(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2011)በሞያሌ ከተማ ከትላንት ጀምሮ የሰዓት እላፊ መደንገጉ ተገለጸ። የሞያሌ ከተማ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጥያቄ መሰረት የተፈጸመ መሆኑንም አስታውቋል። ላለፉት ሁለት ሳምንታት እንደአዲስ ባገረሸው ግጭት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ማንኛውንም ዓይነት እንቅስቃሴን ይከለክላል። በሞያሌና በዙሪያዋ ...
Read More »Author Archives: Central
ኦብነግ በምርጫ እሳተፋለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2011) ከመንግስት ጋር በመደራደር የትጥቅ ትግል በማቆም ወደ ሃገር ቤት የገባው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ / በምርጫ በመሳተፍ ሰላማዊ ትግሉን በይፋ እንደሚቀላቀል አስታወቀ። ሆኖም ሃገሪቱ ላይ ሰላምና መረጋጋት ሳይፈጠር ምርጫ መካሄዱን እንደማይደግፈው የግንባሩ ቃለአቀባይ ገልጸዋል። የኦብነግ የውጭ ጉዳይ ሃላፊና ቃል አቀባይ አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከመንግስት ጎን ሆኖ ለመስራት ኦብነግ በሙሉ ሃይሉ ...
Read More »በሱዳን የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ማህበራት ተቃውሞውን መደገፋቸው ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2011) በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ኦማር አልበሽር ላይ የተጀመረውንና ሁለት ሳምንት ያስቆጠረውን ተቃውሞ 22 ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ማህበራት መደገፋቸው ታወቀ። 22ቱ የሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፕሬዝዳንት አልበሽር ስልጣን እንዲለቁና የሽግግር መንግስት በአስቸኳይ እንዲመሰረትም ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዝዳንት አልበሽር በበኩላቸው በችግሩ ዙሪያ መርማሪ ኮሚቴ አዋቅረዋል። ራሳቸውን የለውጥ ብሔራዊ ህብረት በማለት የሰየሙት 22 ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ማህበራት ትላንት ማክሰኞ በይፋ ባደረጉት ጥሪ ፕሬዝዳንት አልበሽር ስልጣናቸውን ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በመኪና ውስጥ ታፍነው መሞታቸው ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2011)ከታንዛኒያ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ የነበሩ 14 ኢትዮጵያውያን በመኪና ውስጥ ታፍነው መሞታቸው ተሰማ። በምስራቃዊ ታንዛኒያ ግዛት ሚንሱ በተባለ ቦታ በመኪና ውስጥ ሞተው ከተገኙት 14ቱ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ሌሎች 12 ኢትዮጵያውያንም በሕይወት የተገኙ ሲሆን ለህክምና ሆስፒታል መላካቸው ተመልክቷል። በምስራቅ ታንዛኒያ ግዛት የሞሮጎሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዊልብሮድ ሙታፍንግዎ ለታንዛኒያው IPP ሚዲያ በሰጡት መግለጫ በህይወት ከተረፉት 12ቱ ኢትዮጵያውያን 5ቱ ወዲያውኑ ህክምና ...
Read More »የትግራይ ክልል የክልሉ ተወላጅ ላልሆኑ ተጠርጣሪዎች ከለላ ይሰጣል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2011) የትግራይ ክልላዊ መንግስት የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑ ተጠርጣሪዎችን ከለላ በመስጠት በሕግ ቁጥጥር ሥር እንዳይውሉ እያደረገ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሐኑ ጸጋዬ አስታወቁ። የቀድሞውን የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ስንጠይቅም የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል። እናም አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ስንል ጥይት ተታኩሰን የሌላ ሰው ሕይወት እንዲያልፍ አንፈልግም ብለዋል። የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ...
Read More »በተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2011) በቡራዩ ከተማ ከተከሰተው ግጭትና ግድያ ጋር በተያያዘ በ109 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለጸ። በሃዋሳ ከተማ ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘም በወቅቱ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባና የፖሊስ አባላትም ተሳታፊ እንደነበሩም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫ መረዳት ተችሏል። የጠቅላይ አቃቤ ህግ የስራ ሃላፊዎች ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በቡራዩ ከተማ ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘ 649 ሰዎች ተይዘው ...
Read More »በተለያዩ አካባቢዎች የዜጎች ግድያና መፈናቀል ቀጥሏል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2011) በደቡብ ኢትዮጵያ በካፋ ዞን ብሔርን መነሻ ባደረገ ግጭት ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ፍንጭ ውሃ ከተማ ላይ ተመሳሳይ ብሄር ተኮር ጥቃት ተሰንዝሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል ከሁለት ዓመት በላይ ሰላም በማጣት ቆይተናል የሚሉት የአማሮ ኬሌ ወረዳ ነዋሪዎች በኦነግ ታጣቂዎች የሚደርስባቸው ጥቃት በመቀጠሉ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ...
Read More »ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ 1300 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2011) በምዕራባውያኑ 2018 ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ 1300 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የ2018 መጨረሻን ምክንያት በማድረግ ባወጣው ሪፖርት ወደ ጣሊያንና ማልታ ለመሻገር የሞከሩ 1ሺህ 300 ስደተኞች ህይወታቸው አልፏል። አለም አቀፉን የስደተኞች ድርጅት IOMን በመጥቀስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ብዙዎቹ ሟቾች የቱኒዚያ፣ ኤርትራ፣ ኢራቅ፣ ሱዳን፣ ፓኪስታን እና ...
Read More »በአንድ የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ ቤት 500 የሚሆኑ ሽጉጦች ተገኙ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2011)በባህርዳር ከተማ በአንድ የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ ቤት ውስጥ 500 የሚሆኑ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የአማራ ክልል ምክር ቤት ልዩ የጥበቃ ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር ውበቱ ሽፈራው ከመኖሪያ ቤታቸው 498 ሽጉጦች መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል። ታህሳስ 22/2011 ሰኞ ምሽት በመኖሪያ ቤታቸው 498 ሽጉጦችን ደብቀው የተገኙት የፖሊስ ሃላፊ የጦር መሳሪያውን ለምን እንዳከማቹና ከየት እንደሰበሰቡት የተገለጸ ነገር የለም። ፖሊስን ጠቅሶ የአማራ ...
Read More »በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መደበቅ ችግር እየፈጠረ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2011)በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መደበቅና እንዳይያዙ ከለላ መስጠት በአሰራሩ ላይ ችግር እየፈጠረበት መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ገለጸ። ወንጀሎችን ከተደበቁበት ለማውጣትና ለህግ ለማቅረብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድጋፍ እንዲሰጥ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ጠይቀዋል። የተወካዮች ምክርቤት የጠቅላይ አቃቤህግ የ5 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ...
Read More »