Author Archives: Central

በመከላከያ እና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተጨማሪ ለውጦች እንደሚደረጉ ታወቀ

በመከላከያ እና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተጨማሪ ለውጦች እንደሚደረጉ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ነባር የመከላከያ አመራሮች እና የደህንነቱ ሹም ከስልጣን ተነስተዋል። ይህንን ተከትሎ በመከላከያ እና በደህንነቱ ተቋም የብሄር ተዋጽዖን ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች ከስልጣን እንደሚነሱ ታውቋል። ለረጅም አመታት የደህንነት ሹም በመሆን የሰሩት የህወሃቱ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ በጄ/ል አደም ኢብራሂም እንዲተኩ ...

Read More »

በአማሮ ወረዳ ያለው ግጭት ዛሬ ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ

በአማሮ ወረዳ ያለው ግጭት ዛሬ ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ (ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በአማሮ ወረዳ በጉጂ እና በኮሬ ማህበረሰብ መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ በመዋሉ የዜጎች ህይወት አልፏል። ከኮሬ በኩል በዳኖ ቡልቶ ቀበሌ የ49 ዓመቱ አርሶ አደር ሰንበተ ሳንኩራ እና የ42 ዓመቱ ጎልማሳ ቶማስ ገመደ ከብቶቻቸዉን በማገድ ላይ እንደነበሩ ሲገደሉ፣ ከ30 በላይ የቤት እንስሶቻቸው ...

Read More »

የሲ ኤን ኤኑ ጋዜጠኛ አንቶኒ ቦርዲያን ከዚህ አለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 1/2010) ታዋቂው የሲ ኤን ኤን የምግብ ዝግጅት ተራኪና ጋዜጠኛ አንቶኒ ቦርዲያን ከዚህ አለም በሞት ተለየ። አንቶኒ ቦርዲያን በፈረንሳይ ሆቴሉ ውስጥ ራሱን ገድሎ መገኘቱን የአለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የ61 አመቱ አንቶኒ ቦርዲያን በመላው አለም በመዞር ምግብ ነክ ዘጋቢ ፊልሞችን በማዘጋጀት ታዋቂነትን ከማትረፉም በተጨማሪ አለም አቀፍ ሽልማቶችንም አግኝቷል። አንቶኒ ቦርዲያን ዛሬ ጠዋት ለስራ ጉዳይ ባቀናባት ፈረንሳይ ሆቴል ውስጥ ራሱን ገድሎ ...

Read More »

የኢሮብ ወረዳ ሕዝብ የአልጀርሱን ስምምነት ተቃወመ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 1/2010) በትግራይ ክልል የኢሮብ ወረዳ ሕዝብ የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን በመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። የኢሮብ ነዋሪዎች የአልጀርሱ ስምምነት ከሁለት የሚከፍለን በመሆኑ እንቃወማለን ብለዋል። ሕወሃት በበኩሉ የአልጀርሱን ስምምነት በሚመለከት ባወጣው መግለጫ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽንን ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበሉ ተገቢ ነው ብሏል። በጉዳዩ ላይም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የሕወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መግለጫ እንደሚሰጡ ተነግሯል። ...

Read More »

ሜቴክ የሃገሪቱን ሃብት በከፍተኛ ደረጃ እያበከነ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 1/2010)  የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ /የሃገሪቱን ሃብት በከፍተኛ ደረጃ  በማባከን ላይ መሆኑ በፓርላማው ተገለጸ። ኮርፖሬሽኑ ውስጥ ባለው ችግር ሰራተኞች  ከሥራ እየለቀቁ መሆናቸውም ተመልክቷል። የስኳር እና የማዳበሪያ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ እየቀረበ ያለውም ሪፖርት የተምታታና የማይታመን መሆኑም  በፓርላማው ተገልጿል። መንግስታዊው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ረቡዕ ባወጣው ዘገባ በሕወሃት የጦር ጄኔራሎች ሲመራ የቆየው ሜቴክ በዘጠኝ ወራት ውስጥ  ያባከነው የሃገሪቱ ሃብት ከ9 ቢሊዮን ብር ...

