Author Archives: Central

ሂውመን ራይትስ ወች በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰውን በደል አወገዘ

(Aug. 15) የኢትዮጵያ መንግስት አፍሶ ያሰራቸውን 17 የሙስሊም መሀበረሰብ መሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ። የታሰሩ ሙስሊሞች ላይ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ መፈጸሙን አወገዘ። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሲካሄድ በነበረው የሙስሊሙ ማሀበረሰብ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ሲያስተባብሩ የነበሩ እኒህ 17 መሪዎች ጠበቃ የማናገር መብታቸው ታግዶ ከሶስት ሳምንታት በላይ መታሰራቸው ኢፍትሀዊ መሆኑን ሂውማን ራይት ዎች በመግለጫው አስታውቋል። ከጁላይ 13 ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ ...

Read More »

በአዋሳ ጨምበላላ በዓል ላይ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰማ

(Aug. 15) በአዋሳ ከተማ፤ ፊቼ ጫምባላላ በመባል የሚታወቀውን የሲዳማ ብሄረሰብ አዲስ አመት ለማክበር የወጡ፤ ከአምስ መቶ ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን መንግስትን የተቃወመ ትእይንት አደረጉ። በትላንትናው እለት በተጀመረው በዚህ በአል ላይ ህዝቡ ከዚህ ቀደም የተነሳውን የሲዳማ ዞን የክልል ጥያቄ ዳግም አስተጋብቷል። ኢህአዴግንና የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ ችፈራው ሽጉጤንም በጽኑ አውግዟል። ህዝቡ በጭፈራው መሀል ፍትህና ነጸነት በመጠየቅ፤ ይህን የነፈገውን የኢህአዴግ መንግስት፤ “ኢህአዴግ ሰለቸን፤ በቃችሁን፤” ...

Read More »

የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ፤ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀረበ

(Aug. 15) የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለን በ3 የተለያዩ ክሶች ተከሶ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ። ተመስገን ደሳለኝ የክስ መጥሪያ ሳይደርሰው መከሰሱን የሰማው በሬድዮ መሆኑን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የገለጸ ሲሆን፤ ይህም የደርግ ግዜውን አፈሳና እስራት አስታውሶኛል ብሏል። በከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረበው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ “ችሎት አልተሟላም ተብሎ” ክሱ ሀሙስ ነሃሴ 17 ቀን እንዲታይ ቀጠሮ ...

Read More »

ሲ ኤን ኤን በመለስ ዜናዊ መሰወር ፍርሀት መንገሱን ዘገበ

(Aug. 15) የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መሰወር የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል። ሲ ኤን ኤን ዘወትር ከመድረክ የማይጠፉት አቶ መለስ ዜናዊ፤ ከሁለት ወራት በላይ የት እንዳሉ አይታወቅም ሲል ዘግቧል። መንግስት በሚያሰራጨው የተቆጠበ መረጃ መላምቶች እየሰፉ መቀጠላቸውን፤ በሀገሪቱ ፍርሀት መንገሱንም ሲ ኤን ኤን ዘርዝሯል። “ስለ ጠ/ሚ/ሩ ሁኔታ ለማውራት ፍርሀት አለ። ይህ በሕግ ሳይሆን በሀይል የሚመራ ሀገር ነው።” በማለት ለሲ ኤን ...

Read More »

አቶ ስብሐት ነጋ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ መመለስ መናገራቸው ስህተት እንደነበረ ለኢሳት ገለጡ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ከሶስት ሳምንት በፊት ያስታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ አባባላቸው ስህተት መሆኑን ለኢሳት ገለጡ። አቶ በረከት ስምኦን ከአዲሱ አመት በፊት አቶ መለስ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ይህንን የማረጋገጥም ሆነ የማስተባበል መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል። አንጋፋው የህወሀት ታጋይ አቶ ስብሀት ነጋ ለስርአቱ ቅርበት ያላቸው ...

Read More »

አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨመረ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግብርና ሚኒስቴር እና የውጭ ለጋሾች ትናንት በጋራ ያቀረቡት ሰነድ እንደሚያሳየው ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን 200 ሺ ወደ 3 ሚሊዮን 700 ሺ ከፍ ብሎአል። ለእነዚህ ተረጅዎች ከ189 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ3 ቢሊዮን 4 መቶ ሚሊዮን በላይ ብር እንደሚያስፈልግ ታውቛል። 41 በመቶ የሚሆኑት ተረጅዎች ...

Read More »

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በግብጹ ባለስልጣን ንግግር ቅሬታውን ገለጸ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ዞር ሲሉ፤ ግብፆች ፦” ኢትዮጵያውያን ከጥቅማቸው በተቃራኒ ይቆማሉ” ብለው ማሰባቸው ስህተት ነው” ሲሉ አንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩ፡፡ በኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ያሉት፤ አንድ የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የዛሬ ሳምንት ፦” ከመለስ ዜናዊ በሁዋላ የሚኖረው አዲሱ የኢትኦጵያ አመራር -ከአዲሶቹ ...

Read More »

ኢራፓ፦”አገሪቷን ማን እንደሚመራት ባለመታወቁ በስጋት እየታመሰች ትገኛለች”አለ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥራ ላይ አለመሆናቸው ከተነገረና ከተረጋገጠ ጊዜ አንስቶ፣ ኢትዮጵያን ማን እየመራት እንደሆነ ለሕዝብ ይፋ ባለመገለጹ አገሪቱ በወሬ፣ በሐሜት፣ በፍርኀትና በሥጋት እየታመሰች ትገኛለች ሲል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ገለጸ። ኢራፓ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ   አገሪቱ በማን እየተመራች እንደሆነ  ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ እንዲነገረው አሣስቧል። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 12(1) የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት ...

Read More »

ኢነጋማ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በጥብቅ አወገዘ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-”የወቅቱ የኢትዮጵያ አስተዳደር የፍትህ ጋዜጣን  ማገዱ፤ በኢትዮጵያ ጭል ጭል ሲል የነበረው የፕሬስ ነፃነት ሙሉ ለሙሉ መዳፈኑን የሚያመለክት ነው” ሰል  ኢነጋማ ገለጸ። በስደት የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር፦“በፍትህ ጋዜጣና በአዘጋጁ ላይ እየተወሰደ  ያለው እርምጃ፤ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት መብት ጨርሶ መጥፋቱን የሚያረጋግጥ ክስተት ነው” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ፍትህ ጋዜጣ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ብቸኛ ...

Read More »

ኢሳት በባህል አምባሳደርነት የተካፈለበት የስዊዝ አፍሪካ የባህል ፌስቲቫል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየአመቱ  በስዊዘርላንድ  የመንግስት  መቀመጫ  በሆነችው  በበርን  ከተማ  የሚካሄደው ታላቁ የስዊዝ አፍሪካ ፌስቲቫል ከመቸውም  ጊዜ  በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ ተጠናቋል የኢትዮጵያ  ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ከሚዲያ አውታርነት በተጨማሪ  በባህል  አምባሳደርነት በተካፈለበት :  በስዊዝ  የሚገኙ  ኢትዮጵያውያን  በተለያዩ  የብሄር  ብሄረሰቦችን  አልባሳት ተውበውና የቀስተ ደመና አምሳል በሆነው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ አላማ አሸብርቀው የታዩበት የዘንድሮው ፌስቲቫል  ከኣፍሪካ ፌስቲቫልነትወደ ኢትዮጵያ ...

Read More »