(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2011) የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ከመንፈቅ በፊት ተግባራዊ ያደረገው የምህረት አዋጅ ትናንት ማብቃቱ ተገለጸ። ከ13 ሺ በላይ ሰዎች በዚህ የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተመልክቷል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ከሀምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው በዚህ የምህረት አዋጅ በወህኒ የሚገኙ 250 እስረኞች ሲፈቱ በሌሉበት የተፈረደባቸው 430 ዜጎችም የምህረት ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ሃላፊዎች ለመንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። 2 ሺ ...
Read More »Author Archives: Central
አሜሪካ በሶማሊያ አልሻባብ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መቀጠሏ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 13/2011)የአሜሪካ መንግስት በሶማሊያ በአልሻባብ ይዞታዎች ላይ የሚያደርሰውን የአየር ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። በሳምንቱ መጨረሻ በአልሻባብ ላይ በተሰነዘረ የአየር ጥቃት 52 ታጣቂዎች ተገድለዋል። አሜሪካ ባሳለፍነው የምዕራባውያኑ ዓመት 2018 ብቻ 47 የአየር ጥቃት ማድረሷም ተመልክቷል። አልሻባብ ባለፈው ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ በዘመናዊ ሆቴል ላይ እንዲሁም በመቋደሾ በወታደሮች ካምፕ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት በአጠቃላይ 30 ያህል ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። ይህ የሶማሊያ ጽንፈኛ ሃይል ...
Read More »የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአልሻባብ ላይ ጥቃት ሰነዘረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 13/2011)የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአልሻባብ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን መንግስት አስታወቀ። አልሻባብ 50 የኢትዮጵያን መንግስት ወታደሮች ገደልኩ ባለ ማግስት የወጣው የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ 66 የአልሻባብ ወታደሮች መገደላቸውን ያትታል። ከሶማሊያ መንግስት ጦር ጋር በጥምረት ተካሄደ በተባለው በዚሁ ጥቃት ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በኩል የደረሰው ጉዳት አልተገለጸም። አልሸባብ ገደልኳቸው ስላላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮችንም በተመለከተ ምላሽ አልሰጠም። አሜሪካንም በአልሸባብ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች። ባለፈው ...
Read More »የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ተቃውሞ ማስነሳቱ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 13/2011)ባለፈው ሳምንት የጸደቀው የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ የጋምቤላ ነዋሪዎችን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው በሚል ተቃውሞ ተነሳ። የአኝዋክ ተወላጆች የመኖር ህልውናችንን አደጋ ላይ የሚጥል አዋጅ ነው ሲሉ በምሬት በመቃወም ላይ ናቸው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ በአኝዋኮች ህልውና ላይ የተነጣጠረ አደጋ ነው ሲሉ ዶክተር አጆት ሚሩ የሰላምና የሰብዓዊ መብት ተመራማሪ ለኢሳት ገልጸዋል። በአዋጁ መሰረት ከጋምቤላ ነዋሪዎች ቁጥር የሚበልጡት ...
Read More »በሶማሌ ክልል ለውጥ ቀልባሾች እያንሰራሩ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 13/2011)በሶማሌ ክልል ለውጥ ቀልባሾች እያንሰራሩ መሆናቸው ተገለጸ። ከቱርክ ኢስታንቡል ጂጂጋ ድረስ የተዘረጋው የቀድሞ ካቢኔ አባላት ኔትወርክ አዲሱን አመራር ለመጣል እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ሰሞኑን ጅጅጋ ላይ ቦምብ ለማፈንዳት የታቀደውን የክልሉ የጸጥታ ሃይል ማክሸፉም ታውቋል። ከሀገር የኮበለሉት የቀድሞ ካቢኔ አባላት ክልሉን ለማተራመስ ከፍተኛ ገንዘብ መድበው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል። የፌደራል መንግስቱ በሶማሌ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ...
Read More »በሱዳን ካርቱም አንድ ዶክተርንና አንድ ሕጻንን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችም ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) በሱዳን ካርቱም በቀጠለው ተቃውሞ ትላንት አንድ የህክምና ዶክተርንና አንድ ሕጻንን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችም መገደላቸው ተሰማ። ፕሬዝዳንቱ ጄኔራል ኦማር አልበሽር ላይ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተሰማው። ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ በተገደሉት ሰዎች የቀብር ስነስርአት ላይ በተገኙ ሰዎች ላይ ተኩስ መከፈቱም ታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከታህሳስ 19 ጀምሮ በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል አልበሽር ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣የሕክምና ...
Read More »በምዕራብ ጉጂ 33 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀመሩ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011)በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ወደ ስራ መመለሳቸው ተነገረ። በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑንም የምዕራብ ጉጂ ዋና አስተዳዳሪ መግለጻቸው ተዘግቧል። ይሕ በእንዲህ እንዳለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በንፁሃን ዜጎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ስጋቶችንም ያዘለ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011)በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ተስፋን ይዞ የመምጣቱን ያህል በተቃራኒው ስጋቶችንም ያዘለ እንደሆነ በአፅንኦት መገምገሙን የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ኢሕአዴግ በመግለጫው እንዳለው ለዉጡ አሁንም ህዝባዊ መሰረት ይዞ በኢህአዴግ እየተመራ ያለ ቢሆንም በፀረ ለውጥ አስተሳሰብ አራማጆች በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ ተግዳሮት እየፈጠሩ ናቸው። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ላለፉት 3 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በድርጅቱ ውስጥም ሆነ በለዉጡ ...
Read More »ኦነግ የአየር ድብደባ ተፈጽሞብኛል አለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) በምዕራብ ኦሮሚያ ምንም አይነት የአየር ድብደባ አለተፈጸመም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ያወጣውን መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አስተባበለ። በቄለም ወለጋ ዞን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲል ኦነግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በትናንትናው ዕለት በቃል-አቀባዩ ብልለኒ ስዩም በኩል በምዕራብ ኦሮሚያ ጦሩ ያካሄደዉን የአየር ድብደባ የለም በሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር። ይህም ሆኖ ግን የኦሮሞ ...
Read More »መንግስት ወደ ማይፈለገው ወታደራዊ ርምጃ እየተገፋፉ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) በሕዝብ መካከል ተሰግስገው ግጭቶችና ትንኮሳዎች በየአካባቢው ለማቀጣጠል ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ አንዳንድ አካላት መንግስት ወደ ማይፈለገው ወታደራዊ ርምጃ እየገፋፉት ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስቲሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ትላንት የት ነበርን ዛሬስ ወዴት እየሄድን ነው በሚል ርዕስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ባስተላለፈው መልዕክት እዚህም እዚያም ከለውጡ ጋር አብረው የማይሄዱ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው ብሏል። እነዚህ ጊዜያዊ ችግሮች ግን የለውጡን ሂደት ...
Read More »