ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- ድርጅቱ በፈረንጆች አቆጣጠር ዲሰምበር 30 እና 31 ባደረገው ጉባኤ ፣ ለረጅም አመታት ሲታገልበት የነበረውን የመገንጠል አጀንዳ በመሰረዝ ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ የሚመልስ የመታገያ አጀንዳ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ግንባሩ ሁሉም የኦሮሞ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎች ይህን አዲስ ራእይ እውን ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል። የድርጅቱ ጉባኤ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት በፊት በአቶ ዳውድ ኢብሳ ...
Read More »Author Archives: Central
አቶ መለስ ዜናዊ ዲሞክራሲን ለመገንባት የገቡትን ቃል አጥፈዋል ሲሉ አንድ የቀድሞ የአሜሪካ ዲፕሎማት ተናገሩ
ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠሪ የነበሩትና በኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያም ይመራ የነበረውን የኢትዮጵያን መንግስት ከ ኢህአዴግና ከሻእብያ ጋር ሲያደራድሩ የነበሩት አምባሳደር ሄርማን ኮህን፣ “መለስ ዜናዊ በምርጫ 97 የተሸነፈ ቢሆንም ፣ የህዝቡን ድምጽ ሰርቆ የመንግስት ስልጣን ይዞአል” ብለዋል። “በዚህም የተነሳ” ይላሉ አምባሳደሩ ፣ “ስልጣን ከመያዙ በፊት የገባውን ቃል አጥፏል።” አምባሳደር ኮህን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ...
Read More »በአዲስ አበባ የሚገኙ የመጽሀፍ አዙዋሪዎች በአቶ በረከት ስምኦን መጽሀፍ ያተረፍነው ስም ሳይሆን ስድብ ነው አሉ
ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጠው፣ የመጽሀፍ አዙዋሪዎች የአቶ በረከትን አዲሱን “የሁለት ምርጫዎች ወግ” መጽሀፍ በተጽእኖ እንዲሸጡ ቢደረግም፣ ከመጽሀፉ ሽያጭ ያገኙት ትርፍ ስድብና ውግዘት ብቻ ነው። ዘጋቢያችን “አንዱን የመጽሀፍ አዟሪ ” በቀን ውስጥ ስንት የአቶ በረከትን መጽሀፎች ትሸጣለህ?” ብሎ ሲጠይቀው፣ ” በቀን ውስጥ ስንት ስድቦችን አተረፍክ?” ብለህ ብትጠይቀኝ ይሻለኛል” ብሎ እንደመለሰት ገልጧል። ዘጋቢያችን እንደሚለው የአዲስ ...
Read More »የአቦሬ ገበያን ቃጠሎ ተከትሎ፣ በአካባቢው ኗሪ የነበሩ ሰዎች ጐዳና መውደቃቸውንና የወረዳ ስድስት አስተዳደርም ሕገወጥ ናችሁ በማለት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳያገኙ ማድረጉን ተዘገበ
ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት:- በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የአዋሬ ገበያ ከሁለት ሳምንት በፊት በተነሳ ቃጠሎ በርካታ የንግድ ቤቶችና መኖሪያዎች መውደማቸውን ተከትሎ፣ በአካባቢው ኗሪ የነበሩ ሰዎች ጐዳና መውደቃቸውንና የወረዳ ስድስት አስተዳደርም ሕገወጥ ናችሁ በማለት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳያገኙ ማድረጉን ሪፖርተር ዘገበ ላለፉት 22 ዓመታት በአዋሬ ገበያ አካባቢ እንደኖረችና ተወልዳ ያደገችው እዚያው የወደመው ሠፈር ውስጥ እንደነበር የተናገረችው ወጣት ገበያነሽ ለማ፣ የእሷን ...
Read More »በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ሙስሊሞች እየደረሰ ያለውን ጭቆና እንደሚቃወሙ ባወጡት መግለጫና በአሰባሰቡት ፊርማ አስታወቁ
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ከ1 ሺ በላይ የአንሳር መስጂድ አባላት ፣ በሙስሊሞች እየደረሰ ያለውን ጭቆና እንደሚቃወሙ ባወጡት መግለጫና በአሰባሰቡት ፊርማ አስታወቁ:: ሙስሊሞቹ ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓም ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ስራ አስፈጻሚ በጻፉት ደብዳቤ ” የህገ መንግስቱ ቁልፍ ድንጋጌዎች የሆኑት አንቀጽ 9/10/27ን በሚቃረን መልኩ የሙስሊም ዜጎችን የሀይማኖት በነጻነት ማራመድ የሚጋፉ ድርጊቶች ...
