በኢትዮጵያ ሙስና እስከፊ ሁኔታ ላይ መድረሱን ከህዝብ የተሰባሰበ መረጃ አመለከተ

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከህዝብ የተሰባሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው ህዝቡ በሙስና በመማረሩ ስራ መስራት በማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሙስና የሚጠይቁ ሰዎችን ማጋለጥ ህይወትን እስከ ማስከፈል እንደሚደርስም የተሰባሰበው መረጃ ያመለክታል። አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት ሙስናን ለማጋለጥ ቢፈለግም ፣ ለሚያጋልጡ ሰዎች በቂ የሆነ የህግ ከለላ አያገኙም ሙስናን ለማጋለጥ ስንሄድ  “ጀርባቸው ይጠና ተብለን እንደገና ጉዳቱ ሙስናን በምናጋልጥ ሰዎች ላይ ” ይሆናል ...

Read More »

በጊምቢ እስር ቤት ውስጥ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ተከስቶ አንድ እስረኛ ሲሞት 60 ዎቹ በጸና መታመማቸው ተገለጸ

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ሊግ የተባለው ተቋም ለኢሳት በላከው መግለጫ በምእራብ ወለጋ በጊምቢ እስር ቤት በተከሰተው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ አቶ ያቆም ኒጋሩ የተባሉ የፖለቲካ እስረኛ አርፈዋል። ሌሎች በበሽታው የተያዙት 60 ዎቹ እስረኞችም ተመሳሳይ እጣ ሊገጥማቸው እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል። ሟቹ አቶ ያእቆብ ባለፈው ሚያዚያና ግንቦት ወር በኦሮምያ ተከስቶ ከነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በሽብርተኝነት ከተከሰሱት  ...

Read More »

የመንግስት የ11 በመቶ የእድገት ፕሮፓጋንዳ ዜጎችን ከስደት አንዳልታደጋቸው አንደነት ገለጸ

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በቅርቡ በየመን የባህር ዳርቻ ያለቁትን ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ  አደጋው ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው መኖር አለመቻላቸውንና ሰርክ የሚለፈፈው የ11 በመቶ እድገት ዜጎችን ከስደትና ከመከራ ሊታደጋቸው እንዳልቻለ የሚያሳይ ነው ብሎአል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በዜጎች ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፣   ስደትና እልቂት ከዚህ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ህዝቡ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና ለስደት የዳረገውን ...

Read More »

  የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ህዳር 30/ 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ “በሀገራችን ህዝባዊ ሥርዓት ለማምጣትና በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት ለመመስረት በምናደርገው ትግል ሁሉ የሚጠበቅብንን መስዋእትነት ለመክፈልና ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ” ነን ብሎአል። “ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ዘጠኝ ትብብር የፈጠሩ ፓርቲዎች በህዳር ወር ያወጡት መርሐ ግብር አንድ አካል የሆነውን የ24 ሰዓት የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፍ ለመተግበር ሥራ ላይ የነበሩ ...

Read More »

በደቡብ ክልል ፍተሻው ከወትሮው በተለየ መጨመሩን የአይን እማኖች ገለጹ

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ ተጓዞች ለኢሳት እንደገለጹት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ፍተሻ ጨምሯል። ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ተሳፋሪ ለኢሳት እንደገለጸው ፖሊሶቹ ተሳፋሪውን ወዴት ነው የምትሄዱት? ለምንድነው የምትሄዱት በማለት ከመጠየቅ ጀምሮ የሰዎች ኪሶች በመግባት ፍተሻ ያደርጋሉ። በሽተኞችንና ህጻናትን የታቀፉ እናቶች ሳይቀሩ ፍተሻ በሚል ፖሊስ ጣቢያ ታጉረው መዋላቸውን አይን እማኞች ገልጸዋል። ድርጊቱን ሲታዘብ ...

