በአዲስ አበባ የሚታየው የመጓጓዣ ችግር እንደቀጠለ ነው

ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በከተማው ውስጥ በሚታየው የትራንስፖርት ችግር ተማሪዎችም ሆነ የመንግስት ሰራተኞች በሰአቱ ትምህርትቤታቸውና  ስራ ቦታቸው ለመገኘት አልቻሉም። በተለይ ከጧቱ 1 ሰዓት ተኩል እስከ 2 ሰዓት ተኩል እንዲሁም ከ ሰአት በሁዋላ ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በአራት ኪሎ፣ ሜክሲኮ፣ ሀያሑለት፣ ፒያሳ፣ መርካቶና ቦሌ አካባቢዎች ከፍተኛ  የሆነ የትራንሰፖርት ችግር ይከሰታል። በቅርቡ ግንባታው የሚጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋት ችግሩን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቶ ሀይለማርያም ከኤርትራ ጋር ስለሚደረገው እግርኳስ ጫወታ የተናገሩትን ቆርጦ አቀረበ

ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስቱ ቴሌቪዥን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኤርትራ ጋር የእግር ኳስ ጨዋታ በአስመራ ለማካሄድ ችግር የለብንም በማለት የተናገሩት መንግስት ቀደም ብሎ ጨዋታው በገለልተኛ አገር እንዲካሄድ ከጠየቀው ጋር የሚጋጭ መሆኑን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወሳል። ኢቲቪ የአቶ ሀይለማርያምን ቃለምልልስ በአማርኛ ተርጉሞ ያቀረበ ሲሆን፣ የእግር ኳስ ጫወታውን በተመለከተ ያለውን ክፍል ቆርጦታል። ኢቲቪ ቃለምልልሱን ቆርጦ ማቅረቡ የኢሳትን ዘገባ ለማስተባበል ተብሎ ይሁን ...

Read More »

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. አባቶች ድርድር ላይ ያወዛገቡት ደብዳቤዎች እየወጡ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በዳላስ ቴክሳስ የተካሄደው ውይይት ለጊዜው ባለመስማማትና ለሌላ ውይይት ቀጠሮ ተይዞ ቢጠናቀቅም፤ የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ የውዝግቡ መነሻ የነበሩት ሰነዶች ለኢሳት ደርሰዋል። በቤተክርስቲያኒቷ አባቶች መካከል አንዱ የልዩነቱ መነሻ የሆነው የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ የጻፉት ደብዳቤ መሆኑ ታውቋል። የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ ፓትሪያርኩ እንዲነሱ ደብዳቤ መጻፋቸውን አምነው ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ መናገራቸውን ዊኪሊክስ ከሁለት አመት ...

Read More »

በጅጅጋ የሆቴል ባለቤቶች አሻበሪዎችን ታስድራላችሁ በሚል እየተቀጡ ነው

ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጅጅጋ ወኪል የሆቴል  ባለንብረቶችን አነጋግሮ እንደዘገበው   በክልሉ የተቋቋመው እና በከፍተኛ ደረጃ የሚፈራው ልዩ ሚሊሺያ የሆቴሎች ባለቤቶችን እያስገደዱ ገንዘብ ይዘርፋሉ። ሚሊሻዎቹ የሆቴል ባለቤቶችን የሚዘርፉት የኦጋዴን አማጽያንን ያለበቂ ፍተሻና ምዘገባ በሆቴላችሁ ታሳድራላችሁ ፣ በቂ የፍተሻ ሰራተኞችን አልመደባችሁም በማለት ነው። “በመጀመሪያ ሚሊሺያዎች፣ ፖሊሶችና ባለስልጣናቱ ሆቴሎች ውስጥ ገብተው ይቀመጣሉ፣ ከዚያም ይሀው መሳሪያ ይዘን ገብተናል ፣ ፍተሻችሁ ጠንካራ አይደለም ...

