ፍረደም ሐውስ የ 2013 ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት ናት አለ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአለም ላይ ያሉ አገሮችን ነጻነት ( ፍሪደም) በማወዳደር ሪፖርቱን የሚያወጣው አለማቀፋዊ እውቅና ያለው ፍሪደም ሀውስ የ2013 ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጠው  ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት አገር ናት ብሎአታል። ፍሪደም ሐውስ የአለም አገራትን ነጻነት የሰፈነባቸው ከፊል ነጻነት ያለባቸውና ነጻነት የሌለባቸው አገራት በማለት በሶስት ከፍሎ የተመለከተ ሲሆን ፣ ነጻነት የሌለባቸው አገራት ተብለው የተፈረጁት መሰረታዊ የሆኑት የፖለቲካ ...

Read More »

በቦረና ዞን ህዝቡ ለሚሊሻ ማደራጃ ገንዘብ እንዲያወጣ እየተገደደ ነው

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መንግስት የአካባቢ ሚሊሻ ለማቋቋም በሚል ምክንያት እያንዳንዱ ዞኑ ነዋሪ 70 ብር በነፍስ ወከፍ እንዲከፍል አዟል። የአካባቢው ነዋሪዎች ” እኛን መልሶ ለሚበድለን ሚሊሺያ እንዴት ገንዘብ እናዋጣለን” በሚል ተቃውሞውን በማሰማቱ እስካሁን ድረስ፣ በቂ መዋጮ ሊዋጣ እንዳልቻለ ታውቋል። መንግስት በዞኑ እየተባባሰ የመጣውን ከብሄር ጋር በተያያዘ የሚነሳውን  ግጭት ...

Read More »

መንግስት በአገሪቱ በቂ ምርት አለ ቢልም ህዝቡ ግን ሸቀጦች ከገበያ እየጠፉ ነው ይላል

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ውስጥ የመሰረታዊ እቃዎች እጥረት በተለያዩ አካባቢዎች መታየቱን ተከትሎ 13 በመቶ የደረሰው ዋጋ ግሽበት ተመልሶ ያሻቅባል የሚል ስጋት ሰፍኗል። በተለይም በአገሪቱ የስንዴ፣ የዘይት እና ስኳር  እጥረት በስፋት መታየቱ፣ ህዝቡን ስጋት ላይ እንዲወድቅ አድርገውታል። ዳቦ ቤቶች በቂ የሆነ ስንዴ ለማግኘት ባለመቻላቸው በርካታ ዳቦ ቤቶች ዳቦ ማምረት ሊያቆሙ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። መንግስት ከዚህ ...

Read More »

መንግስት እግር ኳሱን ፖለቲካዊ መልክ ለማስያዝ ያሰበውን እቅድ እንዲያቆም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጠየቁ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ31 ዓመት በሁዋላ   የተገኘውን የስፖርት ውጤት በ አገር ቤት ውስጥ ለፖለቲካ ሲጠቀምበት የነበረው ገዥው ፓርቲ ፤በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው  29ኛው  የ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተመሣሳይ  ፖለቲካዊ  ቅስቀሳ  ለማድረግ ማቀዱ ኢትዮጵያኑን አስቆጥቷል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስተባባሪዎች  ፤እንደሚባለው መንግስት ፦<<ባለ ራዕዩ መሪ >>የሚል ጽሁፍ የተፃፈበትንና የአቶ መለስ ፎቶ ያለበትን ቲ-ሸርቲ ተጫዋቾቹም ሆነ ደጋፊዎቹ ...

Read More »

የከተራ በአል ዛሬ በኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ እየተከበረ ነው

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመላ አገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች እየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን ቀን ለማሰብ የከተራ በአልን በድምቀት እያከበሩ ነው። በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ ታቦታት ከእየ አብያተክርስቲያናቱ ተነስተው በምእመናን ፣ ቀሳውስት እና ዘማሪያን ታጅበው ባህረጥምቀቱ ወደ ሚገኝበት ጃን ሜዳ አቅንተዋል። በአሉ በድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል አንዱ በሆነው ጎንደርም እንዲሁ ታቦታቱ ዛሬ ወደ ማደሪያቸው አቅንተዋል። ለ3ኛ ጊዜ ...

