(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2011)የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ኢቢኤስ የሚባለው የሳታላይት ጣቢያ የተሳሳተ ማስታወቂያ በማሰራጨታቸው ከ22 ሚሊየን ብር በላይ እንዲከፍሉ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ ። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና ኢቢኤስ የማስታወቂያና የብሮድካስት ህጉን በመተላለፍ ሸማቹ እንዲታለል አድርገዋል በሚል 22 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተፈርዶባቸዋል። የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪን በግማሽ የቅድሚያ ክፍያ ከውጭ አስመጣላችኋለሁ በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ሰብስቦ ተሰውሯል የተባለው ዙና ትሬዲንግ ባለፈው ሐምሌ ...
Read More »Author Archives: Central
ከጋምቤላ ማረሚያ ቤት ያመለጡ 92 እስረኞች ሁለት ሰዎችን ገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2011)ከጋምቤላ እስር ቤት ከትላንት በስትያ ያመለጡ 92 እስረኞች ሁለት ሰዎችን ገደሉ። በሌሎች ሶስት ሰዎች ላይም ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል። የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት በአኝዋክ ዞን ኢታንግ ወረዳ ላይ ጥቃት የፈጸሙት እስረኞችን ማን እንዳስታጠቃቸው የታወቀ ነገር የለም። በሌላ በኩል በጋምቤላ አኝዋክ ዞን ጆር ወረዳ አንድ ወታደራዊ ካምፕ መገኘቱን ለኢሳት በደረሰ መረጃ ላይ ተመልክቷል። የተደራጁና ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች የሚገኙበት ይህው ...
Read More »በአፋር በተነሳ ተቃውሞ ከ100 በላይ ሰዎች ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2011) በአፋር ክልል በዞን አምስት ገለአሉ ሶምሮቢ በሚባል ወረዳ በተነሳ ተቃውሞ ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ። የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ለኢሳት እንደገለጸው በክልሉ የተንሰራፋውን ጎሰኝነት በመቃወም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ ለማስቆም የአፋር ልዩ ሃይል ደብደባና እስር በመፈጸም ላይ ነው። ለውጥ አፋር ላይ አልመጣም፣ ማሻሻያው ይበልጥ ጎሰኝነትን አስፋፍቷል በሚል የተነሳው ተቃውሞ ወደሌሎች አካባቢዎችም መዛመቱን ለማወቅ ተችሏል። የአፋር ...
Read More »አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ለማ መገርሳ ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2011)አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ለማ መገርሳ የውጭ ጉዳይና የሀገር መከላከያ ሚኒስትሮች ሆነው ተሾሙ። የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ደግሞ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሆነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በአቶ ለማ መገርሳ ምትክ ክልሉን እንዲመሩ ተሹመዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመት ...
Read More »የጌዲዮ ተፈናቃዮች ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2011) በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ መፍትሄ ካልተሰጠ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ በአካባቢው የተሰማሩ የህክምና ባለሙያዎች ገለጹ። ከህክምና ቡድኑ አባላት አንዱ ለኢሳት እንደገለጹት በአካባቢው ካለው የምግብና የውሃ እጥረት ጋር ተያይዞ በርካታ ተፈናቃዮች ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል። ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ርብርብ ቢደረግም ሕጻናቱን ከህመም ለመታደግ አልተቻለም ሲሉ ይገልጻሉ። በጌዲዮ ያለው የተፈናቃዮች ሁኔታ በቃላይ ከሚገለጸውና በወረቀት ከሚጻፈው በላይ ነው ይላሉ ...
Read More »በአፋር ክልል ወጣቶችን ማዋከብ ተጠናክሮ ቀጥሏል
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 10/2011)በአፋር ክልል ወጣቶችን የማዋከብና የማስፈራራት ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ። የአፋር የሰብአዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ከሆነ ወጣቶቹ በክልሉ ያሉት አሰራሮች ይቀየሩ በሚል በሰላማዊ መንገድ ለሚያቀርቡት ጥያቄ እየተሰጣቸው ያለው ምላሽ መሳደድ ሆኗል። ዛሬ ላይ ይላሉ አቶ ገአስ መሳሪያ የታጠቀ ልዩ ሃይልን ዞን አምስት ላይ በማሰማራት ቅሬታውን እያሰማ ያለውን ወጣት የማስፈራርቱን ዘመቻ ቀጥሎበታል። ...
Read More »ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀብራቸው ስነስርዓት በዩጋንዳ በብሄራዊ ጀግና የክብር ስነስርዓት እንደሚፈጸም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ አየር ሃይል የሀገሪቱን ከፍተኛ የጀግንነት የክብር ኒሻን ካገኙት ጥቂት ሰዎች አንዱ የሆኑት ኮለኔል ጌታሁን ካሳ በስደት ለሚኖሩባት ዩጋንዳ አየር ሃይል ከፍተኛ ተግባር በመፈጸማቸ የዩጋንዳ መንግስት ልዩ ክብር እንደሰጣቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1977 ጀምሮ ...
Read More »የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)ከ30 በላይ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጌዲዮ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ። አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ አቅርበዋል። ድምጻውያን፣የቲያትር ባለሙያዎች፣ ደራሲያንንና ሌሎች የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያሳተፈው የልኡካን ቡድን አባላት ዜጎች ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል። የተፈናቀሉት ዜጎች ወደነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢሳት ያነጋገራቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
Read More »የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እሳትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ጥረት አመርቂ አይደለም
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011) የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ጥረት አመርቂ አይደለም ተባለ። በሔሊኮፕተር የሚደረገው ጥረትም በቂ አይደለም ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ገልጸዋል። ውሃ በቅርበት አለመኖሩ በሄሊኮፕተር ጭምር እየተካሄደ ያለውን የማጥፋት ስራ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተመልክቷል። ከእስራዔል የእሳት አደጋ ባለሙያዎች በሰሜን ተራሮች ፓርክ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ ቢሳተፉም እሳቱን መቆጣትጠር እንዳልተቻለ መረጃዎች አመልክተዋል። እስከአሁን ከ700 ...
Read More »የወሊሶ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች የተቃውሞ አድማ እያደረጉ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)ካምፕ የገባው የኦነግ ጦር ተመርዟል መባሉን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የወሊሶ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች የተቃውሞ አድማ እያደረጉ ነው። በአድማው ምክንያት ከወሊሶ ወደ አዲስ አበባ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ ወሊሶ የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዳይገቡና እንዳይወጡ ወጣቶች መንገድ ዘግተዋል ተብሏል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ መግለጫ ያወጣው ኦነግ 200 የሚሆኑ የኦነግ ጦር አባላት የበሉት ምግብ የተበከለ በመሆኑ ለበሽታ መጋለጣቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡ የኦሮሚያ ...
Read More »