በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንቱን የሚተካ ሰው ጠፍቷል ተባለ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ከ3 አመት በፊት የተመረጡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ከተመረጡበት ማግስት ጀምሮ በህመም ምክንያት በስራቸው ላይ ለመገኘት ባይችሉም እርሳቸውን ለመተካት በኦህዴድ ባለስልጣናት መካከል ስምምነት በምጥፋቱ ተተኪ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ አልተቻለም።   አቶ አለማየሁ አቶምሳ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በሁዋላ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት በምግብ መመረዝ ሳቢያ በተነሳ ችግር እስካሁን ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ በእስልምና እምነት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወም ገለጠ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የተደነገጉትን አንቀጾችና የእምነት ነጻነቶችን በመታስ ባለፈው አንድ አመት በእስልምና እመነት ተከታዮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ችግር ፈጥሯል ብሎአል። ፓርቲው አያይዞም የኢህአዴግ መንግስት  የሙስሊሞች ተቃውሞ ከሽብር ጋር ይያያዛል በማለት ቢገልጽም እስካሁን በታየው እንቅስቃሴ ጉዳዩ ከሽብር ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የሚታይ ምንም ነገር የለም ብሎአል። ከዚያ ይልቅ በሚያስደንቅና ጥንቃቄ በተሞላበት ...

Read More »

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ባለው የስኳር ፕሮጀክት ዙሪያ ቅሬታቸውን ገለጹ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም አቶ አባይ ጸሐየ ወደ አካባቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ማነጋገራቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች በፕሮጀክቱ ደስታቸውን እንደገለጡ ተደርጎ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን የቀረበው ትክክል አይደለም። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የጅንካ ከተማ ነዋሪ እንደገለጡት “አቶ አባይ ጸሀየ ነዋሪዎች ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ የተገባላቸው ቃል ባለመከበሩ ተቃውሞ አስነስተዋል በሚል ምክንያት” ወደ አካባቢው ...

Read More »

የአሜሪካ ፌደራል በረራ መስሪያ ቤት በቦይንግ ድሪም ላይነር 787 አይሮፕላን ላይ መርምራ ሊያደርግ ነው

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል መስሪያ ቤቱ ዋና ሃላፊ ሚሸል ሁሬታ  አንዳስታወቁት በአውሮፕላኑ ላይ በደረሰው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የአውሮፕላኑን ዲዛይና ኣመራረቱ ምርመራ ይደረግበታል። አውሮፕላኑ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የጃፓን ኣየር መንገድ ቦስተን ላይ ከቶኪዮ ተመልሶ በሚያርፍበት ሰአት እሳት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ባለፈው አርብ የጃፓን   ኦል ኒፖን አየር መንገድ ሪፖርት አንዳደረገው በሚበርበት ሰኦት በፓይለቱ በኩል ያለው መስኮት በመሰንጠቁ የመመለሻ በረራውን ...

Read More »

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ልትሆን እንደምትችል ተጠቆመ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው    የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የህብረቱ ሊቀ-መንበር ለማድረግ ኢትዮጵያ  ቀደም ካለ ጊዚ ጀምሮ ጥረት ስታደርግ መቆየቷ ተገልጿል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ኢታዮጵያ በመጪው ሳምንት 20ኛውን የ አፍሪካ ጉባኤ ታስተናግዳለች። ከህብረቱ 50ኛ ዓመት የምስረታ በ ዓል ጋት ተጣምሮ ይካሄዳል በተባለው በዚህ ጉባኤ ላይ፤የሁለቱ ሱዳኖች ...

Read More »

ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልጸዋል:: መንግስትም አቡነ መርቆሪዎስ መንበራቸው ላይ ተመልሰው ማየት እንደማይፈልግ በአቶ አባይ ጸሀዬ በኩል ግልጽ አቆሙን ያንጸባረቀ በመሆኑ የዕርቁ ጉዳይ ፍጻሜ ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሎል:: በውጭ የሚገኙ አባቶች በዛሬው እለት በሎስ አንጀለስ በጀመሩት ...

Read More »

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ:: በተለይ የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ  ሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ:: ባለፈው አርብ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ሪፓርት እንዳመለከተው በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሂደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ሪፓርቱ አመልክቶል:: የሀገሪቱን የሙስና መጠን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያጠና የቆየው የአለም ባንክ በተለይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ...

Read More »

በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6 ከመቶ ደኖን አታለች:: በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል:: ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና ከእንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቶል:: ...

Read More »

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ማህበሩን ለሚቀጥለው አንድ አመት የሚመሩ 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡን አስታወቀ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህ መሰረት ማህበሩ ከተቆቆመበት ጀምሮ ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት በመሩት በዶ/ር ሼክስፔር ፈይሳ ምትክ አቶ አበበ ሀይሉ ም/ፕሬዚዳንት ደግሞ ዶ/ር ሰለሞን ረታ አድርጎ ሠይሞል:: በተዋረድ በዋና ጸሀፊነት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በፋይናንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንትና በመድረክ አስተባባሪነት በቀድሞ የስራ አስፈጻሚዎች ምትክ አዲስ ተመርጦል:: የቀድሞ የማህበሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ለአዲሶቹ ተመራጮች የስራና የንብረት ርክክብ የፈጸሙ መሆኑን የገለጠው የማህበሩ መግለጫ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል:: ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የ እስርፍርድ ወስነውበታል:: በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎችእንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበትተወስኖባቸዋል::   የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለውየሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙንማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል:: በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነውይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደሱማሊያ ዳግም መዝመቶንም አስታውሷል::

Read More »