ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ/ም ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡ ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ከስድስት ኪሎ እስከድላችን ...
Read More »ኢህአዴግ የመለስ ሙት አመት መታሰቢያን በልዩ ዝግጅት ሊያከብር ነው
ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት አከባበር ሥነ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ሠራተኞቹን በየደረጃው ማወያየት ጀመረ፡፡ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ከመሰልቸቱ ጋር ተያይዞ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሽፋናቸው እንዲቀንስ ተደርጎ የነበሩት የአቶ መለስ ርዕሰ ጉዳይ- ሙት ዓመታቸውን ተከትሎ እንደገና አዲስ አጀንዳ ሆኗል፡፡ የአስተዳዳሩ ምንጮች እንደገለጹት የአቶ መለስን ሙት ዓመት በአረንጓዴ የልማት ዘመቻ ...
Read More »በወልድያ ከተማ 3 ሰዎች ተገድለው ተገኙ
ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው ሁለቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተገድለው ተጥለው ሲገኑ፣ አንደኛው የተገኘው በተለየ ስፍራ ነው። ሰዎቹ በምን ምክንያት ተገድለው እንደተገኙ ለማወቅ አሳት ወደ አኳባቢው ፖሊስ በመደወል ላቀረበው ጥያቄ፣ ፖሊስ ሰዎቹ ተገድለው መገኘታቸውን አረጋግጦ፣ ስለአሟሟታቸው ምክንያት ማጣሪያ እያደረገ መሆኑና ምርመራውንም እንደጨረሰ መረጃውን ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱት ዝርዝር ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት ውስጥ የተወሰኑት ተፈቱ
ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያአዘ በቅርቡ በጋሞጎፋ ዞን በቁቻ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት በርካታ ሰዎች መካከል 13ቱ ዛሬ በዋስ የተለቀቁ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ደግሞ ለሀምሌ 25 መቀጠራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በቅርቡ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የከተማዋ አገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል ።
Read More »በኢትዮጵያ የሚገኘው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተቋማዊ ብቃት አጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ባለ ጉዳዮች በስፍራው ይገኝ ለነበረው ለኢሳት ዘጋቢ ገለጹ::
ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለጉዳዮቹ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በደርግ ጊዜ ከነበረው የቀበሌ ፍርድ ሸንጐ ማነሱንና በጥራትም በብቃትም እጅግ መውረዱን ገልጸዋል:: የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብና የንብረት ክርክሮችን የሚዳኝ ሲሆን አልፎ አልፎ የወንጀል ጉዳዮችን ይመለከታል:: ይህ ፍርድ ቤት የተሟላ የህዝብ መጸዳጃ የሌለውክመሆኑም በላይ መብራት ሲቋረጥ ጀነሬተር ባለመኖሩና የፍርድ ቤቱ የድምጽ ቀረጻ ስለሚስተጎገል ባለጉዳዮችም ለተጨማሪ ቀጠሮ ይዳረጋሉ ። ...
Read More »የአንድነት አባል የሆኑት አቶ ግርማ ወልደሰንበት አረፉ
ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ግርማ በህይወት ዘመናቸው ለሚወዷት ሀገራቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተለያዩ ሀርፎች ያገለገሉ ሲሆን ወደ ፖለቲካው በመግባትም ትልቅ ዋጋ የከፈሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ ሲል አንድነት ፓርቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል። አቶ ግርማ ወደ ተቃውሞ ጎራው ትግል የገቡት ለ1984 ዓ/ም ከፕ/ር አስራት ወልደየስ ጋር በመሆን መአህድን በመመስረት ነው። የመኢአድ አባልና የአዲስ አበባ ሰብሳቢ በሁዋላም ...
Read More »ፒያሳ የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የተቃውሞ ድምጾች አስተናግዳ ዋለች
ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፒያሳ ከሚገኘው ኑር መስጊድ አንስቶ ዙሪያውን ባሉ መንገዶች ላይ ቆሞ የረመዳንን ጁመዓ ስግደት ሲሰግድ የዋለው ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ፣ ከአንድ አመት በላይ ሲያሰማው ነበረውን ድምጻችን ይሰማ የሚለውን ተቃውሞ በከፍተኛ ድምጽ በማሰማት የፒያሳን አየር ተቆጣጥሮት ውሎአል። ድምጻችን ይሰማ፣ የተነጠቅነውን መስጂዶቻችን ለህዝቡ ይመለሱ፣ የተባረሩ ኢማሞች ይመለሱ፣ አሸባሪ አይደለንም፣ ኢማሞቻችን ይፈቱ፣ ጥያቄው ይመለስ፣ ህገ መንግስቱ ይከበር፣ መጅሊሱ ...
Read More »በአርሲ አንድ አድማ በታኝ ፖሊስ አዛዥ በጩቤ ተወግቶ ተገደለ
ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሻለቃ ማእረግ ያለው ፖሊስ አዛዥ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹ ላይ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ግድያውን ተከትሎ ፖሊስ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ከፍተኛ ፍተሻ ሲያካሂድ ውሎአል። የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም። በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከወትሮው በተለየ ቁጥር በየቦታው ፍተሻ ሲያኪዱ የታዩት የፌደራል ፖሊሶች፣ ምናልባትም ግድያውን ከሙስሊሞች ጥያቄ ጋር ሊያያይዙት እንደሚችሉ ፍንጮች መታየት መጀመራቸውን ጉዳዩን ...
Read More »ከ 27 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለ የቴሌኮሙኒኬሽን ማስፋፊያ ሥራ ለቻይና ኩባንያ ተሰጠ።
ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከስልክ ኔትወርክ ጥራት ጋር በተያያዘ በየጊዜው የሚነሳውን ቅሬታ ይፈታል የተባለ እና 1ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ 27 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ ”ሁዋዌ”ለተሰኘው የቻይና ኩባንያ ትናንት ተሰጠ። የፕሮጀክቱን ውል ስምምነት ትናንት ማምሻውን ኢትዮ ቴሌኮም እና የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ጋር ተፈራርመዋል። ፊርማውን የኢትዮ ቴሌኮም ተቀዳሚ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም አድማሴ ...
Read More »በስፔን የደረሰውን አሰቃቂ የባቡር አደጋ ተከትሎ የባቡሩ ሾፌር በቁጥጥር ስር መዋሉን ቢቢሲ ዘገበ።
ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ከተማ በሆነችው በሳንቲያጎ ደ-ኮምፖስቴላ ረቡዕ እለት በደረሰው የባቡር አደጋ 78 ሰዎች ሲሞቱ 130 ሰዎች ተጎድተዋል። ከ130ዎቹ ቁስለኞች መካከል 35 ቀላል እርዳታ ተደርጎላቸው ከሆስፒታል የወጡ ሲሆን ከበድ ያለ ጉዳት የደረሰባቸው 95 ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ። የባቡሩን ሾፌር ለአደጋው ተጠያቂ ያደረገው የስፔን ፖሊስ ፤አደጋው በሚደርስበት ጊዜ ባቡሩ ከተፈቀደው ፍጥነት ከእጥፍ በላይ ...
Read More »