መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉበርግ ትናንት ይዞት በወጣው አስደንጋጭ ዘገባ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው የበሰቃ ሀይቅ በመስኖ ስራዎች እና በተፈጥሮ እንቅስቃሴ ምክንያት ጨዋማነቱ በ15 እጥፍ በመጨመሩ በሰኔ ወር ዝናብ ከዘነበና ሀይቁ ወደ አዋሽ ወንዝ መፍሰስ ከጀመረ ፣ ወንዙን ለመጨረሻ ጊዜ ከጥቅም ውጭ ያደርገዋል ሲል ጠቅሷል።. ስራ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ የአፈር መሸርሸርና በመሬት የውስጥ እንቅስቃሴ ምክንያት ጨዋማነቱ ...
Read More »በአፋር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ልዩ ወረዳ መጠየቃቸውን የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ተቃወመ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዞን ሁለት ዋና ከተማ በሆነው አብአላ የሚኖሩ 15 ሺ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ራሳችንን በራሳችን ለማስተዳደር ልዩ ወረዳ ይሰጠን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ አይደለም ሲሉ የአፋር ሰብአዊ መብቶች ሃለፊ አቶ ገአስ አህመድ ገልጸዋል። አቶ ጋአስ በዱብቲ ከተማ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጆች ቢኖርም አንድም ቀን የወረዳ ጥያቄ አለማንሳታቸውን ገልጸው፣ ከመቀሌ በ45 ኪሎሜትር ...
Read More »የግራዚያኒ ሀውልት እንዲሰራ ፈቃድ የሰጡት ከንቲባ እየተመረመሩ ነው
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሮም ደቡባዊ ግዛት የምትገኘው ቲቮሊ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ኢርኮሊ ቪሊ የህዝብን ገንዘብ በአለም በወንጀለኛነቱ ለተፈረጀው ሮዶልፎ ግራዚያኒ ሀውልት ማሰሪያ በመጠቀማቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አንሳ የተባለው ድረገጽ ዘግቧል። ሀውልት እንዲቆም የተወሰነው አንድ ማንነቱ ላልታወቀ ወታደር ቢሆንም ፣ ከንቲባው ግን በኢትዮጵያ እና በሊቢያ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎችን ላካሄደው ግራዚያኒ እንዲሆን ማድረጉ ለምርመራ መጋበዙን ድረገጹ ጠቅሷል። ድረገጹ ...
Read More »የፌደራል መንግስቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ላይ ስህተት መፈጸሙን ተናገሩ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለሳምንታት የመላውን ኢትዮጵያውያን ትኩረት በመሳብ መነጋገሪያ ሆነ የቆየው በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመው መፈናቀል በተመለከተ የፌደራል መንግስቱ ከረጅም ጊዜ ዝምታ በሁዋላ ትናንት በጠቅላይ ሚኒሰትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት አቋሙን ግልጽ አድርጓል። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው መፈናቀል በሙስና በተዘፈቁ የአካባቢው ባለስልጣናት መፈጸሙን ገልጸዋል። መንግስታቸው ማጣሪያ በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል። ...
Read More »በቤቶች ጉዳይ አቶ ሀይለማርያም የሰጡት መልስ የፓርላማ አባላቱን አስቆጣ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትላንት የመንግስታቸውን የ2005 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከፓርላማ አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የ40 በ 60 የተባለው የቤቶች ልማት ፕሮጀክትን አስመልክቶ የሰጡት ምላሽ ባልተለመደ መልክ የኢህአዴግ የፓርላማ አባላትን ጉምጉምታ አስከተለ፡፡ 40 በ 60 የሚባለው የቤት ልማት ፕሮግራም ሕዝቡ በአንድ በኩል ቆጥቦ የቤት ባለቤት እንደሚሆን እየተነገረ በሌላ በኩል ...
Read More »አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ መብት አፈና አወገዘ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሪድ ላንድስ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በ53ኛው የአፍሪካ የሰዎች እና የህዝቦች መብት ጉባኤ ላይ ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፕሬስ አፈና በዝርዝር አቅርቧል። አለማቀፍ ተሸላሚውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የተለያዩ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን፣ የኢንተርኔት ስርጭት እንዳይስፋፋ መደረጉን፣ መንግስት ከህዝቡ የሚሰበስበውን ገንዘብ የተለያዩ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማፈኛነት እንደሚያውለው፣ ሽብርተኝነት በመዋጋት ስም የሚወጡት ህጎች ፕሬሱን ...
Read More »በወልድያ ከተማ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመላው አገሪቱ ከሚካሄደው የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልድያ ከተማ 10 ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአለፈው አርብ ጀምሮ መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በዛሬው እለትም እንዲሁ አንድ የሁለተኛ ደረጃ እንግሊዝኛ መምህር የሆኑት አቶ አብደላ እና የመደርሳ ትምህርት ቤት የእቃ ግምጃ ቤት ሀላፊ የሆኑ ግለሰቦች ተይዘው ታስረዋል። መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ...
Read More »የፌደራል ፖሊስ አባላት ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች ይዘው አሰሩ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ከአዲስ አበባ የተንቀሳቀሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከባህርዳር በ35 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ መርአዊ ከተማ በመሄድ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አፍነው ወስደዋል። ፖሊሶቹ ትናንት ምሽት ወደ ከተማዋ በመግባት እና የአካባቢውን ሰዎች በማስፈራራት ልጆቹን አፍነው የወሰዱዋቸው ሲሆን፣ አንድ ወጣት ክፉኛ መደብደቡን ለማረጋጥ ተችሎአል። የታሰሩት ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውም ...
Read More »ከፍተኛው ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የመከላከያ ምስክሮች ያዳምጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አቃቢ ህጎች የጊዜ ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች ታዋቂውን የሰብአዊ መብቶች ተማጓች ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ጨምሮ ሁለት ባለሙያዎችን ለመከላከያ ምስክርነት ከማቅረብ በተጨማሪ ሌሎች የቪዲዮና የኦዲዮ ማስረጃዎችንም አዘጋጅተው ነበር። ይሁን ...
Read More »ከቫት ጋር በተያያዘ በኮምቦልቻና በደሴ ከ15 በላይ ነጋዴዎች ታሰሩ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደሴ ዘጋቢ እንደገለጸው በከተማዋ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ 11 ነጋዴዎች ከቫት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሲሆን፣ በኮምቦልቻም ሶስት ነጋዴዎች ከትናንት በስቲያ ተይዘው ታስረዋል። ነጋዴዎቹ ቫት አልከፈላችሁም ተብለው መያዛቸውን የወረዳው ባለስልጣን መግለጻቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን፣ ነጋዴዎቹ በአሁኑ ጊዜ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባለስልጣናቱ ከመናገር ተቆጥበዋል።
Read More »