ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዳር እና የታህሳስ ወራትን በሙሉ በጾም በጾሎት ምእመኑ እግዚኦታ እንዲያሰማ ቄስ አለሙ ሺጣ የኢትዩጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ጽሓፊ በአምላክ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኢትዩጵያ በአሁኑ ስዓት እየተሰተዋለ ላለው ችግር ፣በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ሐገራት እንዲሁም በአለም ለሚታየውና ለሚሰማው በደል- ሀይማኖቱ በሚጠይቀው ስርዓት እጆችን ወደ አምለክ እንድናነሳ እና እንድናለቅስ የምንገደድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡ ...
Read More »የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ በሳዑዲ አረቢያ ግፍ ከተፈፀመባቸው ዜጎች ጎን እንደሚቆም አስታወቀ።
ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሸንጎው ከፍተኛ የአመራር ምክርቤትቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱመንግስት የጸጥታ ሀይሎችእየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ እንዳጤነው ገል ል። ሸንጎው ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ ከጎናቸው እንደሚቆምምአረጋግጧል። በተመሣሳይ የ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢህአፓ) ሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሁሉ ...
Read More »መንግስት ሁኔታው በርዷል በማለት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በኩል ቢናገርም፣ ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን ግን ችግሩ መክፋቱን እየገለጹ ነው።
ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሴቶች ካምፕ ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ይነጋራሉ። ቀን በጸሀይ ማታ ደግሞ በብርድ እንድናሳልፍ እየተገደድን ነው የምትለው ሌላዋ እስረኛ ሳሚራ፣ ህጻናት እና እናቶች በምግብ እጦት እየተጎዱ ለበሽታም እየተዳረጉ ነው ትላለች። ባለፉት አራት ቀናት የወለዱ እናቶች መኖራቸውን የምትገልጸው ሳሚራ፣ የሳውዲ ፖሊሶች ወላዶችን የት እንደወሰዱዋቸው እንደማታውቅ ገልጻለች። ሀብታም የተባለቸውም እንዲሁ እርሷ በምትገኝበት ቦታ ላይ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ አርብ ለሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ለኢሳት እንደገለጸው ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍል ፣ የሰላማዊ ሰልፍ መጠየቂያ ደብዳቤውን እንደማይቀበል ቢገልጽም፣ ፓርቲው ተቃውሞውን በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ለማድረግ ወስኖ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ተባብሮ ተቃውሞ ማዘጋጀት ሲገባው፣ ፓርቲው እንዳያዘጋጅ መከልከሉ እንዳስገረመው ወጣት አሬድ ገልጿል። ኢትዮጵያውያን ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍም ...
Read More »በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የፖለቲካና ሲቪክ ተቋማት በሳውዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል አወገዙ
ህዳር ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ፣ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ካንውነስል፣ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ፣ ሂውማን ራይተስ ሊግ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም መድረክ ድርጊቱን የሚያወግዙ መግለጫዎችን ለኢሳት ልከዋል።
Read More »በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ግፍ እንደቀጠለ ነው
ህዳር ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ በሳውዲ አረብያ በተለያዩ የማጎሪያ ጣቢያዎች ታስረው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት 2 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ እንደሚናገሩት ሰዎቹ የተገደሉት ባልና ሚስቶችን ለመለያየት በተደረገ ሙከራ ላይ በተፈጠረ ግርግር ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከሳዑዲው አቻቸው ልዑል ሳውድ አል ፋይሰል በስልክ መወያየታቸውን የመንግስት የመገናኛ ...
Read More »በአዲስ አበባ ፍተሻው በአዲስ መልክ ተጀመረ
ህዳር ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ የተባለው አሸባሪ ቡድን እና በኤርትራ መንግስት እገዛ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በኢትዮጽያ ውስጥ የተለያዩ ስፍራዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ አስተማማኝ መረጃ ያለው መሆኑን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ካስታወቁ በኃላ በአዲስአበባ በመንግስት በግል ተቋማት ከወትሮው የተለየ ፍተሻ በአዲስ መልክ ተጀምሯል፡፡ ግብረኃይሉ በዚሁ ...
Read More »የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ
ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ። ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ ...
Read More »ኢህአዴግ በነገው እለት ስለጸረ ሽብር እንቅስቃሴው ሊመክር ነው
ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ለመንግስት ስልጣን አስጊ ሆኗል ባለው የሽብርተኝነት አደጋ ላይ እንደሚመክር ለማወቅ ተችሎአል። ምክር ቤቱ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል ባላቸው ግንቦት7 እና የኤርትራ መንግስት ላይ ተነጋግሮ የመፍትሄ እርምጃ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሳውዲ አረቢያ በካምፕ ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት 4 ሺ 321 ኢትዮጵያውያን ...
Read More »የአፍሪካ ጋዜጠኞች የኢህአዴግ ልማታዊ ጋዜጠኝነት አስተሳሰብ ተቹ
ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮምሽን በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የአፍሪካ ሚዲያ አመራሮች ፎረም ላይ ኢህአዴግ የሚያቀነቅነው የልማታዊ ጋዜጠኝነት ጽንሰ-ሀሳብ በአፍሪካ ጋዜጠኞች ተተችቶአል። ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ችግሮቻቸውን ፊትለፊት አውጥተው መናገር ባለመቻላቸውም ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በዚሁ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጽያ መረጋገጡን በማውሳት ፕሬሱ ግን በውስጡ የአቅም ውስንነቶች እንዳሉበት ይህን ችግር ...
Read More »