Read More »

በውጪ ያለው ሲኖዶስ በአገር ውስጥ የሚደረግን የፓትርያርክ ምርጫ አወገዘ

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እርቀ-ሰላሙ ያልተሳካውም ሆነ የፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው የመመለስ ጉዳይ ተቀባይነት ያላገኘው ቤተ-ክርስቲያንን ለማጥፋት ቆርጦ በተነሳው ኢህአዴግ የተባለ ሀይል ምክንያት ነው ሲል በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ አስታውቋል። “ ለ እግዚአብሔር ተገዙ፤ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ”በሚል ርዕስ በስደት ያለው ሲኖዶስ ባወጣው ባለ 7 ገጽ መግለጫ ላይ፤ አራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ በከፍተኛ ባለስልጣናትና ትዕዛዝ በወታደሮች ተገደው እንዴት ከቦታቸው ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድ ነን አንከፋፈልም አሉ

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “አንድነን አንከፋፈልም” በማለት የሰደቀና የአንድነት ፕሮግራም አዘጋጅተው ውለዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተካሄደው የሰደቃና  የአንድነት ስነስርአት ላይ ተካፍለዋል። ድርጊቱ ገዢው ፓርቲ ሙስሊሞችን ከሁለት ለመክፈል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመቃም የታለመ መሆኑን በስነስርአቱ ላይ የተካፈሉ ሙስሊሞች ገልጸዋል። ተመሳሳይ ዝግጅቶች በሻሸመኔ፣ በጅማ እና በመቱ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል። ...

Read More »

ኢትዮጵያ፤ የአፍሪካ ህብረትን ፕሮቶኮል ጥሳለች ተባለ

ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው 50ኛው የአፍሪካ ህ ብረት ስብሰባ ኢትዮጵያ የሊቀ-መንበርነቱን ቦታ እንደምትረከብ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ በህብረቱ አገራት ዘንድ ጥ ያቄ ማስነሳቱ ተዘገበ። የደቡብ አፍሪካ የውጪ ፖሊሲ ኢኒሺየቲቭ (ሳፍፒ) እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበርነቱን ቦታ ከቤኒን እንደሚረከቡ በ ኢትዮጵያ የተሰጠው መግለጫ የህብረቱን ፕሮቶኮል የጣሰ እና ጊዜውን ያልጠበቀ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ህዝብን እያነጋገረ ነው

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት አዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጠው አዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑትን ምእመናንን እያነጋገረ ነው። ሲኖዶሱ ትናንት ባወጣው መግለጫ በውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር ሲደረግ የነበረው የእርቅ ድርድር ያለውጤት በመጠናቀቁ 6ኛ ፓትሪያሪክ ለማሾም መወሰኑን አስታውቋል።   መግለጫው 4ኛው ፓትሪያርክ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ክብራቸውና ደረጃቸው ተጠብቆ በጸሎት ተወስነው እንዲኖሩ ቢሞከረም እንዲሁም ውግዘት ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እንደ ቢቢሲ ዘገባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት  አዲሱ ቦይንግ ድሪምላይነር ለጊዜው  አገልግሎት እንዳይሸጥ በአሜሪካ አቪየሺን ባለስልጣን ታግዷል።   በመላው ዓለም ላይ 50 የሚሆኑ ቦይንግ ድሪም ላይነር እንዳሉ ያመለከተው የዜና አውታሩ ዘገባ፤የቴክኒክ ፍተሻ እስኪደረግ ድረስ የሁሉም አገራት ቦይንግ ድሪምላይነር ፍላግሺፖች አገልግሎታቸውን እንዲያቆሙ የዩ.ኤስ ፌዴራል አቪየሺን አሳስቧል።   አዲሱ ድሪም ላይነር ነዳጅ የመትፋት፣ የኮክ ፒት ...

Read More »