የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማክበር መንግስት  ከፍተኛ ወጪ መደበ

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማክበር መንግስት እስከ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ መረጃዎች አመለከቱ። ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዝግጅቱን ከማቀድ ጀምሮ የተለያዩ ስራዎችን የሚፈጽሙት ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶች ናቸው። በኢትዮጵያ የሚከበሩ በአላትን እነዚህ ተቋማት ያለተቀናቃኝ በመውሰድ እየበለጸጉበት መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ። ኢህአዴግ ካወጣው መረሃ ግብር ለመረዳት እንደሚቻለው የዘንድሮው ...

Read More »

በሃረሪ ፕሬዚዳንቱ በፓርቲው ዋና ጸሃፊ ተደበደቡ

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብህዳር 12፣ 2007 ዓም የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሙራድ አብዱላሂ በሀረሪ ሊግ ዋና ጸሃፊና በንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃለፊ አቶ ነቢል መሃዲ ጽ/ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ተደብድበዋል። የክልሉ ባለስልጣናት ለሁለት መከፈላቸው የጸጥታ ስጋት መደቀኑንም ምንጮች ተናግረዋል። በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው አቶ ነቢል መሃዲ ከወራት በፊት በተደረገ ግምገማ ከሀረሪ ሊግ ዋና ...

Read More »

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታከሄደ ነው

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት ከማሃል አገር ሰፍረው የቆዩትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ሁመራና ሌሎች የድንበር አካባቢዎች በስፋት እየሰማራ መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገለጹ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከኤርትራ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ምክንያቱ ደግሞ ኢህአዴግን በሃይል አስገድደው ለማውረድ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ የሚለው ስጋት እያየለ በመምጣቱ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። ...

Read More »

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኢቦላ በሽታ የተጠቁ ሶስት የምዕራብ አፍሪካ አገራትን ለመደገፍ ባለሙያዎችን በቀጣይ ሳምንት ለመላክ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በበጎፈቃደኝነት ወደምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ሄደው ለመስራት ካመለከቱ ባለሙያዎች መካከል የተመረጡ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።  ሌሎች ምንጮች ደግሞ አብዛኛዎቹ ባለሙያዎች በመከላከያ የጦር ክፍሎች ውስጥ በሕክምና ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ ዶክተሮች ፣ ነርሶችና የጤና መኮንኖች ናቸው ይላሉ። ወዶ ዘማች ናቸው የተባሉትና 210 የሚደርሱት እነዚሁን ባለሙያዎች የፊታችን ሰኞ ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም ወደሶስት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ...

Read More »

ሱዳን 2 ሺ ኢትዮጵያውያንን በጉበትና በኤድስ ተጠቅተዋል በሚል ልታባርር ነው

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን የሰሜን ግዛት በምትገኘዋ ኤል ዳባ የሚኖሩ ከ2 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ተጠርንፈው ወደ ካርቱም የተላኩ ሲሆን፣ የከተማዋ ባላስልጣናት ኢትዮጵያውያኑ ሄፒታይተስ ሲ የተባለው የጉበት በሽታና የኤድስ ቫይረስ ስላለባቸው መላካቸውን ገልጸዋል። የኤል ዳባ ፖሊስ ኮሚሽነር  ኢስላም አብደል ራህማን ለሱዳን ትሪቢዩን እንደተናገሩት የግዛቱ ባለስልጣናት በውጭ አገር ዜጎች  ላይ በድንገት ባደረጉት የህክምና ምርምራ ከ15 ኢትዮጵያውያን መካከል ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ

ኀዳር ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲያዊና ለፍትሕ ፓርቲ በመጪው 5ኛ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ ሁኔታዎች ምቹ አለመሆናቸውን ቢጠቅስም “ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኖ ህዝቡ እንዲሳተፍ በመቀስቀስና በማበረታታት የተዘጋውን የዴሞክራሲ በር በምርጫ ካርዱ ሊያስከፍት እንደሚችል ከፍተኛ እምነት” እንዳለው አስታውቋል። መንግስት  የመድበለ ፓርቲን ስርዓት ለማጎልበት ምንም ዓይነት ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ከአሁኑ የተለያዩ ...

Read More »

ብርሃንና ሰላም ይሸጣል መባሉ ሰራተኛውን አስደንግጧል

ኀዳር ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሞ የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ከሰራተኛው ጋር በተፈጠረ ውዝግብ ስማቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበሩት የኢህአዴግ አባሉ አቶ አባዲ ተካ ከተሾሙ ካለፈው አመት ጀምሮ ብርሃንና ሰላም መረጋጋት ተስኖት ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ደግሞ ድርጅቱ በኪሳራ ምክንያት ይሸጣል መባሉ ሰራተኛውን አስደንግጧል። በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የሚከሰሱት አቶ ተካ “ድርጅቱ እየከሰረ መቀጠል የለበትም፣ መሸጡም ...

Read More »

ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ዲያስፖራውን ወቀሱ

ኀዳር ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በአሜሪካን ሀገር በቺካጎ ከተማ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸውን የተናገሩት  የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዲያስፖራውን ወቅሰዋል። ፕሮፌሰሩ በዛሬው ዕለት ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው ዘመን መጽሄት የጥቅምት 2007 ዕትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ «ዲያስፖራው ተስፋ የቆረጠና የተናደደ ነው፡፡ ተስፋ ስለቆረጠና ስለተናደደ ገዥው ፓርቲ የሚሰራው ...

Read More »

ከ400 በላይ ህዝብ የተፈናቀለበት መሬት በሙስና ተቸበቸበ

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 11 በተለምዶ ጋሪሳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 470 ሰዎች ቦታው ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል ተብሎ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲፈናቀሉ ከተደረገ በሁዋላ፣ በካሬ ሜትር 1 ብር ከ46 ሳንቲም መሬታቸው እንዲጨጥ ተደርጓል። ጉዳዩ የህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ከቆየ በሁዋላ ሰሞኑን ከህዝቡ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ በተደረገ ህዝባዊና የካቢኔ አባላት ስብሰባ፣ ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የዋስትና መብታቸውን ተከለከሉ

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲዎቹ ሃብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ፣ የአረና ፓርቲው መምህር አብረሃ ደስታ እና ሌሎች 6 የመብት ተሟጋቾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በአቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የተከሰሱት አስሩ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች፣ ህገመንግስቱን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም። ሁሉም እስረኞች በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወቃል። ...

Read More »