(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ካበደረው 5.6 ቢሊየን ብር ውስጥ 3.6 ቢሊየን ብር የተበላሸ ብድር ሆኗል ሲል አረጋገጠ። ልማት ባንኩ ለሰፋፊ እርሻዎች መቀበል የጀመረውን የብድር ጥያቄም ማቆሙን አስታውቋል። በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች ለተሰማሩበት የጋምቤላ የእርሻ ልማት የተሰጠው ብድር ከ63 በመቶ በላይ የተበላሸ ተብሎ የተሰረዘው ባለሀብቶቹ ተጠያቂ እንዳይሆኑ በሚል መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ። የኦክላንድ የምርምር ተቋም በጋምቤላ ...
Read More »Author Archives: Central
4 የህግ ታራሚዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) በሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ 4 የህግ ታራሚዎች በፖሊስ በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገለጸ። ፖሊስ ሊያመልጡ ሲሉ ነው የተገደሉት ይላል። የሲዳማ ሀርነት ንቅናቄ በግፍ ተገድለዋል ሲል ለኢሳት ገልጿል። የሲዳማ ወጣቶች መብታቸውን በመጠየቃቸው በጅምላ እየታፈሱ መሆኑም ተገልጿል። በሌላ በኩል በሲዳማና በወላይታ ወሰን ላይ ግጭት ለመፍጠር በህወሃት አገዛዝ የሚደረገውን ቅስቀሳ ህዝቡ እንዲያከሽፈው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ጥሪ አድርጓል። ግድያው የተፈጸመው ታህሳስ 30 ...
Read More »በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የ45 ሰዎች ሕይወት አለፈ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ርዕሰ መዲና ኪንሻሳ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ45 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በአደጋው ከሞቱት ውስጥ አምስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸው ታውቋል። ከአፍሪካ ከተሞች በሕዝብ ብዛት በሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውና 12 ሚሊየን ያህል ሕዝብ የሚኖርባት የኮንጎዋ ርዕሰ መዲና ኪንሻሳ ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ የሆኑት ለ5 ቀናት ያህል ሳያቋርጥ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እንደሆነም ታውቋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ...
Read More »የውጭ ጉዲፈቻ ታገደ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) ኢትዮጵያ ሕጻናትን በጉዲፈቻ ወደ ውጭ ለመውሰድ የሚፈቅደውን ሕግ በፓርላማ በኩል አገደች። ሕጉ የታገደው በጉዲፈቻ ስም በውጭ ዜጎች ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ ሕጻናት ለበርካታ ጊዜያት በአሳዳጊዎቻቸው ከፍተኛ በደል እንደሚደርስባቸው በመታወቁ ነው ተብሏል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በጉዲፈቻ መልክ ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ ሕጻናት ብዙዎቹ ደብዛቸው ሲጠፋ አንዳንዶቹ ደግሞ እስከመገደል ደርሰዋል። ሕጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ በሚል ከኢትዮጵያ በርካታ ልጆች ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1999 ...
Read More »ሰላም ባስና ዳሽን ቢራ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተጠራ አድማና ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሰላም ባስና ዳሽን ቢራ አስታወቁ። የቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ያነጋገራቸው የሁለቱ ድርጅቶች ሃላፊዎች እንዳሉት በአድማውና በጥቃቱ ምክንያት ከኪሳራ ባሻገር ህዝቡ በአገልግሎታችን እንዳይጠቀም ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጥሯል። ሰላም ባስ በአራት መስመሮች አገልግሎት ማቋረጡን ሲያሳውቅ ዳሽን ቢራ በተለይ በባህርዳር ከፍተኛ የተቀባይነት ቀውስ እንደገጠመው ገልጿል። ለቢቢሲ አማርኛ ቃለ መጠይቅ የሰጡት የሰላም ...
Read More »በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተጎዱ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በአምቦ ዩኒቨርስቲ በተነሳ ተቃውሞ ተማሪዎች መጎዳታቸው ታወቀ። ባለፈው እሁድ የገና በአል ላይ በምግብ አዳራሽ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ግጭት መፈጠሩ የታወቀ ሲሆን እስከትላንት ድረስም መቀጠሉ ታውቋል። በዩኒቨርስቲው የሰፈረው የአጋዚ ሰራዊት ተማሪዎች ላይ ክፈኛ ድብደባ መፈጸሙን ተከትሎ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ለትምህርት ሚኒስቴር የቅሬታ ደብዳቤ መላካቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የተወሰኑ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወተዋል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ትምህርት ሚኒስቴር ጥቃት የፈጸሙትን ...
Read More »የፖለቲካ እስረኞች ከ15 እስከ 18 አመታት የእስር ጊዜ ተፈረደባቸው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በኢትዮጵያ 33 የፖለቲካ እስረኞች ከ15 እስከ 18 አመታት የእስር ጊዜ ተፈረደባቸው። የፊደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ሚፍታህ ሼህ ስሩር የክስ መዝገብ በግንቦት 7 የተከሰሱ 33 ግለሰቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል። ግለሰቦቹ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው በሽብርተኝነት ስም የተከሰሱ መሆናቸው ነው የተነገረው። በክስ መዝገቡ ከተካተቱት ተከሳሾች ቀሪዎቹ ክደው በመከራከራቸው የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ከሀገር ...
Read More »እነ አቶ በቀለ ገርባ የ6 ወራት ተጨማሪ እስራት ተወሰነባቸው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት የሆኑ ተከሳሾች ፍርድ ቤትን ደፍራችኋል በሚል የ6 ወራት ተጨማሪ የእስራት ቅጣት ተወሰነባቸው። ውሳኔው የተለለፈው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የራሱን ውሳኔ በመሻር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለምስክርነት አይቀርቡም ሲል ውሳኔ ማሳለፉን በመቃወማቸው ነው። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ከዚህ ቀደም በሰጠው ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ...
Read More »ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤልን የወሲብ ቅሌት ይፋ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) የሕወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤልን የወሲብ ቅሌት የሚያሳይ ማስረጃ ይፋ ሆነ። ዶክተር ደብረጺዮን በወሲብ ጉዳይ ላይ የኢሜልና የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚያጋልጥ መረጃ ተሰብሮ ወጥቷል። በወጣው መረጃ ላይ ዶክተር ደብረጺዮን ዘወትር የሚጎበኟቸውን የወሲብ ድረገጾች፣ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያደረጓቸውን ግንኙነቶችና ሌሎች ቅሌቶች ይፋ ሆነዋል። የትግራይ ክልልን እንዲመሩ ትላንት የተሰየሙት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የኤሌክትሮኒክስ መልዕክት ሳጥናቸው ተሰብሮ ይፋ የሆነው መረጃ የቴክኖሎጂ ...
Read More »ሼህ መሃመድ አላሙዲን ከሆቴል ወደ ወህኒ ተሸጋገሩ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ባለጸጋ ሼህ መሃመድ አላሙዲንን ጨምሮ 60 ያህል እስረኞች ከሆቴል ወደ ወህኒ ቤት መሸጋገራቸው ይፋ ሆነ። የሳውዳረቢያ መንግስት በድርድር እንዲፈቱ የጣለባቸውን የገንዘብ መጠን ለመክፈል ያልፈቀዱት እስረኞች በወህኒ ሆነው የሙስና ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ተመልክቷል። ምግብን ሳይጨምር ለመኝታ ብቻ በቀን 800 ዶላር እየተከፈለላቸው በዘመናዊው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ውስጥ የነበሩት ልኡላንና ባለጸጎች አልሔር ወደ ተባለው ወህኒ ቤት የተዛወሩት ከሶስት ቀናት ...
Read More »