በአብርሃ ጅራ አለመረጋጋቱ ጨምሯል

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው። እስካሁን በተደረገው አፈሳ የወረዳው ምክር ቤት  የህዝብ ግንኙነት ...

Read More »

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ፖለቲከኞች የሽብር ክሱን አጣጣሉት

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ የተከሰሱ የቀድሞው የአንድነት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣  ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አመራር መምህር አብራሃ ደስታ ከሌሎች 6 ተከሳሾች ጋር መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ...

Read More »

በአብርሃጅራ ከተማ ጸጉረ ልውጦች ገብተዋል በሚል ፍተሻ እየተካሄደ ነው

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ  አርማጭሆ በአብርሃጅራሃ ከተማ ፀጉረ ልውጥ ሽፍቶችን አስገብተዋል በተባሉ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። የከተማው ሕዝብና የአካባቢው ገበሬ በከፍተኛ ሥጋት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በሆቴሎች በዋና ዋና መንገዶችና መተላለፊያዎች ላይ  ፍትሻ እየተካሄ ነው። ነዋሪዎች ደግሞ በሚሄዱበት አካባቢ ሁሉ መታወቂያቸውን እየተጠየቁ ነው። እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋለ አንድም ጸጉረ ልውጥ ...

Read More »

ሶስቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች የአዳጊ ክልሎችን ሪፖርት አዳማጡ

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ልዩ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል በሚል ክልሎችን ህወሃት፣ ብአዴንና ኦህዴድ እንዲያስተዳድሩዋቸው ካከፋፈለ በሁዋላ፣ የክልሎችን የመጀመሪያ ሪፖርት ሰሞኑን ተቀብሎአል፡ ኢሳት ቀደም ብሎ በሰራው ዘገባ የሶማሊ ክልል በህወሃት፣ ሃረሪ በኦህዴድና ህወሃት፣ አፋር በህወሃት፣ ቤንሻንጉል በብአዴን እንዲሁም  ጋምቤላ በህወሃት እንዲተዳደሩ መወሰኑን ዘግቦ ነበር። እነዚህ አዳጊ የተባሉ ክልሎች ማንኛውንም የስራ እንቅስቃሴያቸውንና እቅዶቻቸውን  ለእነዚህ ድርጅቶች የማቅርብ ግዴታ ተጥሎባቸው የቆየ ...

Read More »

መንግስት የሚያከፋፍላቸውን ዘይት እና ስኳር ከምርጫ ካርድ ጋር እያያዘው ነው

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በመጪው ግንቦት ወር ምርጫ የምርጫ ካርድ ያልያዙ ሰዎች ስኳርና ዘይት እንደማያገኙ እንደተነገራቸው ለኢሳት ተናግረዋል። አንዳንድ ቀበሌዎች የምርጫ ካርድ ዘይትና ስኳር ለመሸጥ የምርጫ ካርድ አብረው የሚጠይቁ ሲሆን፣ ካርድ ላልወሰዱት እንዲወስዱ እየጠየቁ ነው። መራጮች የመምረጥም ሆነ ያለ መምረጥ መብት ቢኖራቸውም ፣ ገዢው ፓርቲ ከስኳርና ዘይት ጋር ማያያዙ ተገቢ አለመሆኑን ነዋሪዎች ...

Read More »

ታዋቂ ወጣት ፖለቲከኞች ታሰሩ

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-3 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ወጣት ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል። ወጣቶቹ በምን ምክንያት እንደታሰሩ ለማወቅ አልተቻለም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው ይፋ መግለጫ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ የፓርቲው ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት በመጪው ...

Read More »

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት  በአሜሪካ የደረሰባቸው ተቃውሞ በጠ/ሚ ሃይለማርያም፣ ጌታቸውን አሰፋ፣ ኢሳትና ሌሎች ሃይሎች የተቀነባበረ ነው አሉ

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ተቃውሞ ያገጠማቸው አቶ አብዲ ሙሃመድ ተቃውሞውን ያቀነባበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢሳት ፣ ግንቦት7 እና የኤራትራ መንግስት በጋራ በመሆን ነው ሲሉ አካራ ኒውስ በተባለው የግል ዌብሳይታቸው ላይ በሶማልኛ ባወጡት ረጅም ጽሁፍ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞውን ሲያሰማ የነበረውን መኮንን የተባለውን ሰው ስም ከፊት በማስቀደም፣ መኮንን ጌታቸው ...

Read More »

ኤልፓና መከላከያ በባቡር የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የተነሳ እየተወዛገቡ ነው

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰራው የቀላል የባቡር መንገድ የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ዝርጋታ ርክክብን በተመለከተ በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሽንና እና በመከላከያ ኢንጂነሪንግ የስራ አስፈፃሚ አመራሮች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን የውስጥ ምንጮች አመለከቱ፡፡ በመጀመሪያ መንግስት ለባቡሩ የሚያስፈልገውን  የኤሌክትሪክ አቅርቦት ግንባታ ለማስጀመር ከአንድ የግብጽ ኩባንያ ጋር ለመዋዋል በእንቅስቃሴ የነበረ ቢሆንም፣  ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካኤል ...

Read More »

የውሃና ችግር የኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት መነጋገሪያ ሆኗል

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከትግራይ እስደ ደቡብ ክልል የውሃ ጀሪካኖችን በምንጮችና በውሃ መስጪያ ባንቧዎች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች የውሃ እጥረት ማጋጠሙን የየክልሉ ሪፖርተሮች ከሚልኩት እለታዊ መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

Read More »

በሚስጢር የተያዘው የአባይ ግድብ ስምምነት ሊፈረም ነው

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚስጢር ሲያደርጉት የቆዩት ድርድር ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የሶስቱ አገር መሪዎች በተገኙበት በካርቱም እንደሚፈረም መረጃዎች አመልክተዋል። የፊርማ ስነስርአቱ የፊታችን ሰኞ በካርቱም የሚካሄድ ሲሆን፣ ዝርዝር ይዘቱ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ተደርጓል። የአባይ ግድብ  ከህዝብ በውዴታና በግዴታ በሚዋጣ ገንዘብ እየተገነባ መሆኑ እየታወቀ፣ ስምምነቱን ገንዘቡን ለሚያዋጣው ህዝብ ይፋ ለማድረግ ለምን እንዳልተፈለገ ግልጽ አይደለም። ሱዳንና ግብጽ ስምምነቱ ...

Read More »