Read More »

በዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ኢህአዴግ ስልጠና ሊሰጥ ነው

ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት በመጪው ሳምንት በሚጀመረው በዚህ የስልጠና መርሀግብር የሁለተኛ ደረጃ ፣ የመሰናዶ፣ የኮሌጅ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይሳተፋሉ። በመርሀ ግብሩ መሰረት ከነዚሁ የትምህርት ተቋማት የሚመረጡ ቁልፍ ተማሪዎች በቅድሚያ ስልጠና ከተሰጣቸው በሁዋላ፣ እነዚሁ ሰልጣኞች ተመልሰው በመሄድ ለተቀረው ተማሪ ስልጠና ይሰጣሉ። ስልጠናው የሚቆየው ለአንድ ሳምንት ሲሆን፣ የሚሰለጥኑበት ሁኔታም በአብዛኛው ኢህአዴግ ባለፉት 8 አመታት ስላስገኛው ድሎች፣ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ወጣቶች የቃሊቲ ጉብኝት ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ተባለ

ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው እሁድ ታህሳስ 7፣ 2005 ዓም አለአግባብ የታሰሩ የሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ መሪዎችን በቃሊቲ ተገኝተው ለመጠየቅ የወጠኑት እቅድ ጥሩ ምላሽ እያገኘ መምጣቱን አዘጋጆች ገልጸዋል። ማንኛውም የህገመንግስቱን የእምነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንዳለበት የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ወደ ቃሊቲ በመሄድ ድጋፉን እንዲያደርግ እንጠይቃለን የሚል መግለጫ ካወጡ በሁዋላ ጥሪው በማህበራዊ ድረገጾች ...

Read More »

ከጅቡቲ ደረቅ ጭነት የጫኑ ከ100 በላይ መኪኖች አዋሽ አርባ ላይ ቆመዋል ተባለ

ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲሱ መልቲ ሞዳል ሲስተም መሰረት እቃዎችን ከጅቡቲ በመጫን ወደ መሀል አገር የገቡ ከ100 በላይ መኪኖች ውሳኔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ላለፉት 10 ቀናት አዋሽ አርባ ላይ መቆማቸውን  ሾፌሮች ተናግረዋል። ጭነቱ የመንግስት መሆኑን የተናገሩት ሾፌሮች በሞጆ ደረቅ ወደብና በአዲስ አበባ ደረቅ ወደብ መራገፍ ቢኖርበትም ውሳኔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ እስካሁን ሊራገፍ አልቻለም። የመኪኖቹ ባለንብረቶች ለመንግስት ባለስልጣናት ችግሩን ...

Read More »

በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌዴንና የኦህኮ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሊሊሳ ከሌሎች 7ተከሳሾች ጋር ዛሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው የ8 እና የ13 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የኦፌዴን ም/ል ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል  የሆኑት አንደኛው ተከሳሽ አቶ በቀለ ገርባ በ8 አመት ፣ ሁለተኛው ተከሳሽ  የኦህኮ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ50 ሺ ብር ዋስ እንዲያቀርብ ታዘዘ

ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ50 ሺ ብር ዋስ በማስያዝ ክሱን በውጭ ሆኖ እንዲከራከር ትእዛዝ አስተላልፎአል። ዳኛው በመዝገብ ቁጥር 123 ሺ 875 የተከሰሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ከዚህ ቀደም ለብይን ተቀጥሮ እያለ አቃቢ ህግ ክሱን በማንሳቱ የተቋረጠ ቢሆንም አቃቢ ህግ እንደገና ክሱን በመቀስቀሱ ነው ለዛሬ የተቀጠረው ብሎዋል። የአቃቢ ህግን የክስ አስተያየት ...

Read More »

ኦህዴድ በውስጥ ያለውን ክፍፍል ለማብረድ አባላቱን ሰበሰበ

ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት አቶ ሙክታር ከድር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ደረጃ ያለውን አመራር የማጠናከር፣ የማረጋጋትና የማጽዳት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ከፍተኛ ችግር በሚታይበት በምስራቅ ኦሮሚያ እና በሀረሪ ክልል የሚገኙ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ አመራሮች ፣ መምህራንና ርእሰ መምህራን፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የድርጅት አባላቶች ከህዳር 27 ጀምሮ ስብሰባ ላይ ናቸው። በሀረሪ ክልል በአሚር አብዱላሂ ...

Read More »