የዩናይትድ ስቴት የሴኔት ኣባላቶችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን ደቡብ ሱዳን ነዳጆንበኢትዮጵያ በኩል ለተቀሪው ኣለም አንድትልክ ፕሬዝዳንቱን ሳልሻ ኬርን አስጠነቀቁ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሱዳን ትሪቡንን ዋቢ ያደረገው ኦል ኣፍሪካ አንደዘገበው የመሴኔቱ ኣባላቶችየደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬርን ነዳጃቸውን ለኣለም ገበያ ለማቅረብካርቱምን መጠቀምና መጠበቅ አንደሌለባቸው ኣሳስበዋል:: ባለፈው ኣመት ግንቦት ወር የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ሚኒስቴር ስቲፍን ዶ ለዎልስትሪት ጆርናል አንደገለጹት ቢያንስ ቢያንስ የነዳጅ ምርታቸውን 10 በመቶወይም ሰላሳ አምስት ሺ በርሜል በቀን በከባድ መኪና (በቦቴ) ኢትዮጵያንናኬንያን አቆራርጠው በጅቡቲ ለአለም ገበያ ለማቅረብ አቅደዋል:: በዚህ ሳምንት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን የጎበኙት የአሜሪካ የሴኔት አባላቶች የሰሜን ሱዳን የነዳጅ ዘይት ማጎጎዝን የማስ ፉከራ ትርጉም የለውም ካሉ በሆላ ነዳጃቸውን ለአለም ገበያ ለማቅረብ ከባድ መኪናንና ኢትዮጵያን መጠቀም አለባቸው ሲሉ አስታውቀዋል::

Read More »

33ቱ ፓርቲዎች ” በህዝባዊ ንቅናቄ ትግላችንን እንቀጥላለን” አሉ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከረሙት 33ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ዛሬ ባወጡት መግለጫ  ለምርጫ ቦርድና ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ ” ስለምርጫ ተሳትፎ ማሰብ ‘ ተጨፈኑ ላሞኛችሁን’ መቀበል በመሆኑ በጋራ ይዘን ለተነሳነው ጥያቄ ምርጫ ቦርድም ሆነ ገዢው ፓርቲ ተገደው እንዲሰሙ ለማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠርና በማስተባበር የተባበረና የተቀናጀ ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል። ፓርቲዎቹ ” ጥያቄያችን ባልተሟሉበት እውነታ ...

Read More »

አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የቻይና አምባሳደር ስዩም መስፍን ከሲሲቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ማእድናትን በምታወጣበት ጊዜ የአካባቢ ውድመት ታደርሳለች እየተባለ በአፍሪካውያንና በምእራባዊያን ዜጎች የሚደርስባትን ወቀሳ መከላከል አያስፈልጋትም ብለዋል። አምባሳደሩ ይህን መልስ የሰጡት የሲሲቲ ጋዜጠኛ ” ብዙውን ጊዜ አገራችን በሌሎች አገሮች ማእድናትን ስታወጣ የአካባቢውን ህዝቦች ታፈናቅላለች፣ በአካባቢውም ላይ ውድመት ታደርሳለች ...

Read More »

20 የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም እንደታሰሩ ነው

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በቅርቡ በድሬዳዋ ከምግብ ጋር በተያያዘ ተነስቶ በነበረው ግጭት ታስረው ከነበሩት መካከል 300 የሚሆኑት ሲፈቱ አሁንም 20 ተማሪዎች ታስረዋል። የዩኒቨርስቲው ምንጮች እንደገለጡት የፌደራል ፖሊስ አባላት በጊዜው በተማሪዎች ላይ ካደረሱት ከፍተኛ ድብደባ በተጨማሪ የተማሪዎችን ሞባይሎች ሳይቀር መወሰዳቸው ታውቋል። በእለቱ በተፈጠረው ችግር ግምቱ ከ150 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወድሟል። የግጭቱ መንስኤ ከምግብ ...

