ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንግሊዝ አገር የሚታተሙ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ በቂ ሽፋን አይሰጡም በሚል ሲተቹ ቢቆይም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በማንሳት እንግሊዝ በኢትዮጵያ የምትከተለውን ፖሊሲ የሚነቅፉ ዘገባዎችን እያወጡ ነው። ዘ ቴሌግራፍ ” እርዳታችን ለተበላሹ እጆች” በሚል ርእስ ባወጣው ሃተታ፣ በቅርቡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ...
Read More »በአዲስ አበባ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ቤት ፈላጊዎች ቢኖሩም ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ ደካማ ነው ተባለ
ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የመኖሪያ ቤቶችን እጥረትን ለመፍታት ዳግም በተደረገው ምዝገባ ከ993 ሺ በላይ ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውንና ይህን የቤት ፍላጎት ለማርካት በመንግስት በኩል እየተካሄዱ ያሉ ግንባታዎች አፈጻጸም ደካማ መሆኑን ከኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። እንደመረጃው ከሆነ የአዲስአበባ ቤቶች ግንባታ ለማየት በተካሄደው የመስክ ግምገማ የአዲስአበባ የቤቶች ግንባታ አፈጻጸም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ፡፡ በቤቶች ...
Read More »የቡርኪናፋሶ ወጣቶች ተቃውሞ ባነሱ ማግስት መሪያቸውን አባረሩ
ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ27 አመታት አገሪቱን የመሩት ብሌስ ካምፓወሬ፣ እንደገና ለመመረጥ የነበራቸውን ፍላጎት ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ መተዋቸውን ካስታወቁ በሁዋላ፣ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት በመሆን ለማገልገል መፈለጋቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጅ ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን ካልተባረሩ ተቃውሞአችንን አንተውም በማለታቸው፣ ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። ተቃውሞቸውን ሲያሰሙ የነበሩት ሁሉ የመሪውን መውረድ እንደሰሙ ደስታቸውን ገልጸዋል። የአገሪቱ ጦር የሽግግር መንግስት እንደሚያቋቁሙ ገልጸው፣ ...
Read More »መንግስት በጸጥታ ዙሪያ የቴፒን ህዝብ ሰበሰበ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል። ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል። የከተማዋ ነዋሪዎች ችግሩን የምትፈጥሩት እናንተ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ በእስር ላይ የሚገኙት አመራሮቹ ኢሰብአዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው አስታወቀ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ያክል በታሰረበት ክፍል ውስጥ እንዲጸዳዳ መደረጉን፣ ለ3 ቀናት በጨላ ክፍል ውስጥ ታስሮ የበቀል እርምጃ እንደተወሰደበት ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ደግሞ በታፈነ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉን፣ በተቅማጥና በሌሎች በሽታዎች እየተሰቃየ ቢሆንም መጸዳጃ ቤት እንዳይሄድ መከለክሉን ...
Read More »የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ንብረት በሆነው ኢትዮ ድሪም የአበባ እርሻ የሚሰሩ ሰራተኞች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምዕራብ ሸዋ በሆለታ ገነት የሚገኘው የሼክ ሙሃመድ አላሙዲጅ ንብረት በሆነው ” ኢትዮ ድሪም” ድሪም የአበባ እርሻ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው በመሆኑ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ሰራተኞች አቤቱታቸውን ለድርጅቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም መልስ ማጣታቸውን ገልጸዋል። አብዛኛው ሰራተኛ 600 ብር እንደሚከፈለው የሚናገሩት ሰራተኞች፣ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 150 ብር የቤት ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ጦርነት እንደገና አገረሸ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሪክ ማቻር የሚመራው የተቃዋሚ ቡድን ቤንቲዩና ሮቡክና የተባሉ ቦታዎችን መቆጣጠሩን መረጃዎች አመለክተዋል። ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስታረቅ በኢትዮጵያ በኩል ሲደረግ የነበረው ድርድር ውጤት አለማምጣቱን ታዛቢዎች ይናገራሉ። የሪክ ማቻር ሃይሎች ሃይላቸውን እያጠናከሩ በመሆናቸው ሌሎች ከተሞችንም ለመያዝ ተከታታይ ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ ሲሉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ገልጸዋል።
Read More »ሚኒስትሮች ባልተወራረደ የመንግስት ገንዘብ ጉዳይ ላይ ጎራ ለይተው ተከራከሩ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ አባካኝ የመንግስት ተቋማት በሚል ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት እና ለተወካዮች ም/ክር ቤት አፈ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ ሚኒስትሮችን አወዛግቧል። አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ጸጋየ በርሄ፣ የፌደራል ኦዲተሩ ሪፖርት ለህዝብ በፍጹም ሪፖርት መደረግ የለበትም ብለው ሲከራከሩ፣ የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በብሄራዊ ደረጃ ለሚደረገው ትግል ህዝቡ ተባባሪ እንዲሆን ጠየቀ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል ብሎአል። ኢህአዲግከዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መለኩ ዜጎችን ለአንድ ሀሳብ ብቻ እንዲገዙ አስገዳጅ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም አፋኝ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ እንደሚገኝ የሚገልጸው ሰማያዊ ...
Read More »የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው ምርቃት አካሄደ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል። የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ ‘’ህዝባዊ ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ ...
Read More »