(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) ከሕገ መንግስታዊ ስርአት ውጪ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ዜጎች ካሳ ተከፍሏቸው ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ መድረክ አሳሰበ። በማፈናቀሉ ሒደት የተሳተፉ አካላትም እስካሁን ተጠያቂ አለመሆናቸውን መግለጫው አስገንዝቧል። በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/፣ አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት/አረና/፣Yeኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ/ኢሶዴፓ/ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ ትላንት ጋዜጣዊ መግለጫውን ሰጥቷል። መድረክ በዚህ መግለጫው መንግስት በህገወጥ መንገድ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ማያውቋቸው አካባቢዎች ...
Read More »Author Archives: Central
ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚሰየሙ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) ትላንት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚሰየሙ የኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለፓርቲና ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አቶ ደመቀ መኮንን ራሳቸውን ከምርጫው እንዳገለሉም አረጋግጠዋል። በተለያዩ ወገኖች ይፋ በሆኑ ተመሳሳይ መረጃዎች መሰረት ዶክተር አብይ አህመድ ከ170 መራጮች የ108ቱን ድምጽ በማግኘት መመረጣቸውም ታውቋል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ...
Read More »የአንድ አማራ ድርጅት አዲሱን የፖለቲካ ድርጅቱን አስተዋወቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010)በአማሮች ላይ ላለፉት 27 አመታት በተደራጀ መንገድ ሲካሄድ የነበረውን ጥቃት ለመከላከልና የአማራውን ሕልውና ለማስጠበቅ “በአንድ አማራ” ስር ተደራጅተናል ያሉ ኢትዮጵያውያን አዲሱን የፖለቲካ ድርጅታቸውን በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስተዋወቁ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩና በመአሕድ አባልነትና አመራር ውስጥ ጭምር ማለፋቸው የተገለጸው የአዲሱ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በሃገር ውስጥ የሚደርገውን ትግል ለማገዝና የአማራውን ሕልውና ለማስጠበቅ መነሳታቸውን ገልጸዋል። “የአንድ አማራ” ...
Read More »የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መልሶ መታሰር ተወገዘ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010) አለማአቀፉ የፕሬስ ተቋም የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን መልሶ መታሰር በጽኑ አወገዘ። ተቋሙ እስክንድር ነጋን ጨምሮ እንደገና የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖሊቲከኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አድርጓል። የእነ እስክንድር ነጋ መልሶ መታሰር በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ እንደሚያስፈልግ አመላካች መሆኑን ደግሞ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል። የአለም አቀፉ የፕሬስ ተቋም/አይፒአይ/ምክትል ዳይሬክተር ስኮት ግሪፊን እንዳሉት ከዚህ ቀደም እስረኞች ሲለቀቁ በኢትዮጵያ መልካም ነገር ይመጣል የሚል ተስፋ ተሰንቆ ...
Read More »የስዩም ተሾመ ጉዳይ በልዩ ሁኔታ በሚቋቋም ፍርድ ቤት ይታያል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010)የመምህሩና ጦማሪው ስዩም ተሾመ ጉዳይ በልዩ ሁኔታ በሚቋቋም ፍርድ ቤት እንደሚታይ ተገለጸ። መደበኛው ፍርድ ቤትም በፖሊስ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መዝገቡን ዘግቷል። በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ልዩ ፍርድ ቤት ማቋቋም በአዋጅ የተከለከለ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሷል በሚል ከአምቦ ዩኒቨርስቲ ወልቂጤ ካምፓስ የታሰረው ስዩም ተሾመ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሲታይ ነበር። ይህም ሆኖ ግን የስዩም ተሾመ ጉዳይ በአስቸኳይ ጊዜ ...
Read More »ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010) በሞያሌ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩን አለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ። መንግስት ስደተኞቹ እየተመለሱ መሆናቸውን ቢገልጽም አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ትላንት እንዳስታወቀው በየቀኑ 500 ሰዎች እየተሰደዱ ኬንያ በመግባት ላይ ይገኛሉ። ችግሩ በተፈጠረ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት 8 ሺ 200 ኢትዮጵያውያን መሰደዳቸውን ያስታወሰው አለም አቀፉ ቀይ መስቀል በመጪዎቹ 3 ቀናት ቁጥሩ ወደ 15ሺ እንደሚያሻቅብም አስታውቋል። ...
Read More »በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳን ጨምሮ ውጥረት መንገሱ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010)በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳን ጨምሮ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ውጥረት መንገሱ ተገለጸ። ጨለማን ተገን አድርጎ በተደራጀ መልኩ በቅኝት ያሉና በወታደራዊ ደህንነቱ ውስጥ የሚሰሩ ወታደሮች በሚያመሹበት ስፍራ መገደላቸው ውጥረቱን እንዳባባሰው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከሞያሌ 147 ተብሎ ከሚጠራው ካምፕ ወታደሮች እየጠፉ መሆኑንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል በሰራዊቱ ውስጥ ከሃምሳ አለቃ በላይ ማዕረግ ላላቸው የበታች ሹሞች የመቶ አለቅነት ማዕረግ ሊታደላቸው መሆኑን ...
Read More »ወታደራዊ እዙ በመተማ ዮሃንስ ያዘጋጀው ስብሰባ በተቃውሞ ተቋረጠ
ወታደራዊ እዙ በመተማ ዮሃንስ ያዘጋጀው ስብሰባ በተቃውሞ ተቋረጠ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው እሁድ መጋቢት 15/2010 ዓ.ም፣ በመተማ ዮሃንስ በቀበሌ 03 አዳራሽ ወታደራዊ እዙ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ከመተማ ህዝብ ጋር ለማድረግ የሞከረው ስብሰባ በከፍተኛ ሁከትና ብጥብጥ ምክንያት ስብሰባው ተቋርጧል። ህዝቡ ፣ “የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ መልስ ያግኝ፣ ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው የአባቶቻችን ርስት በአስቸኳይ ይመለስልን፣ በማስፈራራት ስልጣን ...
Read More »የአምቦ ዩንቨርሲቲ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት አይታይም ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቀ
የአምቦ ዩንቨርሲቲ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት አይታይም ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሶስት ሳምንት በፊት የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም ከሕግ አግባብ ውጪ በኮማንድ ፖስቱ ተይዞ ማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው በአምቦ ዩንቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበም። ፍርድ ቤቱ የካቲት 30 ቀን 2010 ...
Read More »አብዲ ኢሌን የሚቃወሙ የዲያስፖራ አባላት የታሰሩ ወላጆቻቸውን ለማስለቀቅ ሲባል በኢንተርኔት ይቅርታ እንዲጠይቁ እየተገደዱ ነው
አብዲ ኢሌን የሚቃወሙ የዲያስፖራ አባላት የታሰሩ ወላጆቻቸውን ለማስለቀቅ ሲባል በኢንተርኔት ይቅርታ እንዲጠይቁ እየተገደዱ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ/ም) በውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሊያውን የክልሉ ፕሬዚዳንትና ግብረ አበሮቻቸው የሚፈጽሙትን የጅምላ ጭፍጨፋ በመቃወም ድምጻቸውን ማሰማታቸው፣ እንዲሁም የክልሉ ህዝብ ለነጻነቱ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወገኖቹ ጋር በመሆን ለመብቱ እንዲነሳ ዱል ሚድድ የሚል ንቅናቄ መስርተው መታገል መጀመራቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ባለስልጣናት እርሳቸውን የሚቃወሙዋቸውን ሰዎች ወላጆችና ...
Read More »