Read More »

በመከላከያ ሰራዊትና በሱሪዎች መካከል የተካሄደው ግጭት ቀጥሎ 3 ሱሪዎች መገደላቸው ታወቀ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በሱሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተነሳ ግጭት 3 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በግጭቱ በርካታ የሱሪ ከብቶች መገደላቸውን ለማወቅ  ተችሎአል። ባለፈው ቅዳሜ በአካባቢው ግጭት ተነስቶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

Read More »

በአዲስ አበባ የባዶ መሬትና የንግድ ቤቶች ሽያጭ ጣራ ነካ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ በመንግስት የሚቀርቡ የቤት መስሪያ ቦታና የንግድ ሱቆች ሽያጭ ከግዜ ወደ ግዜ በአስደንጋጭ መልኩ ዋጋቸው እየተሰቀለ መምጣቱን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ የአዲስአበባ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በልደታ ክፍለከተማ የተሰሩ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ጋር ተያይዞ የሚገኙ 150 የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለመሸጥ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ለአንድ ካሬሜትር እስከ ብር 56 ሺ164 ከ11 ሳንቲም ...

Read More »

ምርጫ ቦርድ 33ቱን ፓርቲዎች ጨምሮ ምልክት ያልወሰዱ በምርጫው እንደማይሳተፉ ገለጸ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምርጫ ቦርድ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀርበው የምርጫ ምልክቶቻቸውን ያልወሰዱ ፓርቲዎች በሚያዝያው ምርጫ መሳተፍ እንደማይችሉ በይፋ አስታወቀ፡፡ ከ33ቱ ፓርቲዎች መካከል የአንዱ  የአመራር አባል የምርጫ ቦርድ እርምጃ 33ቱ ፓርቲዎች ከምርጫው ወጥተናል ከማለታቸው በፊት “አባረናቸዋል” ለማለት የተወሰደ ስልታዊ እርምጃ ነው በሚል አጣጥለውታል፡፡ ቦርዱ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች በማዕከል በቦርዱ ጽ/ቤት ተገኝተው የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የሚወስዱበት ጊዜ ህዳር ...

Read More »

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የውሃ ያለህ ይላሉ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ውሀ እጥረት ማጋጠሙን ዘጋቢያችን ገልጿል። በስድስት ኪሎ፣  መነን፣ ፈረንሳይ፣ ጃን ሜዳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ሰሜን ማዘጋጃ እና በተለያዩ የሰሜን አዲስ አበባ  የሚገኙ ሰፈሮች ውሀ ለማግኘት ውሀ ያለባቸውን አካባቢዎች ማሰስ ግድ ብሎቸአዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች ውሀ ለሳምንታት የማይመጣ ሲሆን፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሳምንት አንድ ጊዜ ጥሩ ከተባለም በሳምንት ሁለት ጊዜ ያገኛሉ። ...

Read More »

ሰፈር ያሸበረ ዶሮ በፍርድ ቤት ሞት ተወሰነበት

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከጽዮን ሆቴል ጀርባ በሚገኘው መደዴ ሰፈር ውስጥ ነዋሪውን   ያመሰ ዶሮ፤ በፍርድ ቤት ሞት ተፈረደበት። ሸገር ራዲዮ ዶሮውን << አሸባሪ>> ብሎታል። በጽዮን ሆቴል ጀርባ በሚገኘው መደዴ ሰፈር ወጪ ወራጁን፣አላፊ አግዳሚውን እየደበደበ ያስቸገረ ጉልበተኛ አለ የሚል ጥቆማ በደረሳቸው መሰረት ወደ ስፍራው ማቅናቸውን ነው የሸገር ጋዜጠኞች የሚናገሩት። ይህን ጉልበተኛ የደፈረችውም፤ ሰናይት የምትባል የሰፈሩ ሴት ...

Read More »

በሁስተን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል ተንበሸበሹ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት እሁድ ሁስተን/አሜሪካ ላይ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶቹም ሆነ በሴቶቹ ምድብ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ የአሸናፊነትን ድል መቀዳጀታቸው ታወቀ። በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት በዙ ወርቁ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ በመግባት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሲሆን፣ አትሌት ተፈሪ ባልቻ 2፡12፡50 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ፣  ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሞላ ሰለሞን ደግሞ 2:14:37 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ...

Read More »