Read More »

አቶ አባዱላ ገመዳ እና አቶ ግርማ ብሩ ጡረታ ወጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 1/2010) አቶ አባዱላ ገመዳ እና አቶ ግርማ ብሩ ጡረታ እንዲወጡ ተወሰነባቸው ። አቶ ግርማ ብሩ በሚኒስትርነት እና በአምባሳደርነት 27 ዓመታተ ሥርዓቱን ሲያገለግሉ ፣አቶ አባዱላ ገመዳ ደግሞ በጦር አዛዥነት፣በአፈጉባኤነት እና በክልል ፕሬዝዳንትነት ሰርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሁለቱን  የኦህዴድ የቀድሞ መሪዎች በጡረታ ያሰናበቱት በትናትናው ዕለት ነው። ኦሕዴድ በመጋቢት 1982 ሰሜን ሸዋ ደራ ላይ በሕወሃቱ የደህንነት ሃላፊ አቶ ክንፈ ገብረመድህን ...

Read More »

ሳሞራ ዩኑስ በጄኔራል ሳዕረ መኮንን ተተኩ

ሳሞራ ዩኑስ በጄኔራል ሳዕረ መኮንን ተተኩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ምትክ ጀነራል ሳዕረ መኮንን ጠቅላይ ኢታማዦር ሆነው ተሹመዋል። ኢሳት ከሁለት ሳምንት በፊት ምንጮቹን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና ፣ በኢህአዴግ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሹም ሽር ተከትሎ ለረጅም አመታት የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ሆነው የቆዩትን ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሰዓረ ...

Read More »

የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚኒስትሩ እንዲያናግሯቸው ጠየቁ

የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚኒስትሩ እንዲያናግሯቸው ጠየቁ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የህወሃት ደህንነቶች አንድ የአብዲ ኢሌን ተቃዋሚ ለመያዝ ያደረጉት ሙከራም ሳይሳካላቸው ቀርቷል በአብዲ ኢሌ ፍጹማዊ አገዛዝ የተማመሩ ከውጭ አገር ወደ አገር ቤት የተመለሱ እንዲሁም በክልሉ የሚኖሩ የአገር ሽማግሌዎች ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ ባለመሳካቱ ዛሬ በቤተመንግስት ዙሪያ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። የህወሃት ነባር አመራሮች ሽማግሌዎችን ...

Read More »

46 ኢትዮጵያውያን በኤደን ባህር ላይ ህይወታቸው አለፈ

46 ኢትዮጵያውያን በኤደን ባህር ላይ ህይወታቸው አለፈ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት በምህጻረ ቃሉ -አይ ኦ ኤም እንዳስታወቀው ትናንት ረቡዕ 100 የሚሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው መርከብ በመስጠሟ፣ 37 ወንዶችና 9 ሴቶች ህይወታቸውን አጥተዋል። 16 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። በጀልባዋ ላይ የተሳፈሩት ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ የገለጸው አይ ኦ ኤም፣ ከሶማሊያ የቦሳሶ ወደብ ተነስተው የመን ...

Read More »

ጄ/ል አለምሸት ደግፌና ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰላቸው

ጄ/ል አለምሸት ደግፌና ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰላቸው (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው ከ9 ዓመታት እስር በሁዋላ በቅርብ የተፈቱት ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌና የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዲየር ጀኔራል አለምሸት ደግፌ፣ ወታደራዊ ማዕረጋቸው እንዲመለስላቸው መደረጉን የጠ/ሚኒስትሩ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትወተር ገጻቸው አስታውቀዋል። ሁለቱም ጅኔራሎች ማእረጋቸውን እንደያዙ የጡረታ መብታቸው እንዲከበርላቸው መደረጉንም ባለስልጣኑ ገለጸዋል። ብርጋዴር ...

Read More »