ብአዴን ወሳኝ የሚባሉ ርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 21/2010) የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝ የሚባሉ ርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በዚሁም መሰረት የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ እንደሚሻሻልና የድርጅቱ ስያሜም እንደሚለወጥ ገልጿል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው ያልተለመደ መግለጫ ብአዴን የሚመራበትን ርዕዮት ሊቀይር እንደሚችል አስታውቋል። ድርጅቱ የግለሰብ መብትና የቡድን መብት ተጣጥመው እንዲከበሩ ጠይቋል። የክልል አስተዳደራዊ ወሰኖች እንደገና እንዲሻሻሉ እንደሚታገልም ነው ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው። በዚሁም ...

Read More »

አቶ አብዲ ኢሌ በተለያዩ ወንጀሎች ይጠየቃሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር አብዲ ዒሌ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች እንደሚጠየቁ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። አቶ አብዲ ዒሌ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ አስታውቋል። እሳቸውና ሌሎች ሰባት የሶማሌ ክልል የቀድሞ አመራሮችና ግለሰቦችም ያለመከሰስ መብታቸው መነሳቱም ተገልጿል። አቶ አብዲ ዒሌ በተያዙበት ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ...

Read More »

የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት ተወሰዱ

የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት ተወሰዱ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) ባለፉት 10 አመታት በሶማሊ ክልል ለደሰው የሰው እልቂት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ስደት በዋነኝነት ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። አቶ አብዲ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች እንደሚጠየቁ ታውቋል። የተለያዩ አለማቀፍ ...

Read More »

በድሬዳዋ ከተማ የተነሳውን ግጭት ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

በድሬዳዋ ከተማ የተነሳውን ግጭት ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) በድሬዳዋ ቀበሌ 09 ትናንት ነሃሴ 20 በኦሮምያና በሶማሊ ተወላጆች መካከል የተነሳው ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ግጭቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። ግጭቱ የከተማውን ህዝብ የማይወክልና አንዳንድ ግለሰቦች ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቀሰቀሱት ግጭት መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የድሬዳዋ ከተማ የስልጣን ክፍፍል ሁኔታ በከተማው ለሚታየው ...

Read More »

የኢትዮጵጣ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው

የኢትዮጵጣ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቦሌ ፣ በባህርዳርና መቀሌ የሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ ቢመቱም ፣ የበረራ አገልገሎት ግን አልተቋረጠም። የስራ ማቆም አድማ መነሻው ከደሞዝና ከተለያዩ ጥቅማጥቆሞች ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱ ለጥያቄያቸው በቂ ምላሽ አልሰጠም። የሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን አድማ በመቱ ሰራተኞች ቦታ በጡረታ የተገለሉና በተለያዩ ምክንያቶች ...

Read More »

ኤርትራ ህገመንግስት ይፋ ልታደርግ ነው

ኤርትራ ህገመንግስት ይፋ ልታደርግ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ መቀራረብ በመፈጠሩ ኤርትራ ህገ መንግስት በማርቀቅ ለህዝቡ አዳዲስ አማራጭ መንገዶችን ለማቅረብ ትሰራለች። ህዝቡ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያደርግበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንሰራለን ያሉት አቶ የማነ፣ ህዝቡ በአገሩና በመንግስት አሰራር ዙሪያ የተሻለ ተሳትፎ ይኖረዋል ብለአል። አገሪቱ በቅርቡ ህገመንግስት ማርቀቅ እንደምትጀመር የማስታወቂያ ...

Read More »

የብእዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ያለምንም ችግር መካሄዱ ተገለጸ

የብእዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ያለምንም ችግር መካሄዱ ተገለጸ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ለወራት በለውጥ ፈላጊ የብአዴን አመራሮችና የቆየውን አካሄድ ማስቀጠል በሚፈልጉ አመራሮች መካከል የተነሳው ልዩነት በድርጅቶች ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ተጽዕኖ የፈጥራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የመጀመሪያው ቀን ስብሰባ ያለ ምንም ችግር መጠናቀቁን ምንጮች ገልጸዋል። ለውጡን የሚመሩት ሃይሎች ያቀረቡዋቸው አጀንዳዎች ያለምንም ችግር መጽደቃቻውን የገለጹት ምንጮች፣ አብዛኞቹ የጸደቁት ...

Read More »

የቀድሞውን የድህንነት አዛዥ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው

የቀድሞውን የድህንነት አዛዥ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም የመስቀል አደባባይ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የቀድሞው የደህንነት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የእስር ማዘዣ መውጣቱን ተከትሎ፣ የህወሃት ባለስልጣናት ግለሰቡን በሱዳን በኩል ከአገር እንዲወጡ አድርገዋቸዋል የሚል እምነት በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ ያለ ሲሆን፣ ያሉበትን ቦታ ...

Read More »

በሞያሌ በቦረና ኦሮሞዎችና በገሪ ሶማሊዎች መካከል የተጀመረው እርቅ መጨናገፉ ተሰማ

በሞያሌ በቦረና ኦሮሞዎችና በገሪ ሶማሊዎች መካከል የተጀመረው እርቅ መጨናገፉ ተሰማ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነሐሴ 15 2010 ዓ. ም የከተማዋ ሙስሊሞች የአረፋ በዓልን ለማክበር ለስግደት የወጡበትን አጋጣቢ በመጠቀም፣ አንድ አባት ባደረጉት ጥረት የቦረና እና ገሪ ህዝብ እርስ በርስ እንዲገናኙና እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ለማድረግ መቻላቸውን ተከትሎ፣ በድርጊቱ የተደሰተው የከተማው ህዝብ በአዋጅ የተጠራ ይመስል አደባባይ በመውጣት እየተቃቀፈ ...

Read More »

የጳጉሜ ወር የአገራዊ እርቅ ወር ለማድረግ ጥሪ ቀረበ

የጳጉሜ ወር የአገራዊ እርቅ ወር ለማድረግ ጥሪ ቀረበ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአገራቸው ጉዳይ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን ፣ አገራችን የጀመረቸው በጎ ጎዳና ቀጣይነት ባለው መልኩ ውጤታማ ሆኖ ሁላችን ልናያት የምንመኛት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ህዝባችን ወደ ተሻለና ዘለቄታዊነት ወዳለው ህብረትና አንድነት እንዲመጣ የጻጉሜ ወር የእርቅ ረው እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በላኩት ደብዳቤ፣ አብያተ እምነቶች እርቅን ...

Read More »