ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ፕሬዚዳንቱ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ሲጠይቁ ፣ የእርሳቸው ተቃዋሚዎች ደግሞ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ላወረደው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት በታህሪር አደባባይ ተገኝተዋል። ለፕሬዚዳንቱ ከስልጣን መወገድ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት ጄኔራል አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ሰሞኑን ህዝቡ ለወሰዱት እርምጃ ድጋፋቸውን እንዲሰጣቸው ተማጽነው ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ከፍልስጤሙ ...
Read More »ከ40 በላይ የቁጫ ወረዳ ሽማግሌዎች ጉዳያቸውን ለፌደራል መንግስቱ አቀረቡ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀምሌ ወር መግቢያ በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩትን ከ60 በላይ የከተማዋ ታዋቂ ሰዎችን ለማስፈታት እና ላቀረቡትም ጥያቄ መልስ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በትናንትናው እለት 40 አገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ጥያቄአቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል። ምክር ቤቱም ጥያቄውን የማየት ስልጣን ያለው የክልሉ መንግስት በመሆኑ አጥጋቢ መልስ ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚታየው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ተባብሷል
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ኃይል በፈረቃ የማዳረስ ተግባር በሚስጢር ማከናወኑን አጠናክሮ መቀጠሉን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ በተለይ በአዲስአበባ ከሰኔ ወር 2005 አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ የኤሌክትሪክ ኃይል በመቋረጥ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች የኃይል መቋረጡ በተከታታይ እስከሶስት ቀናት የሚወስድ ጭምር መሆኑ ነዋሪውን ሕዝብ ግራ የሚያጋባ ሆኗል፡፡ የኃይል መቆራረጡ እንደባንክ፣ አየር መንገድ ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ...
Read More »በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የአጭር ጊዜ ቪዛ አሳጣጥ አሰራሩ ላይ ለውጥ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2005 ጀምሮ ወደአሜሪካን ለሚጓዙ ሁሉ የቪዛ ሒደትን የሚያቃልል አዲስ አሰራር እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ ኤምባሲው ትላንት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንደጠቀሰው የአሜሪካን ኤምባሲ የቪዛ ሒደት ክፍያን ከፍለው ቀጠሮ ያስያዙ አመልካቾች ከሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በፊት ቀጠሮ እንዲይዙ በጥብቅ አሳስቧል፡ ቀጠሮአቸውም ከሐምሌ 24 ቀን 2005 በፊት ...
Read More »የዱከም ድልድይ ግንባታ ውል እንዲቋረጥ ተወሰነ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ንግድ ዕቃዎች የሚስተናገዱበት ዋና ጎዳና ላይ የዱከም ድልድይን ለመገንባት የተረከበው አክሽን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ሥራውን በውሉ መሠረት ባለማከናወኑ የኮንትራት ውሉ እንዲቋረጥ መወሰኑ ተገለጸ፡፡ ሪፖርተር ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው “ጎጊቻ” በሚባለው ወንዝ ላይ የተጀመረው የድልድይ ግንባታ በውሉ መሠረት እየተከናወነ ባለመሆኑና የግንባታው መጓተት እያስከተለ ያለውን ችግር ከግምት በማስገባት፣ ከኮንትራክተሩ ጋር የተገባው ውል እንዲቋረጥና ሥራው ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳደር ከ18 ሄክታር በላይ መሬት ማስመለሱን ገለጸ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስተዳድሩ በሊዝ ለማልማት መሬት ወስደው በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ ካላለሙ 284 አልሚዎች መሆኑን የኢህአዴግ ልሳን ሆነው ፋና ዘግቧል። ባለፉት 5አመታት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት ከህገወጥ ወራሪዎች ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ መግባቱንም መስተዳድሩ አስታውቋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ 155 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት የለማ ሲሆን፥ ከ2 ሺህ 900 ሄክታር በላይ ...
Read More »በሶሪያ ግጭት ከ100 ሺ በላይ ሰዎች ተገደሉ
ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ እንደገለጹት በሶሪያ የበሽር አላሳድን መንግስት ለመገልበጥ የተቃውሞ ትግል ከተጀመረበት ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ ከ100 ሺ ህዝብ በላይ ተገድላል። የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ባለፈው ወር ካወጣው አሀዝ ጋር ሲነጻጸር የማቾች ቁጥር በ7 ሺ ከፍ ብሎአል። ባንኪሙን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ጆን ኬሪ ጋር በመሆን ነው መግለጫውን የሰጡት። ሁለቱም ወገኖች ለሶሪያ ...
Read More »ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለተኛ ዙር መዋጮ የመንግስት ሰራተኞች ፈቃደኛ አልሆኑም ተባለ
ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አመት የወር ደሞዛችን በአመት ከፍለናል አሁን ግን ዳግመኛ ለመከፈል አቅሙ ስሌለለን እና እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ስለማንችል፣ ከእንግዲህ ወዲህ ገንዘብ ልንከፈል የምንችለው ባገኘንበት ጊዜ ብቻ ነው ” በማለት በአማራ ክልል የሚገኙ የመምህራን ማህበራት አስታውቀዋል፡፡ መንግስት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከሰራተኛው ለመቁረጥ አቅዶት የነበረ ቢሆንም ፣ በክልል ቢሮዎች ብቻ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመንግስት ...
Read More »የፓርላማው ውይይት መታፈኑን ያጋለጠው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከሥራ ተባረረ
ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ርዕስ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል። ዜናው በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ...
Read More »የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲከፈት ቅዱስ ሲኖዶሱ ቢወስንም ተግባራዊ አልሆነም ተባለ
ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተማሪዎቹ ያነሷቸውን ጥያቄዎች የተመለከቱት ፓትሪያሪኩ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በኮሌጁ ይሰጥ የነበረው የትምህርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲቀጥል እና ተመራቂ ተማሪዎችም በወቅቱ እንዲመረቁ የወሰኑ ቢሆንም ተማሪዎቹ ግን እስከትናንት ድረስ ትምህርት አለመጀመራቸውን ተማሪዎቹን አነጋግሮ ሰንደቅ ዘግቧል። የተማሪዎች መማክርት ሰብሳቢው ዲያቆን ታምርአየሁ አጥናፌ ለጋዜጣው እንደገለጸው፣ ሐሙስ እለት ውሳኔውን ሰምተው ቢሄዱም ጊቢው ውስጥ ግን የተለወጠ ነገር አልነበረም፣ ...
Read More »