ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2004 ዓ.ም 10 ወራት ከማዘጋጃ ቤት ያገኘው ገቢ በግማሸ ማሸቆልቆሉን የኢሳት ምንጮች ገለጸዋል፡፡ አስተዳደሩ በተለይ በዋንኛነት ከሊዝና ከስም ዝውውር ጋር በተያያዘ ከሐምሌ 1 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ባሉት 10 ወራት 726 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም ማሳካት የቻለው 363 ነጥብ 3 ...
Read More »Author Archives: Central
የአሜሪካ የምክር ቤት አባላት የመለስ መንግስት የፕሬስ ነጻነትን ጨምሮ የዜጎችን መብት እንዲያከብር ጠየቁ
ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ሊቀመንበርና አሁን ሽብርተኝነትን፣ አውዳሚ የጦር መሳሪያን እና ንግድን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚመለከተውን ኮሚቴ የሚመሩት ኤድዋርድ ሮይሲ ለአቶ መለስ ዜናዊ በጻፉት ደብዳቤ ፣ በእስር ላይ ስለሚገኙት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ስላለው የፕሬስ አፈና ያላቸውን ስጋት ገልጠዋል። ያለ ፕሬስ ጠንካራ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት እንደማይቻል የገለጡት ሮይስ፣ በአገር ደህንነትና ሽብርተኝነትን ...
Read More »ሚኒስትሩን የዘለፈችው ሙስሊም ወጣት፤ በደህንነቶች በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ
ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩን ስብሰባ ላይ የዘለፈችው ሙስሊም ወጣት፤ በደህንነቶች በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ። ይህ አሳዛኝ ዜና ይፋ የሆነው፤የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ አካል የሆነው “ድምፃችን ይሰማ” ኮሚቴ ፦አሳዛኝ የግፍ ዜና”በሚል ርዕስ ያሰራጨው መረጃ ነው። በቅርቡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሙስሊሞችን ጥያቄ በተመለከተ ከየክፍለ-ከተማው ሰዎችን በመምረጥ ስብሰባ አካሂዶ እንደነበር ያወሳው ኮሚቴው፤በዚሁ ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ...
Read More »አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አይወክሉንም ሲሉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያን ተቃውሞ አሰሙ
ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በኢትዮጵያ -የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሚስተር አሮፕ ዴንግ ኩኦል እኛን አይወክሉንም” ሲሉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያን ተቃውሞ አሰሙ። ደቡብ ሱዳናውያኑ የአምባሳደር አሮፕን ሹመት የማይቀበሉት ከአገራቸው ብሔራዊ ጥቅም አኳያ ብቻ ሳይሆን፤የቪየና ኮንቬንሽን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነትን የጣሰ በመሆኑም ጭምር በመሆኑ ነው ማለታቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። የአምባሳደሩ ሹመት የቪየናን ኮንቬንሽን እንደሚጥስ ከተጠቀሱት ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በዋልድባ ከፍተኛ ሰራዊት በማሰማራት አካባቢውን ማረስ መጀመሩ ህዝቡን አስቆጣ
ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልድባ አካባቢ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ባለፉት ስድስት ቀናት በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢው በመሄድ የሰፈሩ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን መስፈር ተከትሎ አካባቢው መታረስ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል። የአካባቢው ህዝብ መከላከያ ሰራዊቱ ጋር ተፋጦ የሚገኝ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተፈጠረ ግጭት የለም። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው የአካባቢው ህዝብ በመንግስት ድርጊት በእጅጉ ማዘኑን ገልጠው፣ ...
Read More »ሚኒሰትሩ የጋምቤላ ችግር የእርስ በርስ ሽኩቻ ውጤት ነው አሉ
ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከግንቦት 10 እስከ 12 የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በጋምቤላ በተደረገው ስብሰባ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒሰትር የሆኑት አቶ ሺፈራው ተክለማርያም ” የክልሉ ችግር የእርስ በርስ የስልጣን ችኩቻ የወለደው ነው ” ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋምቤላ ሰላም በመጥፋቱ በርካታ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን እየጣሉ ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል፤ የክልሉን ጸጥታ የማስጠበቅ ስራ ለፌደራል ፖሊስና ለመከላከያ ...
Read More »በመተከል ለረጅም አመታት የቆዩ ህዝቦች ከአካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እየተደረገ ነው
ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመተከል ዞን -ዳንጉር ወረዳ ውስጥ ለእርሻ ሥራ ሄደው ለረጅም አመታት የቆዩ የአማራና የአገው ብሔር ተወላጆች በክልሉ ካድሬዎች ለጅምላ እስራት ከመዳረጋቸውም በላይ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እየተደረገ መሆኑን ፍኖተ-ነጻነት ዘገበ። በተጠቀሰው አካባቢ የአማራና የአገው ተወላጆች ለጅምላ እስራት መዳረጋቸውን ተከትሎ የወረዳው የሃይማኖት አባት ሰዎቹ የታሰሩበት እስር ቤት ድረስ በመሄድ፦ “ወዶ አማራና አገው ...
Read More »ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ያሰማው ተቃውሞ የኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ መሆኑን ቀጥሎአል
ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው መንግስት የአበበ ተቃውሞ እንዳይሰማ የኢንተርኔት ስርጭቶችን ቢዘጋም አስቀድመው ቪዲዮውን ያገኙ ኢትዮጵያውያን በሞባይል ስልክ ሳይቀር እየተቀባበሉት ነው። አንዳንድ ደፋሮች ለስልካቸው መጥሪያ እየተጠቀሙበት ነው ብሎአል። የከተማው ታላቁ የመወያያ ርእስ የአበበ ድርጊት መሆኑን የገለጠው ዘጋቢያችን ፣ ገዢው ፓርቲ መልእክቱ እንዳይሰራጭ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካላትም ብሎአል። በሌላ በኩል ደግሞ የገዢው ፓርቲ ...
Read More »በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተደረገው ተቃውሞ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቧል
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እንግዶች ሆነው ወደ አሜሪካ ከተጓዙት የአፍሪካ መሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መለስ ከፍተኛ ተቃውሞ በማስተናገድ በኩል ብቸኛው መሪ ናቸው። የጋና ፣ የታንዛኒያና የቤኒን መሪዎች ያለምንም ተቃውሞ ተልእኮዋቸውን ሲያሳኩ፣ አቶ መለስ ዜናዊ ከጉባኤ አዳራሽ ውጭ ብቻ ሳይሆን ባልጠበቁት ሁኔታ በአዳራሹ ውስጥ የገጠማቸው ተቃውሞ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቧል። በአውሮፓ ውስጥ ...
Read More »በጋሞጎፋ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ከፍተኛ ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገለጡ
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ባለስልጣናት በፈጠሩት ችግር ለዘመናት አብረው የኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች እርስ በርስ ለመጋጨት ተፋጠዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጠዋል። የደምባ ጎፋ ወራዳ አስተዳዳሪና ምክትል አስተዳዳሪ ሰሞኑን ወደ ዛንዳ ቀበሌ በመሄድ ግጭት ለመፍጠር መሞከራቸውን አንድ የአካባቢው ተዋቂ አዛውንት ተናግረዋል:: አዛውንቱ በአካባቢያቸው ያለው ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ይገልጣሉ ። እርሳቸው እንደሚሉት ከስምንተኛ ክፍል ...
Read More »