ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ ግንቦት15 ፣ 2007 ዓም የተካሄደው ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንደተካሄደ መንግስትና ብቸኛው የውጭ ታዛቢ የአፍሪካ ህብረት ቢገልጽም፣ በምርጫው የተሳተፉ ታዛቢዎችና መራጮች ምርጫው በአሳዛኝ ሁኔታ መካሄዱን መስክርነታቸውን እየሰጡ ነው። በአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ የነበረው አቶ መሰለ አድማሴ እንደገለጹት እርሳቸው በታዘቡበት የምርጫ ጣቢያ፣ የምርጫ ኮሮጆዎች ታዛቢዎች ሳይገኙ መከፈታቸውን፣ ...
Read More »ከ2 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመለሱ
ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦም ኤም፣ የመን ውስጥ በችግር ላይ የነበሩ 2061 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል። ከተመሰሉት መካከል የቆሰሉ ኢትዮጵያውያንም አሉበት። አይ ኦ ኤም በአዲስ አበባ ጊዚያዊ ማቆያ ጣቢያ ተመላሾችን በማስፈር የትራንስፖርት እና የጤና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል። ሃድራ የተባለች ተመላሽ በቤት ሰራተኛነት ስትሰራ እንደነበር ገልጻ፣ የአየር ድብደባ በሚካሄድበት ወቅት ...
Read More »በዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች ላይ ምስክሮች ቀረቡ
ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስር ላይ በሚገኙ ዞን ዘጠኝ በሚል መጠሪያ ስም በሚታወቁት ወጣት ጸሃፊዎች ላይ ምስክሮች ቀርበው ፣ የክሱን ጭብጥ በደንብ በማያስረዳና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ነገሮች በመናገር ማሳለፋቸውን ችሎቱን የተከታሉት ታዛቢዎች ገልጸዋል። ችሎቱን ለመከታተል የታደሙ ታዛቢዎች ምስክሮች ሲንተባተቡ እያዩ ችሎት ውስት ይስቁ እንደነበር ታዛቢዎች ገልጸዋል። ወጣት ጸሃፊዎቹ በማእከላዊ እስር ቤት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ...
Read More »አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ምልክት አሳይተዋል ያሉዋቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎች አስጠነቀቁ፡፡
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ተገኝተው ከኢህአዴግ የም/ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህ ምላሻቸውም በስም ያልጠቀሱዋቸውን ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ወደምርጫው የገቡት በግማሽ ልብ መሆኑን ፣ የብጥብጥና የሁከት አማራጭ ከተገኘ ያንን ለማካሄድ የሚያስቡ ናቸው ሲሉ ፈርጀዋቸዋል። ” የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ እኛ አሸንፈናል፣ ከተሸነፍን ደግሞ ምርጫው ተጭበርብሮአል፣ ይህንን አውቃችሁ ...
Read More »በየመን 5 ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተዘገበ
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዩተርስ ከካይሮ እንደዘገበው በሳውድ አረቢያ የሚመራው የጥምር ሃይል በየመን በአንድ አለማቀፍ የበጎ አድራጎት ጽህፈት ቤት ላይ በወሰደው ጥቃት 5 ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ 10 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃቱ የሃውቲ ሚሊሺያዎች ዋና ደጋፊ ተደርጎ በሚቆጠረው ሃጅያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ማይዲ ከተማ ላይ በከባድ መሳሪያና በአየር መፈጸሙን የዜና ድርጅቱ ገልጿል። የሳውድ አረቢያ ጦር ከሃውቲ ሚሊሺያዎች ...
Read More »በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለአማራው መፈናቀል ምክንያት የሆነው ክልሉ የፈረመበት ደብዳቤ ኢሳት እጅ ውስጥ ገባ
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 ዓም ቁጥራቸው ከ20 ሺ ያላነሰ በአብዛኛው ከመስራቅና ምእራብ ጎጃም የመጡ ዜጎች፣ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው ቁጥራቸው በውል ያልተወቁት መንገድ ላይ ሲሞቱ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል። በጊዜው ኢሳትና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ባደረሱት ተጽኖ መንግስት ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ቢያደርግም፣ አጥፊዎችን ለፍርድ የማቅረቡ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ሲጓተት ቆይቶ በመጨረሻ መንግስት የተወሰኑ የወረዳ ባለስልጣናትን ...
Read More »የአየር ሃይልና የመከላከያ አባላት ክስ ተመሰረተባቸው
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል፤ አባላትን መልምለዋል፤ ለሽብርተኛ ቡድኑ መረጃ አቀብለዋል፤ እንዲሁም ወደኤርትራ በመኮብለል የሽብር ድርጅቱን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ተሰናድተው ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ በሚል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በ7 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመሰርቱን ሰንደቅ ዘግቧል። ተከሳሾች መቶ አለቃ ...
Read More »በተቃዋሚ ፓርቲ ወጣት አባላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ አስከፊ ሆኖ ቀጥሏል
ሚያዝያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ህዝቡን አስተባብረው ህዝባዊ አመጽ ያስነሱ ይሆናል በሚል የሚጠረጥራቸውን ወጣቶች ሁሉ እያፈሰ ከማሰር አልፎ ፣ አንዳንዶች እየተገደሉ ሌሎች ደግሞ አሰቃቂ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ የሚማር አንድ የመድረክ አባል እንደሆነ የሚታወቅ የ3ኛ አመት ተማሪ ግቢው ውስጥ ወድቆ ከተገኘ በሁዋላ የተሻለ ህክምና ለማግኘት ባለመቻሉ ህይወቱ ...
Read More »ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ሲሄዱ ተያዙ የተባሉት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሚያዝያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ግንቦት 12/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት በሃያዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው ፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ ናቸው። ተከሳሾች “ኤርትራ ውስጥ መቀመጫውን ባደረገውና በሽብርተኝነት በተፈረጀው ግንቦት ሰባት ስር አባል ሆነው የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ወስነው ከድርጅቱ ጋር ለመቀላቀል የኢትዮጵያንና የኤርትራን ...
Read More »መጭውን ምርጫ ተከትሎ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ውጥረት እየታየ ነው
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በተለይ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል አብዛኛው ህዝብ ረብሻ ይነሳል ብሎ ያምናል። በዚህም የተነሳ ቀድም ብለው ገንዘባቸውን ባንክ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸውን እያወጡ ለምግብ የሚውሉ የእህል ዘሮችን፣ ጨውና ሌሎችንም እቃዎች እየገዙ ነው። ወፍጮ ቤቶች ሰሞኑን ተጨናንቀው ታይተዋል። አቅም ያለው ቤተሰብ ለሶስት ወር የሚበቃ እህል ሲያስፈጭ፣ ድሃው ...
Read More »