Author Archives: Central

በያዝነው ክረምት ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች መካከል የሚታሰሩ እንዳሉ ታወቀ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከፌደራል ፖሊስ የኢሳት ምንጮች በተገኘው መረጃ የፍርድ ቤቶችን መዘጋት አስታኮ በክረምቱ ወራት ከአንድነት ፓርቲ፣ ከፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እና ከፍትህ ጋዜጣ የሚታሰሩ መንግስት ስጋቴ ናቸው ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ። እንደመረጃ ምንጮች ሰዎችን በክረምት ለማሰር የተፈለገው ግለሰቦችን በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ለማሰቃየት እንዲያመች ነው። እስካሁን ድረስ እነማን ይታሰሩ እንማን ይቅሩ በሚለው ላይ የፖለቲካ ውሳኔ አልተሰጠም፣ ...

Read More »

ከ47 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አለቁ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ እንደዘገበው ከታንዛኒያ ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በማላዊ ሀይቅ ላይ ሰምጠዋል። ሟቾቹ የሶማሊያ ዜጎች መሆናቸው የተገለጠ ቢሆንም፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር ሰራተኞች አካባቢውን ከጎበኙ በሁዋላ እንዳረጋገጡት በርግጥም ስደተኞች የሶማሊያ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው። መርከቧ ከአቅም በላይ በመጫኗ ሳትሰምጥ እንዳልቀረች የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። እስካሁን ድረስ የ47 ሰዎች ...

Read More »

በሰሜን ሸዋ ዞን አንድነትን ወክለው በምርጫ የተወዳደሩት ግለሰብ ተገደሉ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቅዱስ ሀብት በላቸው ፍኖተ ነጻነትን በምንጭነት ጠቅሶ እንደዘገበው ፍቼ አካባቢ የሚገኘው ልዩ ስሙ ግራር ጀርሶ ጊዮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ውስጥ ይኖሩ የነበሩት አቶ ቸሩ ዘውዴ ባለፈው እሁድ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተገድለዋል። በምርጫ 2002 አንድነትን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የተወዳደሩት ሟች አቶ ቸሩ ዘውዴ፤ የአካባቢው ሃላፊዎች በተደጋጋሚ አባል የሆኑበትን የአንድነት ፓርቲን አውግዘው፣ የኢሕአዴግ ...

Read More »

በፍርድ ቤት ዳኞች ቁጣ ሕብረተሰቡ መማረሩ ተገለፀ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአገራችን በሚገኙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ውስጥ የተሰየሙ ዳኞች በባለጉዳዮች ላይ በሚያሰሙት ቁጣና ሃይለ ቃል በመረበሽ ባለጉዳዮች በችሎት ውስጥ ባግባቡ ሃሳባቸውን ባግባቡ ሳይገልፁ መመለሳቸው እውነት መሆኑን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ፕሬዚዳንት አመኑ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ፤- ከትናንት በስቲያ በፓርላማው ተገኝተው የ2004 ዓመት ሪፖርት ያቀረቡት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ፤ ይህንኑ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ...

Read More »

በሲዳማ ዞን በአለታ ጭኮ ከተማ በተደረገው ተቃውሞ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ተቃውሞው የተነሳው ከአዋሳ እጣ ፋንታ ጋር በተያያዘ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደተናገሩት በአለታ ጭኮ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ፖሊስ የታረደ ሲሆን ሁለት ነዋሪዎች በፖሊሶች ሳይገደሉ አልቀረም አራት ተማሪዎችም በጽኑ ቆስለዋል። በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የገለጠው ዘጋቢአችን በነገው እለት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ሊነሳ ይችላል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው። የመከላከያ ሰራዊት እና ...

Read More »

በሽብር ወንጀል በተከሰሱት በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ላይ ነገ ፍርድ ይሰጣል

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፣  ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበረሰብ አባለት በነገው እለት የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጣቸው ሲሆን ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ የፖለቲካ አጋሮቻቸው ከፍርድ ቤቱ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። በእነ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ እና አቶ ናትናኤል መኮንን፣ የመኢዴፓ አመራር ...

Read More »

አሜሪካ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለኢትዮጵያ ልትለግስ ነው

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብ ልማት ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት አቶ አህመድ ሼዲ እና የአሜሪካ አለማቀፍ የልማት ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ሚ/ር ቶማስ ስታል  ስምምነቱን ፈርመዋል። ገንዘቡ ለትምህርት ለጤናና ለመልካም አስተዳዳር ግንባታ እንደሚውል የልማት ድርጅቱ ዳይሬክተር ተናግረዋል። አሜሪካ ይህን ያክል ገንዘብ ለኢትዮጵያ ስትለግስ የአሁኑ የመጀመሪያ ነው። ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት አያያዙዋ በስቴት ዲፓርትመንት ሳይቀር ክፉኛ ብትተችም፣ አሜሪካ መንግስት አሁንም ለኢትዮጵያ ...

Read More »

የሱዳን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው።

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተማሪዎቹ ተቃውሞውን ያነሱት መንግስት በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የሚወስደውን እርምጃ ተከትሎ ነው። የአገሪቱ ተቃዋሚዎች ህዝቡ በፕሬዚዳንት አልበሽር መንግስት ላይ እንዲነሳ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የበሽር መንግስት በተማሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ የአሜሪካ መንግስት አውግዟል። አመጹ በካርቱም ብቻ ሳይሆን ከካርቱም ውጭ ባሉ ዋና ዋና ከተሞችም ተሸጋግሯል። ተቃውሞውን ለመዘገብ ወደ ዩኒቨርስቲዎች የተጓዙ የውጭ አገር ጋዜጠኞችም በጸጥታ ...

Read More »

ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ በአንድ ቀበሌ ከ200 በላይ አርሶአደሮች ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በማዳበሪያ እዳ የተያዙ ከ200 በላይ አርሶአደሮች መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ገልጧል። ገዢው ፓርቲ ለገቢ ማሰባሰቢያ በሚል በግዴታና በውዴታ ማዳበሪያ በእዳ ሲያከፋፍል ከቆየ በሁዋላ ካለፉት 2 ወራት ጀምሮ አርሶአደሮቹ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ትእዛዝ ወርዶባቸዋል። እዳቸውን ለመክፈል አቅሙ ያጠራቸው አርሶአደሮች በገፍ እየተያዙ በእስር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል። አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የጠየቀ ሰው ለኢሳት እንደገለጠው በእስር ላይ ከሚገኙት አርሶአደሮች መካከል ...

Read More »