(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2011)የኢትዮጵያ ስፓርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ /ኤስ ኤፍ ኤን ኤ/ በአንድ የቀድሞ የቦርድ አባሉ ቀርቦበት የነበረውን ክስ በድል ማጠናቀቁን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ። አስፋው ተፈሪ የተባለ የቀድሞ የፌዴሬሽኑ ቦርድ አመራር አባል ከሀላፌነቴ ያለአግባበ ተነስቻለሁ በሚል በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ክርክሩን በማሸነፉ 100 ሺ የአሜሪካን ዶላር በፌዴሬሽኑ እንዲከፈለው አስወስኖ ገንዘቡም ተከፍሎት ቆይቷል። ይህ በሆነበት ጊዜም ፌዴሬሽኑ ወሳኔውን በመቃወም የሰጠውን መግለጫ ...
Read More »Author Archives: Central
በራያ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ወከባና እንግልት እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2011)በራያ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ወከባና እንግልት እየተባባሰ መምጣቱን የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አግዘው ህዳሩ አስታወቁ። በተለይ ወጣቶች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ የሚደረገው አፈናና ድብደባ እየተባባሰ መቷል ብለዋል። ስቃይና እንግልቱ የበዛበት እንድ የራያ ወጣትም ራሱን ማጥፋቱ ታውቋል። የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄን ለማስመለስ የተለያዩ ስራዎችን ቢሰራም በራያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት ግን ሊቆም አልቻለም ይላሉ ...
Read More »በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2011)በኦሮሚያና በሱማሌ ክልሎች የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ ኢንስቲትዩቱ በሽታው በወረርሽኝ መልክ መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ በሽታውን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኙ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን በ11 ወረዳዎች፣ በምዕራብ ሃረርጌ ዞን በ4 ወረዳዎች ፣ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደግሞ በ2 ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ተከስቷል፡፡ በሱማሌ ...
Read More »የኢኒጂነር ታከለ ኡማ ሹመት የነዋሪው ውክልና የለውም በሚል የሚነሱ አስተሰሰቦች ህጋዊ መሠረት እንደሌላቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2011) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የኢኒጂነር ታከለ ኡማ ሹመት የነዋሪው ውክልና የሌለው ነው በሚል የሚነሱ አስተሰሰቦች ምንም ዓይነት ህጋዊ መሠረት የሌላቸው ናቸው ሲል የከተማዋ አስተዳደር ምክር ቤት ገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባልተለመደ ሁኔታ ስለ መዲናይቱ ከተማና በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ አንዳንድ ወገኖች በህግ የተቋቋመውን የአስተዳደሩን ተግባራት በማደናቀፍ ያልሆኑ ጥያቄዎችን የህዝብ በማስመሰል ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል ብሏል፡፡ እናም ...
Read More »በሚድሮክ ወርቅ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ለማንሳት የሚያስችል ደረጃ ላይ መደረሱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 12/2011)በሚድሮክ ወርቅ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ለማንሳት የሚያስችል ደረጃ ላይ መደረሱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ መግለጻቸው ተሰማ። የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት ለመገናኛ ብዙሀን ዝግ በነበረ ስብሰባ በዘርፉ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርጎ መሻሻል ስለሚገባቸው አሰራሮች ተነጋግሯል። እገዳው የሚነሳው ሚድሮክ በአካባቢው አስከትሎታል የተባለውን ብክለት የሚያጠና የተፅዕኖ ግምገማ ቡድን ጥናቱን አጠናቆ በመጨረሱ ነው ተብሏል። የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትሩ ዶር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንዳሉት ...
Read More »ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲስ የቦርድ አባላት ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 12/2011) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲስ የቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ። ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት አዲስ የቀረቡ ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባላትን ሹመት በዛሬው ዕለት መደበኛ ስብሰባው ላይ አፅድቋል። በዚሁ መሰረት አቶ ፍቃዱ ተሰማ ሰብሳቢ ሆነው ሲሾሙ አቶ ተፈራ ደርበዉ ፥ ዶ /ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አባል ፥ ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ፥ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ ...
Read More »ኢትዮጵያ እና ሱዳን እስረኞችንና የተያዙ ንብረቶችን ተለዋወጡ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 12/2011)የሱዳን እና የኢትዮጵያ መንግሥታት እስረኞችንና የተያዙ ንብረቶችን ተለዋወጡ፡፡ በቅርቡም በወሰን አካባቢ አልፎ አልፎ የሚነሱ ግጭቶችን ማስቆም በሚቻልባቸው እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተው የሁለቱም ሀገራት ኢታማዦር ሹሞች በተገኙበት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ በኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የ33ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ዓለሙ በሱዳን ታስረው የነበሩ ስድስት ኢትዮጵያውያን፣ ሁለት የእርሻ ትራክተሮች፣ አንድ ሞተር ሳይክል እና ከ40 ሺህ ብር በላይ ለኢትዮጵያ ...
Read More »የአባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ በደጀን ወረዳ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2011) በአማራ ክልል በዓባይ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር ሊሰሩ ከታቀዱ 20 ኢንዱስትሪዎች አንደኛው የሆነው የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ በደጀን ወረዳ ተጀመረ። የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታን ያስጀመሩት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን በአማራ ክልል ኢንዳስትሪዎችን ለማስፋፋት ከግል ባለሀብቱ ጋር የክልሉ መንግሥት የጋራ ጥምረት ፈጥሮ እየሰራ ነው ብለዋል። በደጀን የተጀመረው የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ክ8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ ...
Read More »የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተፈቀደለት በጀት ውጭ መጠቀሙ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2011)የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2009 ዓ.ም 331 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከተፈቀደለት በጀት ውጭ መጠቀሙን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አጋለጠ ። ሚኒስቴሩ የተጠቀሰውን ገንዘብ ከመጠቀሙ በፊት የገንዘብ ሚኒስቴርን ፈቃድ ማግኘት እንደነበረበትም ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ገልጿል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚኒስቴሩን የ2009 በጀት ዓመት የሂሳብ ኦዲት ግኝትን ገምግሟል። የፌደራል ዋና ኦዲተር ...
Read More »በሳውላ ማረሚያ ቤት የታሰሩ ወጣቶች ያለፍትህ እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2011)በጎፋ ዞን ሳውላ ማረሚያ ቤት የታሰሩ ወጣቶች ያለምንም ክስ ከአራት ወራት በላይ በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገለጸ። ኢሳት እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ቁጥራቸው 50 የሚደርሱት ወጣቶች የታሰሩት ባለፈው ህዳር 2011 ነው። በነዚህ ጊዜያት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የተደረጉት ወጣቶች በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው ድብደባና ኢሰብአዊ ድርጊት ለከባድ የጤና ችግር እያጋለጣቸው መሆኑን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ...
Read More »