(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010) የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ነባር ታጋዮች በንቅናቄው 37ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ተገለጸ። በግብርና ስራ የተሰማሩና በኑሮ የተጎሳቆሉት የቀድሞ የንቅናቄው ታጋዮች ዛሬ የታወስንበት ምክንያት ሊገለጽልን ይገባል የማለት ተቃውሞ ማቅረባቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ብአዴን የተመሰረተበትን 37ኛ ዓመት ሲያከብር በመርሃግብር ከያዛቸው መርሃ ግብሮች አንዱ ለንቅናቄው ነባር ታጋዮች እውቅናና የምስክር ወረቀት መስጠት ነበር። ይሁንንና የትም ወድቀው የቀሩና ብዙዎች ...
Read More »Author Archives: Central
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጡ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010)የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ታወቀ። ለአንድ ሳምንት ትምህርት አቁመው ጥያቄያቸው እስኪመለስ ቢጠብቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ግቢውን ሙሉ በሙሉ ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የታጠቁ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት ተማሪዎችን እየደበደቡ መሆናቸውም ታውቋል። በመቱ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች አልተመለሱም። በግቢው የቀሩትም ትምህርት አለመጀመራቸው ታውቋል። ከአንድ ሳምንት በላይ ትምህርት አቋርጠው የቆዩ የቡሌ ሆራ ...
Read More »ሜቴክ ከኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ ነው
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010)ሜቴክ በአቶ አርከበ እቁባይ ትዕዛዝ ከኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ እንደሆነ በፓርላማ ተገለጸ። ጥሬ ሐብቱ እየተበዘበዘበት ያለው ህዝብም ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው። በሕወሃቱ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/በሕግ ከተቋቋመበትና ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ከኦሮሚያ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ መሆኑ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ...
Read More »የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በግራ ዳኛው መዳኘት አንፈልግም አሉ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010) በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረቡት የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በግራ ዳኛው መዳኘት አንፈልግም ሲሉ ተቃውሞአቸውን አሰሙ። ሌሎች በችሎቱ የነበሩ ተከሳሾችም የመንግስትን አቋሚ በሚያንጸባርቁትና የሕወሃት የፖለቲካ አራማጅ በሆኑት ዘርአይ ወልደሰንበት አንዳኝም በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ከተከሳሾቹ የተነሳው ጥያቄ ትክክል መሆኑንና እንደዚህ አይነት አቋም ያለው ዳኛ ተከሳሾቹ ቅሬታ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን አስወግደው በጋራ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩና በተለያዩ ማህበረሰቦች የተደራጁ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን አስወግደው በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በጋራ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ። በዚህም በግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመታደግ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ በጋራ ያስተባበሩትና ለተፈናቃዮች መደገፊያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት ነገ በሴንትፖል ሚኒሶታ እንደሚካሄድ ታውቋል። በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚኖሩትና በተለያዩ ማህበረሰቦች ተደራጅተውና ሳይደራጁ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በአንድነት ለመንቀሳቀስ ...
Read More »ሮበርት ሙጋቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ መድረክ ላይ ታዩ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)ሮበርት ሙጋቤ ከሁለት ቀናት የቁም እስር ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ መድረክ ላይ መታየታቸው ታወቀ። ስልጣኑን ለጊዜው የተቆጣጠረው ወታደራዊ ሃይል ሙጋቤ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው በሰላማዊ መንገድ እንዲለቁ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁም ታውቋል። ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ለነገ ተዘጋጅቷል። የስልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ አንድ አመት የቀራቸው ዶክተር ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ የመሪነቱን ስፍራ ለባለቤታቸው ለማመቻቸት ምክትላቸውን ከወር በፊት ከስልጣን ማባረራቸው ...
Read More »አዘዞ በሚገኘው የ24ኛው ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ተፈጸመ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010) ጎንደር አጠገብ አዘዞ በሚገኘው የ24ኛው ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አስታወቀ። ዛሬ ንጋት ላይ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት የካምፑ የተወሰኑ ቤቶች በቃጠሎ መውደማቸውን ንቅናቄው አስታውቋል። በተያያዘ ዜና ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ከባድ ተሽከርካሪ /ቦቴ/ ላይ በተወሰደ ርምጃ ተሽከርካሪው ከጫነው ነዳጅ ጋር መውደሙን አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ገልጿል። የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ...
Read More »የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ ችግሮችን እንዳባባሰ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010) የትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተከሰቱ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ችግሮቹን እንዳባባሰ ተገለጸ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የችግሮቹ ዋነኛ ምንጭ ትንሽ የሚባሉ ተማሪዎች ናቸው ሲል የሰጠው ሰበባዊ መግለጫ ለችግሩ መባባስ በምክንያትነት ተቀምጧል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌጤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያጋጠሙ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ በተቋማቱ የተፈጠረው ችግር በ20ና 30 ተማሪዎች ማሳበባቸው ችግሩን እንዳባባሰው ነው ለኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ...
Read More »በባህር ዳር የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)ከባህርዳር ከነማ ጋር ውድድሩን ሊያካሂድ ባህርዳር የገባው የአክሱም ከነማ እግር ኳስ ቡድን ያረፈበት ሆቴል ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ውጥረት መንገሱ ተሰማ። ማምሻውን የልዩ ሀይል ፖሊሶች ተጫዋቾቹን ከሆቴሉ ለማስወጣት እየሞከሩ መሆናቸው ታውቋል። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ነገ ይካሄዳል ተብሎ ስለሚጠበቀው ጨዋታ ግን የተባለ ነገር የለም። በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ /ባቱ/ ከተማ በግለሰቦች መካከል ተቀስቅሷል የተባለ ጸብ ወደ ሌሎች ...
Read More »በሻኪሶ ዛሬ ከባድ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 8/2010)በሻኪሶ ዛሬ ከባድ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ለተቃውሞ የወጡት ሜድሮክ ኢትዮጵያ በአካባቢው የሚያከናውነውን የወርቅ ማውጣት ስራ ለተጨማሪ 10 አመት እንዲታደስለት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የሰልፈኞቹ ለተቃውሞ መውጣት ምክንያቱ ይህ ነው ይባል እንጂ ዋነኛ ጥያቄያቸው ግን የወያኔ ስርአት ይብቃን የሚል ነው። ሜድሮክ ኢትዮጵያ በሻኪሶ የወርቅ ማዕድን ለማውጣት ከህወሃት መንግስት ጋር የተፈራርመው የ20 አመት ውል ...
Read More »