የውሃና ችግር የኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት መነጋገሪያ ሆኗል

መጋቢት (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከትግራይ እስደ ደቡብ ክልል የውሃ ጀሪካኖችን በምንጮችና በውሃ መስጪያ ባንቧዎች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች የውሃ እጥረት ማጋጠሙን የየክልሉ ሪፖርተሮች ከሚልኩት እለታዊ መረጃ ለመረዳት ይቻላል።