(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤት ገለጹ። ችሎት ቀርበው የደረሰባቸውን በደልና ስቃይ የገለጹት የኮሚቴው አባላት በቀል እየተፈጸመብን ነው ሲሉም ተናግረዋል። በወልቃይት ጉዳይ በአደባባይ አቋማቸውን ያሳወቁትን ዳኛ ዘርአይ ወልደሰበትን በመቃወሜ ከህዳር 26 ጀምሮ ከ2 ወራት በላይ በጨለማ ቤት ታስሬ እገኛለሁ ሲሉ የኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ መብራቱ ጌታሁን ለችሎቱ ገልጸዋል። በዛሬው ...
Read More »Author Archives: Central
ለያያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ተጨማሪ 9 ቢሊየን ብር ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) ሜቴክ ያያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 9 ቢሊየን ብር እንዲከፈለው ጠየቀ። ማዳባሪያ ፋብሪካው ተሰርቶ መጠናቀቅ የነበረበት ከ6 አመት በፊት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። በሕወሃት ጄኔራሎች የሚመራው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ከያዛቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል ያያ ማዳበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው። ሜቴክ ማዳበሪያ ፋብሪካውን አጠናቆ ለመጨረስ የሚፈጅበት ሁለት አመት ብቻ እንደሆነና የፕሮጀክቱ ወጪም 11 ቢሊየን ብር እንደሆነ የገባው ውል ...
Read More »ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ሁለተኛ ሆነች
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ከቻይና ቀጥሎ በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች መባሉን የሀገሪቱ አገዛዝ አስተባበለ። በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል በሰጠው መግለጫ ኢንተርኔት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም ሲል አስተባብሏል። ፍሪደም ሃውስ የተባለው አለም አቀፍ ድርጅት ሰሞኑን ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በማፈን ከአለም ከቻይና ቀጥሎ 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች የሚል ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል። በፍሪደም ሃውስ ሪፖርት መሰረት ቻይና፣ ኢትዮጵያና ሶሪያ ...
Read More »ከ700 የሚበልጡ እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2010) ላለፉት 7 አመታት ያህል በወህኒ የቆዩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ ከ700 የሚበልጡ እስረኞች እንዲፈቱ መወሰኑን የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ጠቅላይ አቃቢ ህግን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃኑ እንደዘገቡት በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው እስረኞች ቁጥር በአጠቃላይ 746 ናቸው። ከመስከረም 3/2004 ጀምሮ በወህኒ ቤት የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ከተፈቺዎቹ ውስጥ በስም ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ...
Read More »ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ ሰልፍ እንዲዘጋጅ ጠየቁ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር በዋሽንግተን ታላቅ ወታደራዊ ሰልፍ/ፓሬድ/እንዲያዘጋጅ ጠየቁ። በፕሬዝዳንቱ የቀረበው የወታደራዊ ትዕይንት ጥያቄ ከተለያዩ ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ባለፈው አመት በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የፈረንሳውያኑ አመታዊ ባስቲል ዴይ ወታደራዊ ሰልፍ ላይ ተገኘተው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ ሰልፉን “በሕይወቴ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ወታደራዊ ሰልፍ አይቼ አላውቅም” በማለት ገልጸውት ነበር። ስለፈረንሳዩ ሰልፍ አድናቆታቸውን የገለጹት ...
Read More »የበይነ መረብ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) በአለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል የተጠራውን የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ዘመቻ ለማጠናከር ዛሬ የበይነ መረብ ዘመቻ በማካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። ዘመቻው ፌስ ቡክንና ቲውተርን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ መረጃ መረቦች መጀመሩ ተገልጿል። የዘመቻው አላማ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ህዝብን ለመግደልና ለመጨቆን የሚጠቀምበት መሆኑን ለማሳወቅና የዘመቻውን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል። ...
Read More »ለፕሬዝዳንት ሙላቱ ህክምና የተጻፈው ደብዳቤ ሾልኮ ወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለህክምና ወደ ቻይና ይሄዳሉ በሚል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የተጻፈላቸውን የውስጥ ደብዳቤና የተመደበላቸውን የሰው ሃይል ብዛት የሚያሳይ መረጃ ይፋ ሆነ። የውስጥ ደብዳቤው ከፕሬዝዳንቱ ጋር ለህክምና ወደ ውጪ የሚጓዙት ሰዎች ብዛት 11 መሆኑን ያሳያል። ለእያንዳንዳቸው ተጓዦችም የ10 ቀናት የውሎ አበል በውጭ ምንዛሪ እንደተዘጋጀላቸውና ለመጠባበቂያ የሚሆንም 10ሺ የአሜሪካን ዶላር እንደተመደበላቸው መረጃው አጋልጧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ...
Read More »ኦህዴድ 14 የምክር ቤት አባላትን አባረረ 4 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አገደ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ 14 የምክር ቤት አባላትን በማባረር እንዲሁም አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ 4 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በማገድ ስብሰባውን አጠናቀቀ። ለአስር ቀናት በአዳማ ያካሄደውን ስብሰባ ትላንት ያጠናቀቀው ኦህዴድ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፣አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት እንዲኖርና ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን እንደሚሰራም አስታውቋል። የኦሮሞ ሕዝብ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን የሀገራችንን ቀጣይ ጉዞ የማቃናት ሚናውን ዛሬም እንደትላንቱ ሊጫወት ይገባልም ብሏል። ...
Read More »ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከሃላፊነት ሊነሱ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ በአሸናፊነት የወጣውና በአቶ ስብሃት ነጋ የሚደገፈው ቡድን ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ከሃላፊነት እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ገለጹ። የሕወሃትን የበላይነት ባስጠበቀ ሆኖም በሀገሪቱ የተከሰተውን ውጥረት በሚያረግብ መልኩ እየተከናወነ ነው የተባለው የሰራዊቱ አመራር ብወዛ፣በክፍለ ጦር አዛዦችና በተዋረድ ባሉ መዋቅሮች ላይ ምንም አይነት መሰረታዊ ለውጥ ሳያመጣ የሕወሃት ታጋዮች በአመራሩ ስፍራ እንደሚቀጥሉም ተመልክቷል። የሃገሪቱን አራት ...
Read More »በኬንያ ከተዘጉት ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁለቱ ስራ ጀመሩ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የሚያሳየውን ትዕይንት ለመዘገብ በመንቀሳቀሳቸው ከተዘጉት ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁለቱ ስራ መጀመራቸው ታወቀ። ሲትዝን የተባለው የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ግን አሁንም ከሳምንት በላይ ስርጭቱ እንደተቋረጠ ይገኛል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥር 30/2018 የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና እጩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የሚያሳየውን ...
Read More »