123ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለመዘከር ዝግጅቱ ተጠናቋል

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)123ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለመዘከር የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ እና በሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ድርጅት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ለኢሳት ገለጸ።

የሂውስተን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ድርጅት እንደገለጸው የአድዋ ድል በዓልን በመጪው ቅዳሜ በተርጉድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።

ይሕ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበስረሰብ በሰሜን አሜሪካ በመጭው እሁድ 123ኛወ የአድዋ ድል በዓል ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል።በእለቱ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ከኢትዮጵያ በክብር እንግድነት

እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

123ኛው የአድዋ ድል በዓል የካቲት 12 በመላው ኢትዮጵያ የሚከበረው ጀግኖች አባቶች የጣሊያንን ወረራ የመከቱበትን እለት በማስታወስ ነው።

የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ምልክት ሆኖ ለአፍሪካውያንም ጭምር የኩራት ምንጭ መሆኑ ይታወቃል።

የቀኝ ግዛትን ተስፋፊነት የመከተውና በአጼ ሚኒሊክ መሪነት በድል የተጠናቀቀው የአድዋ ጦርነት ለመላ ኢትዮጵያውያን በነጻነት መኖር ካደረገው አስተዋጽኦ ሌላ ዜጎች በራሳቸው እንዲተማመኑ ያደረገ መሆኑም ይታመንበታል።