የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አከባበር ነቀፉ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢሳት ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦች በአል አከባበር  የይምሰል ነው በማለት ተችተዋል።  የተረፈች ልጅ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስድስት ኪሎ ግቢ ተማሪ እንደተናገረው ኢትዮጵያ በጥቂቶች የምትገዛ ፣ አብዛኛው ህዝብ የበይ ተመልካች የሆነባት አገር ናት ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብሄሮች መብት አለመከበሩ በግልጽ የሚታየው በስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ...

Read More »

በባህርዳር በመቶዎች የሚቆጠሩ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ተይዘው አንድ ካምፕ ውስጥ ታጎሩ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ለኢሳት ከባህርዳር የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር ይለምኑ የነበሩ ሰዎች ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ተሰብስበው ጅንአድ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ እንዲጠራቀሙ ተደርጓል። ጎስቋሎቹ የተያዙት በባህርዳር የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል  ውበት ይቀንሳሉ፣  ለከተማዋም መጠፎ ምስል ይፈጥራሉ  በሚል ምክንያት ነው። እንደ ፈለጉ የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲታጎሩ የተደረጉት ጎስቋሎች፣ በአሁኑ ጊዜ በቂ ምግብና ...

Read More »

በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸው

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር  ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል።  መንግስት ...

Read More »

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎችን ጉዳይ ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- 16ኛው ወንጀል ችሎት የኮሚቴ አባላቱ ጠበቆች ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ ነበረ ቢሆንም፣ ቀጠሮውን ለታህሳስ 8 ፣ 2005 ኣም ለማሸጋጋር ወስኗል። ዳኞች ለጠበቆችና አቃቢ ህጎች፣ የተከሳሾች ቁጥር ብዙ በመሆኑ ሁሉንም ተመልክተን ለመወሰን አልቻልንም በማለት እንደነገሯቸው ታውቋል። ዳኞቹ እስረኞቹ ችሎት እንዳይቀረቡ የተደረገው ለደህንነታቸው ሲባል ነው በማለት መናገራቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ...

Read More »

ጠ/ሚ/ር ሀይለማሪያም ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በማናቸውም መድረክ አስመራ ጭምር ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በማናቸውም መድረክ አስመራ ጭምር ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ:: አቶ ሀይለማሪያም ይህንን የገለጡት ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው:: በዛሬው እለት በተሰራጨው የአቶ ሀይለማሪያም ቃለምልልስ አስመራ ሄዶ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የመነጋገር ፍላጎት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፍላጎት ጭምር እንደነበር ገልጠዋል:: አቶ መለስ ከአቶ ...

Read More »

የዩናይትድ ስቴት ፓርላማ አመታዊው የዲቪ ሎተሪ እጣ እንዲቆም አርብ እለት ባካሄደው ስብሰባ ገለጠ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ሴኔትና በፕሬዚዳንቱ ካልጸደቀ በስተቀር ተግባራዊ እንደማይሆን ታውቆል:: በሪፐብሊካን አነሳሽነት ለፓርላማ እንደቀረበ በተገለጠው የዲቪ ሎተሪ ይቁም ጥያቄ ከ245 የፓርላማ አባል የ 139ኙን ድምጽ በማግኘት ነው ያለፈው:: በሀገሪቱ ስደተኞችን ለመግታት በሚለው የሪፐብሊካን አንዱ ስትራቴጂ እንደሆነ በሚነገርለት የዲቪሎተሪ ይቁም ሀሳብ በተለዋጭ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንጂነሪን ፡ በቴክኖሎጂና በሳይንስ ለተማሩ የውጭ ሰዎች ቪዛው ይሰጣል ...