Read More »የኢትዮጵያ ጦር በለወደይን በምትባለው የሶማሊያ ግዛት ከፍተኛ ጦርነት እያካሄደ ነው ተባለ
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ከ3 ሺ እስከ 5ሺ የሚገመተው የኢትዮጵያ ጦር አብዛኛውን የበለደውይን ከተማ ተቆጣጥረዋል። የኢትዮጵያ ጦር ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም ውጊያ መክፈቱንም የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጠዋል። በለደወይን ወደ ሞቃዲሾ የምትወስድ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር መካከል የምትገኝ ስትራቴጂክ ከተማ ናት። ቢቢሲ እንደዘገበው በእስካሁ ጦርነት 20 የኢትዮጵያ ወታደሮች እና የአልሸባብ ተዋጊዎች ተገድለዋል። አልሸባብ ባለፈው ነሀሴ ወር ከሞቃዲሾ መውጣቱን ...
Read More »የዳርፉር አማጽያን መሪ የነበሩት ዶ/ር ካህሊል ኢብራሂም በአካባቢ እና አለማቀፍ ሀይሎች ጥምረት መገደላቸውን ምክትላቸው አስታወቁ
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህና የእኩልነት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሙሀመድ ሱሌይማን ባወጡት መግለጫ፣ መሪያቸው የተገደለው የአካባቢው ሀይሎች ከሱዳን መንግስት ጋር በጋራ በመመሳጠር ባወጡት እቅድ መሰረት መሆኑን አመልክተዋል። እነዚህ አገሮች የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ ዶ/ር ካሊልን ማስገደላቸውን የጠቀሱት ምክትላቸው፣ አሁን ባለበት ደረጃ የአገሮችን ስም ለማውጣት ባንፈቅድም፣ ከጥንስሱ ጀምሮ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሙሉ መረጃ እንደደረሳቸው አመልክተዋል። ንቅናቄው ወንጀሉን የፈጸሙትን ...
Read More »ግዛቷን አቋርጠው ወደ እስራኤል ለመግባት ሲሞክሩ የተደረሰባቸው 93 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሷን ግብፅ ገለፀች
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማላዊን ድንበር ሲያቋርጡ ከተያዙት ኢትዮጵያውያን መካከል አራቱ ረዥም ጊዜ በዘለቀ ረሀብ ሞተው አስከሬናቸው በሀይቅ ውስጥ ሲገኝ፤ ቀሪዎቹ 90 ኢትዮጵያውያንም በፍርድ ቤት ጥፋተኞች ተባሉ አሶሼትድ ፕሬስ የግብፅን አየር መንገድ ባስልጣናት ጠቅሶ ከካይሮ እንደዘገበው፤ ኢትዮጵያውያኑ በሱዳን ድንበር በኩል ወደ ግብፅ ገብተው የሲና በረሃን በማቋረጥ ወደ እስራኤል በሕገ ወጥ መንገድ ለመግባት ሲሞክሩ ነበር፤ በአየር መንገዱ ሰራተኞች አማካይነት ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት የስዊድን ጋዜጠኞችን ለማስፈታት ጫና የሚያደርግ ከሆነ እንደማይቀበሉት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ገለጡ
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ለመንግስት ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የስዊድን መንግስት እስካሁን ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ ይፋዊ የሆነ ጥያቄ አለማቅረቡን ተናግረው ይሁን እንጅ የአውሮፓ ህብረት ከመደበኛው ድርድር ውጭ ጫና ለማሳረፍ ቢሞክር ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል። የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት እና የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትን “መንታ ምላሶች” በማለት አቶ ሀይለማርያም ወቀሰዋቸዋል ተችተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ባለበት አለማቀፍ ጫና የተነሳ የስዊድን ጋዜጠኞችን ለመፍታት ቢፈልግም፣ ...
Read More »አዳማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ
ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የፌደራል ፖሊሲ በስፍራው በመገኘት ግጭቱን አስቁሟል። ይህንን ተከትሎም በርካታ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን የኦሮሞ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ሲጮሁ፣ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳት ሲጠይቁ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ መምህር ግጭቱ የብሄር ግጭት ...
Read More »