያውያን ለንግድም ይሁን ለቤተሰብ ድግማ የሚልኩት የውጭ ምንዛሪ እንዳይላክ ማድረግ በሃገሪቱ ያለውን አምባገነን አገዛዝ ለማድከም ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ መግለጫው አመልክተዋል። ድርጅቶቹ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪው መላካቸውን ለ3 ወራት ካቆሙ ...
Read More »በአፋር የሎጊያ ከተማ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ማክሰኞ በአፋር ክልል በሌጊያ ከተማ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከመማር ማስተማር ሂደት ችግና ከመልካም አስተዳዳር እጦትና ጋር በተያያዘ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ሰልፉን ተከትሎ ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽመዋል። ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ። አካባቢው በወታደሮችና በልዩ ሃይል አባላት እየተጠበቀ መሆኑን የደረሰን መረጃ ...
Read More »ኢህአዴግ “ገምግሞ ከስልጣን ያወረዳቸውን ባለስልጣናት” ወደ ትምህርት ሊልክ ነው
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በጥልቅ ትሃድሶ ስም በሙስና የተዘፈቁ ያላቸውን 479 የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች የወረዳ እና የቀበሌ ባለስልጣናት ወደ ትምህርት ሊላከቸው መሆኑን ምንጮች ገለጹ። “ኢህአዴግ ህዝብን ያስቸገሩ እና ያመረሩ ፣ የመልካም አሰተዳደር ችግር ያለባቸው እና ስርአቱን አደጋ ውስጥ የጣሉ ናቸው” በሚል ከአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች የተለዩትን ባለስልጣናት ማባረሩ “አመራሮቹ ወደ ተቃዋሚዎች ገብተው ለስርዓቱ ...
Read More »በለገዳዴና ለገጣፎ አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታሰሩ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ትናንት ሰኞ ከምሽት ጀምሮ ወታደሮች በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ለገጣፎ፣ ለገዳዲ እና ሌሎችም አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በእሬቻ በአል ወቅት ወረቀት ሲበትኑ የነበሩትን አጋልጡ እየተባሉ የአካባቢው ሰዎች ስቃይ ሲደርስባቸው ቆይቷል። በእስር ላይ የነበሩ 10 ሺ ወጣቶች መለቀቃቸው እንደተነገረ የተጀመረው የእስር ዘመቻ፣ ትናንት ምሽት ተጠናክሮ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ በጽኑ ታሞ ባቱ ሆስፒታል ገባ
ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታህሳስ18 ቀን 2009 ዓ.ም በፀና ታሞ በአንፑላንስ ተጭኖ ዝዋይ በሚገኘው ባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል። በተደጋጋሚ ጊዜያት ከቤተሰቦቹ እና ሕጋዊ ጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ሲደረግ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት በሚገቡበት ወቅት በአቅራቢያው የሚገኙትን ...
Read More »