Read More »

በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ከሰመጡት ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን መካከል የአብዛኞቹ አስከሬን አልተገኘም

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ወደ የመን ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያዊያን ያለቁ ሲሆን እስካሁን ከ14 ያልበለጡ ሰዎች ብቻ አስከሬን መገኘቱን ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ገልጿል። የሟቾች ቁጥር አስቀድሞ በመገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው ሳይሆን 79 መሆኑን ግሩም አክሎ ተናግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕጋዊ ጉዞን ከአንድ ዓመት በላይ አግዶ በመቆየቱ በየጊዜው ለሚሞቱ ሰዎች ምክንያት ...

Read More »

በጋምቤላ 2 የምክር ቤት አባላት አዲስ አበባ ላይ ታሰሩ

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት  አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በካውች ማሞና ኦብዱል ኦቻር የሚባሉትን ባለስልጣኖች አውርዷቸዋል። ግለሰቦቹ ያለመከሰስ መብታችን የተነሳው በህገወጥ መንገድ ነው በማለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለማግኘት ሙከራ ቢያደርጉም፣ ደህንነቶች ይዘው አስረዋቸዋል። ባለስልጣኖቹ ከውጭ ሃይሎች ጋር ትገናኛላችሁ በሚል መከሰሳቸውን የአኝዋ ሰርቫይቫል ዋና ሃላፊ አቶ ኒካው ኦቻላ ለኢሳት ገልጸዋል

Read More »

በአዲስአበባ ባለፉት ሶስት ቀናት የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት በዛሬው ዕለት ተባብሶ በአብዛኛዎቹ ማደያዎች በተሸከርካሪዎች ወረፋ ተጨናንቀው ዋሉ፡፡

ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችን በአራት ኪሎ፣ በቦሌ፣ በካዛንቺስ፣ በልደታ አካባቢዎች የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ተዘዋውሮ እንደተመለከተው በብዙዎቹ ማደያዎች በዛሬው እለት ነዳጅ ቢኖርም ነዳጅ ለመቅዳት የተሰለፉ ተሸከርካሪዎች በመብዛታቸው ረጃጅም ሰልፎች መታጣቸውንና የትራፊክ መጨናነቅ መከሰቱን መታዘብ ችሎአል፡፡ በዓለም ገበያ ላይ የነዳጅ ዋጋ መቀነስን ተከትሎ ከትላንትና ህዳር 30 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ንግድ ሚኒስቴር መጠነኛ ቅናሽ አድርጓል። ሚኒስቴሩ በነዳጅ ምርቶች ...

Read More »

መድረክ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የሆነው መድረክ የኢህአዴግ አገዛዝ በህዝባችን ህገመንግስታዊ ነጻ የመምረጥ መብት ላይ የሚፈጽማቸውን የመብት ረገጣዎች እንዲያቆም፣ በሃገራችን ነፃ ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ እውን እንዲሆና የምርጫ ሜዳውም ለሁሉም እኩል የተመቻቸ እንዲሆን ለመጠየቅ ለታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ መጥራቱን አስታውቋል። መድረክ ለኢህአዴግ አገዛዝ የውይይትና የድርድር ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ቢያቀርብም፣ አገዛዙ አሻፈረን ማለቱን አስታውሶ ” ይህንኑ ...

Read More »

በእስር ላይ በሚገኙት የ9 ፓርቲዎች ትብብር አባላት ላይ የተወሰደውን እርምጃ የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጀቶች አወገዙ

ኀዳር ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የሽግግር ካውንስል ለኢሳት በላከው መግለጫ የአፓርታይድ ስርአትን እአካሄደ ያለው የወያኔ አገዛዝ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ሊወገዝ ይገባዋል ብሎአል። የኢኮኖሚ እድገት አምጥቻለሁ እያለ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ መንግስት ፣ በስልጣን ላይ ለመቆየት ብቸኛ መተማመኛው ሃይል መሆኑን አሳይቷል ያለው የሽግግር ካውንስል፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ድርጊቱን እንዲያወግዙ ጥሪ አቅርቧል። ግንቦት7 በበኩሉ ድርጊቱን ...

Read More »