(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 25/2011) የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በእሳት እየተቃጠለ መሆኑ ተነገረ፡፡ 4ኛ ቀኑን የያዘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ሆን ተብሎ በሰዎች የተለኮሰ መሆኑ ተነግሯል። የእሳት ቃጠሎወን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በእሳት እየጋየ መሆኑ ታውቋል። በፓርኩ የተከሰተው የእሳት አደጋ 4ኛ ቀኑን ይዟል። የአደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም አደጋውን ...
Read More »Author Archives: Central
ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት ከ126 የአለም ሃገራት 118ኛ ደረጃ ላይ መሆኗ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 25/2011)ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት መለኪያ ከ126 የዐለም ሐገሮች 118ኛ ደረጃ መያዟን አንድ ጥናት አመለከተ። በዓለም የፍትሕ ፕሮጀክት በተሠራውና በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሰሞኑን ይፋ በተደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ከ126 አገሮች 118ኛ ደረጃን መያዟ ታወቋል፡፡ በዓለም የፍትሕ ፕሮጀክት የተሰራው ጥናት ለሕግ ተገዥነትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመለካት 120,000 የቤት ለቤትና የ3,800 ባለሙያዎችን አስተያየት መነሻ በማድረግ የዳሰሳ ጥናት አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉና በጥናቱ ...
Read More »ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተበድረው ያልመለሱ በሕግ ሊጠየቁ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2011)ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተለይ ለእርሻ ሥራ ተበድረው ያልመለሱ በሕግ እንዲጠየቁ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ። ለእርሻ ሥራ ከልማት ባንክ ብድር ተበድረው ባልመለሱት ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እየተወሰደ ያለው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰጠው መመርያ መሠረት ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበላሸ ብድር ከ 40 በመቶ በላይ ደርሷል።ይህ የተበላሸ ብድር መጠንም ባንኩ በአስከፊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመላካች ነው።የልማት ባንክ የተበላሸ የብድር መጠን አሁን ...
Read More »የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አዛዥ ለትግራይ ህዝብ ጥሪ አቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2011)የትግራይ ህዝብ በህወሃት መሪዎች የሚደረገውን የጦርነት ትንኮሳ እንዲያወግዝ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አዛዥ ጥሪ አቀረቡ፡፡ አዛዡ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንደገለጹት የህወሃት የመከላከያና የደህንነት ሃላፊዎች የትግራይን ህዝብ ለአላስፈላጊ ግጭት እየቀሰቀሱት ነው፡፡ በሌብነትና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም ትግራይ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙት የህወሃት የጦር ጄነራሎች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት የትግራይን ህዝብ ለጦርነት ...
Read More »በወልቃይት ዳንሻ ሁለት ወጣቶች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2011)በወልቃይት ዳንሻ ባለፉት ሁለት ቀናት በትግራይ ልዩ ሃይል በተከፈተ ጥቃት አንድ ወጣት ተገደለ፡፡ አራት ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል። በዳንሻ የአማራ ክልል ሰሌዳ ያላቸው ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጡ መከልከሉን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የትግራይ ልዩ ሃይል ከ60 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማሰሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ ትላንት የ19 ዓመት ዕድሜ ያለው ወጣት በመገደሉ የዳንሽ ነዋሪ ለተቃውሞ አደባባይ መውጣቱም ታውቋል፡፡ ተጨማሪ ሃይል ያስገባው የትግራይ ...
Read More »በወላይታ ሶዶ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ አራት ሰዎች መሞታቸው ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2011) በወላይታ ሶዶ ህገወጥ ቤቶችን ማፍረስ በሚል በተነሳ ግጭት የፖሊስ አባላትን ጨምሮ አራት ሰዎች መሞታቸው ተሰማ። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። እንደ መረጃው ከሆነም ህገወጥ ተብለው ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ዳስ እንዳይጥሉ ተከልክለዋል። የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ካለው ተግባር እንዲቆጠብ የወላይታ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ግንባር ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ታውቋል። ግንባሩ በቅርቡም ሰላማዊ ሰልፍ ...
Read More »123ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለመዘከር ዝግጅቱ ተጠናቋል
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)123ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለመዘከር የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ እና በሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ድርጅት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ለኢሳት ገለጸ። የሂውስተን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ድርጅት እንደገለጸው የአድዋ ድል በዓልን በመጪው ቅዳሜ በተርጉድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል። ይሕ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበስረሰብ በሰሜን አሜሪካ በመጭው እሁድ 123ኛወ የአድዋ ድል በዓል ለማክበር ...
Read More »በወላይታ ሶዶ ቤቴ አይፈርስም ያሉ አዛውንት በግሬደር ተገጭተው ሞቱ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2011)በወላይታ ሶዶ ቤቴ አይፈርስም ያሉ አዛውንት በግሬደር ተገጭተው መገደላቸውን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ። በከተማዋ በህገወጥ መንገድ ቤት ገንብታችኋል በሚል ከ2ሺ በላይ አባወራዎች መፈናቀላቸው ተሰምቷል። ከሳምንት በፊትም በዛው በወላይታ ኦቶና በሚባል አካባቢ ዘጠኝ መቶ የሚሆኑ ቤቶች መፍረሳቸውንና ነዋሪዎቹም አደባባይ ላይ እንዲወድቁ መደረጋቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። መነሻው ህገወጥ ግንባታ የሚል ነው ይላሉ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች። ከሳምንት በፊት የመጀመሪያ ዙር ...
Read More »የኦሮሚያ የአዲስ አበባ ልዮ ጥቅም ጉዳይ በምክክርና ህግን በተከተለ ሁኔታ ብቻ ይፈታል
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2011)ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ያላት ልዮ ጥቅም ጉዳይ በታሪክና በህገ-መንግስቱ መሰረት በምክክርና ህግን በተከተለ ሁኔታ ብቻ እንደሚፈታ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ገለጹ። የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮችን ሌላ መልክ በመስጠት አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳና እርስ በእርሱ እንዲጋጭ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መላው ህዝብ እንዲታገል አቶ ለማ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ፕሬዝዳንት ጥሪውን ያቀረቡት በአዳማ ከተማ በተካሄደው 9ኛው የጨፌው ጉባኤ ...
Read More »ደኢህዴን የፌዴራል ስርዓቱ ለክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የህልውና ጉዳይ ነው አለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)የፌዴራል ስርዓቱ ለክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የህልውና ጉዳይ እንደሆነ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ገለጸ። ደኢህዴን ህብረብሄራዊነትን የሚያስተናግደውን የፌደራል ስርዓት አጠናክሮ ማስቀጠል የክልሉ መሪ ድርጅት የሁል ጊዜ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀጥል በስብሰባው አቅጣጫ አስቀምጧል። አዳዲስ የክልል ጥያቄዎች የክልሉን መሪ ድርጅት ቀጣይነት፣ ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታ እና የሁሉንም ህዝብ ጥቅም ማዕከል ተደርጎ መታየት እንዳለበት ማዕከላዊ ኮሚቴው ገልጿል። የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን ...
Read More »