ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል፣ ሲዳማ ዞን፣ በንታ ወረዳ ቡና አምራች ገበሬዎች ተቃውሞውን ያነሱት የቡና መሸጫ ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ሆኖአል በማለት ነው። በትናንትናው እለት ቡና አምራቾች ለቡና ግዢ የሄዱ ነጋዴዎችን በተለያዩ መሳሪያዎች በማስፈራራት ፣ ሚዛኖቻቸውን በመሰባበርና ንብረታቸውንም በመቀማት አካባቢውን ለቀው አንዲወጡ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የወረዳው ፖሊሶች ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ሞክረው ሳይሳካላቸው ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይግባኝ ወረቀቱን በእስር ቤት ሀላፊዎች ተነጠቀ
ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብር ወንጀል ተከሶ 18 ዓመታት የግፍ እስር የተፈረደበት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማቅረብ ተገኝቶ ነበር። እስክንድር ይግባኝ ለማለት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ቢሆንም፣ የይግባኙን ሰነድና ለፍርድ ቤት ሊያቀርበው ያዘጋጀውን የወረቀት ማስታወሺያዎች የቃሊቲ እስር ቤት ፖሊሶች ስለነጠቁት ሳይችል ቀርቷል። ጋዜጠኛ እስክንድር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለእስር ቤት ፖሊሶች ትእዛዝ ...
Read More »መከላከያ የባንክ ባለቤት ሊሆን ነው
፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጲያ መግስት ለ2005 የበጀት ጥቅምት አመት ከያዛችው ዋንኛ የሰራ እቅዶች መካከል ወታደራዊ ባንክ ማቋቋም መሆኑን አስታውቆል።ሪፖርተር ከአዲስ አበባ እንደዘገበው መከላኪያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ባንኩን ለማቋቋም እየሰራ ነው። በተያዘውም አመት ተጠናቆ ሰራ ይጀምራል ብሏል።የመከላኪያ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ባቀረበው የስራ ክንውንና ዕቅድ ሪፖርት ላይ ይፋ የሆነው ወታደራዊ ባንክ ግንባታ በዋነኝነት ወታደራዊ ቁልፍ ስልጣኖችን በእጁ ...
Read More »እነ አቶ በቀለ ገርባ ጥፋተኛ ተባሉ
ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዩጵያ መንግስት አሸባሪ ሲል ክስ የመሰረተባቸው የመድረክ ስራ አስፈጽሚና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውጭ ቋንቋ መምህር አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች 8 ሰወች በተከሰሱበት አሽባሪነት ክስ ጥፋተኛ ተባሉ። ከሁለት አመት በፊት የፊደራል አቃቢ ህግ አሽባሪ ሲል ክስ የመሰረተባቸው አቶ በቀ ለገርባ እና አቶ አልባማ ሌሊሳ ኦፍዴንና ኦህኮን ሽፋን በማድረግ ለኦነግ እንዲሰሩ ወጣቶችን መልምለው ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በስቃይ ላይ መሆናቸው ተነገረ
፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዜሮ አንድ ከ 2000 በላይ አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ። የክፍለ ከተማው ፖሊሶች በነቂስ ወተው ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች የፈረሱበትን ዘመቻ ነዋሪውን በማሰርና በመደብደብ ጭምር አስፈጽመዋል። በተለምዶ ሀና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ጥዋት ሶስት ግሬደር ተሰማርቶ ባደረገው የማፍረስ ዘመቻ መስኪድና ቤተክርስትያን ጭምር ፈሮሶል ተብሎል። ኢሳት ...
Read More »በደጋን ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች ታሰሩ አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ተከቧል
ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ ዞን በደጋን ወረዳ ከሳምንታት በፊት የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ አካባቢው ከትናንትጀምሮ እንደገና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በሁዋላ ከ100 በላይ ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል። ወጣቶችም አካባቢውን ለቀው ወደ ወደ ገጠር በብዛት መሰሰደዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል በከተማዋ ውስጥ በእድሜ አዛውንት የሆኑት የ90 አመቱ አቶ እንድሪስ ከማል ይገኙበታል። ኢሳት ...
Read More »ተቃዋሚዎች በዘንድሮ ምርጫ መዳከም አሳይተዋል
ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የአካባቢና የአዲስአበባ ከተማ ምርጫ ተቃዋሚዎች እስካሁን ምንም ዓይነት ዝግጅት አለማድረጋቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ ምርጫ ቦርድ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ምርጫው የሚያካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በምርጫው ዕጩዎቻቸውን ለማስመዝገብ የቀራቸው ጊዜ ሶስት ወራት ብቻ ነው፡፡ ይህም ሆኖ እስካሁን ...
Read More »የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው
ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሀማድ ቢን ጃቦር አልታህኒ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል ። አቶ መለስ ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የ ካታር መንግስት የኤርትራን መንግስትና የመንግስትን ተቃዋሚዎች እንዲሁም አልሸባብን ይረዳል በሚል የዲፕሎማሲው ግንኙነት እንዲቋረጥ አድርገው ነበር። በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውዝግብ ...
Read More »በውጭ አገር የሚገኘው ሲኖዶስ አዲስ ፓትሪያርክ ለመሾም የሚደረገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት አይኖረውም አለ
ጥቅምት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሲኖዶሱ ” በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ 34ኛው መደበኛ ጉባኤ መግለጫ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ የቤተክርስቲያንን ሰላምና አንድነት፣ በተለይም ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ መንበራቸው ስለሚመለሱበት ሁኔታ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው መነጋገራቸውን ጠቅሷል። በመግለጫው” በአዲስ አበባ ያሉት አባቶች ቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ ...
Read More »የለገጣፎ ለገዳዲ ነዋሪዎች ትናንት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የጦፈ ክርክር አደረጉ
ጥቅምት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኘው የገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ነዋሪዎች ትናንት ባካሄዱት ስብሰባ በአካባቢያቸው ስለሚፈጸመው ሙስና ከአካባቢውና ከክልል ባለስልጣናቱ ጋር ክርክር አካሂደዋል። ከ1000 በላይ ተሰብሰባዎች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ህብረተሰቡ በአካባቢው ስለሚካሄደው የመሬት ዝርፊያ ብሶቱን እያወጣ አሰምቷል። በስብሰባው ላይ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ” 90 በመቶ የሚሆነው የአካባቢው ህዝብ ካርታ ሳይሰጠው፣ ከ 18 ሺ የሚደረስ ካርታ ...
Read More »