(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪና መምህር የነበሩት የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት ተፈጸመ። በስደትና በእስር ለበርካታ ዓመታት በኤርትራ ቆይተው ከወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የቀብር ስነስርዓት በምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ መፈጸሙን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአማራ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ...
Read More »Author Archives: Central
የኤርትራ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊሄድ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)የኢትዮጵያና የኤርትራን ወዳጅነት ለማጠናከር ያለመ የኤርትራ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያ እንደሚገባ ኤርትራ አስታወቀች። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንደገለጸው ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዘው የልኡካን ቡድን ታዋቂ የኤርትራ ሙዚቀኞችን ቡድን አካቷል። ይሄ የሙዚቀኞች ቡድን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያቀርብም ተመልክቷል። ታዋቂ የኤርትራ የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው የተባለው የኤርትራ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ዝግጅቱን በባህርዳር እንደሚጀምርም ...
Read More »ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሐገር ገንዘብ በኢትዮጵያ ድንበር ተያዘ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)በሕገወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጣ የነበረ 7 ኪሎግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሐገር ገንዘብ ትላንት በኢትዮጵያ ድንበር ላይ መያዙ ተገለጸ። በሕገወጥ መንገድ ከሐገር ሊወጣ ሲል በቶጎ ውጫሌ ኬላ ላይ ከተያዘው 7ኪሎ ግራም ወርቅ በተጨማሪ 1 ሚሊየን 527ሺ 14 የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም 8ሺ 280 ዩሮና 31ሺ 900 ፓውንድ መያዙም ተመልክቷል፡ የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በተጨማሪም 25ሺ 665 የካናዳ እንዲሁም 8 ...
Read More »የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድበውና አልኮልን ማስተዋወቅ የሚከለክለው አዋጅ ፀደቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድብና አልኮልን በብሮድካስት ሚድያ ማስተዋወቅ የሚከለክለውን አዋጅ አፀደቀ። ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች አልኮል መሸጥ ክልክል መሆኑም ተገልጿል። የምክር ቤቱ አባላትም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያዩ በኋላም አፅድቀውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ዛሬ ያፀደቀው የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድበውና አልኮልን በብሮድካስት ሚድያ ማስተዋወቅ የሚከለክለውን አዋጅ በመስሪያ ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና የወጣቶች መዝናኛ በሚገኙባቸው ...
Read More »የፖለቲካ ፓርቲዎች ህገ መንግስቱን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይደነገጋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)የፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ ፓርቲዎች ህገ መንግስቱን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ፣ ህገ መንግስቱን ከሚፃረሩ ድርጊቶች እንዲታቀቡም ይደነግጋል ተባለ። የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንኙነታቸውንና የተናጠል እንቅስቃሴያቸውን የሚገዛ የአሰራር ስርዓት ረቂቅ ቃል ኪዳን ሰነድ ላይ ተወያይተዋል። በውይይቱ የክልልና የሃገር አቀፍ ፓርቲዎችን ጨምሮ በቅርቡ ከውጭ ሀገር የተመለሱ በምዝገባ ሂደት ላይ የሚገኙ በጥቅሉ 103 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገኝተዋል። በጋራ ምክር ቤቱ የቀረበው የቃልኪዳን ሰነድ በሦስት ምዕራፎችና ...
Read More »አሜሪካ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣች
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2011)አሜሪካ በኬንያ ናይሮቢ ለሚኖሩና ወደዚያ ለሚጓዙት ዜጎች የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣች። ብሪታኒያም ተመሳሳይ የጉዞ ማሳሰቢያ ይፋ ማድረጓ ታውቋል። ምዕራባውያንን ኢላማ ያደረገ የአሸባሪዎች ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ያለችው አሜሪካ ከናይሮቢ ባሻገር በሌሎች የኬንያ የባህር ዳርቻ ከተሞች የአብራሪዎች ጥቃት እንደሚኖርም አሳስባለች። የብሪታኒያ መንግስትም ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ የብሪታኒያ ዜጎች ከሶማሊያና ኬንያ ድንበር አካባቢ እንዲርቁ እንዲሁም ከባህር ዳርቻዎች እንዳይንቀሳቀሱ አሳስበዋል። በኬንያ ...
Read More »ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2011)የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበሩት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በ1969 ኢትዮጵያ በሶማሊያ በተወረረችበት ወቅት በአየር ላይ ውጊያ ሃገራቸውን ከታደጉ የበረራ ባለሙያዎች አንዱ የነበሩት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ለከፍተኛ ህክምና በተጓዙበት ህንድ ህይወታቸው ያለፈው በትናንትናው ዕለት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። በ1983 ዓም የኢህአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ ካባረራቸው የበረራ ባለሙያዎች አንዱ የነበሩት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ በኤርትራ ...
Read More »የብሔራዊ እርቅና ሰላም እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽኖች አባላት ሹመት ጸደቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2011)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች አባላትን ሹመት አጸደቀ። ሹመቱ ፖለቲከኞች፣ የሀይማኖት እባቶችን እና ታዋቂ ሰዎችን ያካታተ ነው። የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ለማጽደቅ በተሰጠው ድምጽ 22 ታቃውሞና 4 ድምጸ ታእቅቦ ተመዝግቧል። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የቀረቡ 40 እጩ አባላትን ሹመት በ22 ...
Read More »አቶ ዛዲግ አብርሃ ከድርጅታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2011)ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕውሃት/ ከለውጡ በተቃራኒው በሚያደርገው ጉዞ እና በራያ ህዝብ ላይ በሚያደርሰው በደል ሳቢያ ከድርጅቱ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ። በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዲሞክራታይዜሽን ማዕከል አስተባባሪ በመሆን የሚያገለግሉት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለሕወሃት ያስገቡት 5 ገጽ ማመልከቻ ኢሳት ደርሶታል። ቀደል ሲል የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ድኤታና የፍትህና የህግ ስርዓት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዛዲግ አብርሃ “ለሕዉሃት ልዩ ...
Read More »በሶማሊያ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ 11 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 27/2011)በሶማሊያ ርዕሰ መዲና ሞቃደሾ ዛሬ አሸባሪዎች የጠመዱት ፈንጂ ፈንድቶ 11 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ቆሰሉ። አልጀዚራ እንደዘገበው ሞቃደሾ በሚገኝ በአንድ የገበያ አደራሽ አቅራቢያ ባለ የመኪና ማቆሚያ ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ በፈንጂው ፍንጣሪና በፍርስራሹ 10 ሰዎች ወዲያውኑ መሞታቸው ተረጋግጧል። ሞቃዲሾ የገበያ አደራሽ ውስጥ በደረሰው በዚህ ፍንዳታ 11 ሰዎች ወዲያውኑ መሞታቸውን የሶማሊያ ፖሊስ መኮንን ሞሃመድ ሃሰን ለሮይተርስ ያረጋገጡ ሲሆን 10 ሰዎች ...
Read More »