Read More »

ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ደህንነቶች እንደሚመረመሩና እንደሚታሰሩ ተገለጠ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ጋምቤላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ተጉዘው የነበሩት ዶ/ር ማኝ አንግ ለኢሳት እንደገለጡት በጋምቤላ በክልሉ ፕሬዚዳንት ተጠርተው ደህንነቶች እንደሚፈልጎቸው ከተነገራቸው በሆላ ለ 2 ሰአት ያህል እንደመረመሮቸው አስታውቀዋል:: ማንኛውም የጋምቤላ ተወላጅ ወደተወለደበት ሀገር ሲሄድ ያሬድ፡ ኤፍሬምና ዳዊት በሚባሉ የመንግስት ደህንነቶች ይመረመራል፤ በጋምቤላ ከሚገኙ የተቃዋሚ መሪዎች፤ ከግምቦት ሰባትና በጋምቤላ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ...

Read More »

በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ ፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ::

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ የፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ:: የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ ገብቶል በማለት ያነሱት ተቃውሞ አመት ማስቆጠሩን ያስታወሰው የፊርማ ማሰባሰብ መግለጫ በአሰሳ አርሲና በገርባ በመንግስት ታጣቂዎች 7 ሰዎች መገደላቸውን ፡በረካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ሌሎች መሰደዳቸውን በመግለጽ ...

Read More »

በቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ዕርቅን ለመፍጠር በሚካሄደው ውይይት ላይ ለመገኘት ከአዲስ አበባ የተወከሉት አባቶች አሜሪካ ገቡ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጭ የሚገኙ አባቶችና ከሐገር ቤት የመጡት ልዑካን በትናንትናው ዕለት ዳላስ ቴክሳስ ሲደርሱ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት እንዲያመጡ የተማፅኖ ፊርማዎ እየተሰበሰበ ይገኛል። በውጭ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ መልከ ፀደቅ የሚመራው ልዑካን ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ከካናዳና አውሮፓ ትናንት ዳልስ ገብቷል። ከብፁዕ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊም የጀመሩት ሰላማዊ ትግል ከዳር እንዲደርስ በስደት ላይየኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የመምህራን የትግል አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን አስታወቀ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው በደል በሌላውህብረተሰብ ላይም እየተፈጸመ መሆኑንም ገለጸ:: የመምህራን ማህበሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀውበሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ መንግስት እያደረሰ ያለው ግድያ፡ እስራትና በደልበሌላው የህብረተሰብ ክፍልና ቡድን ላይ ሲደርስ የቆየና እየደረሰ ያለው ግፍአካል በመሆኑ በስደት ያለውን መምህራን የትግል አጋርነት ያስፈልጋል ሌላውምየህብረተሰብ ክፍል የትግሉ አጋር ሊሆን ይገባል ሲል ጥሪ አስተላልፋለሁ:: በተለያዩ ወቅቶች አንድ ላይ ሆነን ባለመነሳታችን የከሸፉትን የትግልእንቅስቃሴዎች ልናስታውስ ይገባል ያለው የመምህራን ማህበሩ መግለጫለስኬት በአንድነት ሆነን ልንነሳና ልንታገል ይገባል ብሏል:: በዘር ምንጫቸውና በቋንቋቸው ተነቅሰው ቤታቸው በብልዶዘር የፈረሰንብረታቸው የተዘረፈና ከኖሩበት ቀዬ የተባረሩ ኢትዮጵያውያኖችን ያወሳውመግለጫው በነጻ ሚድያ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው የአሸባሪነት ክስናየተወሰደው እርምጃንም በማስታወስ በገዢው ፓርቲ ያልተበደለ የህብረተሰብክፍል የለም ካለ በኋላ በጋራ ልንታገለው ይገባል ሲል አስታውቋል:: የመምህር የኔሰው ገብሬን የትግል ቆራጥነትና መስዋዕትነት በመግለጽመስዋዕትነቱ መና አልቀረም ያለው በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ መግለጫ ህዝባዊ አመጽ ደግሞ መስዋዕትነቱም ውጤቱምዘላለማዊ ነው ሲል የጋራ እንነሳ መልዕቱን አጠናቋል::

Read More »