ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የኮሚቴው አባላት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በችሎቱ ቢታደምም፣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የማሰማቱን ሂደት በድጋሜ ወደ ሰኞ አራዝሟል። ችሎቱ የአቃቢ ህግ መስክሮችን ቃል አንብቦ ከጨረሰ በሁዋላ ተከሳሾች ለፖሊስ ሰጡት ያለውን ቃል በንባብ አሰምቷል። የፊታችን ሰኞ የመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ...
Read More »በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ የሚሰጠው ፍርድ ለነገ ተራዘመ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የነበረውን ፍርድ ያራዘመ ሲሆን፣ ፍርዱ ለምን እንደተራዘመ ግን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በአቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ 18 የኮሚቴው አባላት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው የመጨረሻውን ፍርድ ለመስማት ችሎት የተገኙ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ የክሱን ጭብጥና የምስክሮችን ቃል በማጠቃለያ መልክ ...
Read More »ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት የሚመዘገብ ወጣት መጥፋቱ እየተነገረ ነው
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመከላከያ ሰራዊት ያወጣው አዲስ የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሰሜን ሸዋ ከሁለት ሳምንት በፊት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ተመዝጋቢ በመጥፋቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል። በአርባምንጭ ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች በመኪና እየዞሩ ወጣቱ ለመከላከያ አባልነት እንዲመዘገብ እየቀሰቀሱ ነው። ይሁን እንጅ ለጥሪው ወጣቱ የሚሰጠው ምላሽ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ...
Read More »ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባለአክሲዮን የሆኑበት ኮሌጅ የህግ ትምህርት መስጠቱን ቀጥሎአል
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም መልኩ የህግ ትምህርት በግል ተቋማት እንዳይሰጥ የከለከለ ሲሆን፣ የአቶ ደመቀ ከፊል ንብረት የሆነው ሚሸከን ኮሌጅ ግን ተማሪዎችን እያሰተማረ እንደሚገኝ መረጃዎች አመልክተዋል። ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀሙ ኮሌጆች ቢዘጉም፣ ለሚሽከን ኮሌጅ ግን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ከማሰጠንቀቂያ ያለፈ ውሳኔ አልሰጠውም። የሚሽከን ኮሌጅ መስራች በአዊ ብሄረሰብ አሰተዳደር ዞን ...
Read More »በአርባምንጭ የፌደራል ፖሊሶች ሲከታተሉት የነበረ መኪና መስመር በመጣሱ 7 ሰዎች ሞቱ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓም ከጧቱ 1 ሰአት ላይ መድሃኒአለም በሚባል አካባቢ ሁለት መኪኖች ኮንትሮባንድ እቃ ጭነዋል በሚል ምክንያት ሲከተሉዋቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በድንገት ተኩስ በመክፈታቸው አንደኛው መኪና መስመሩን ስቶ ከወጣ በሁዋላ በመገልበጡ 7 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። አብዛኞቹ ሟቾች በማግስቱ ለሚደረገው የአርባምንጭ ...
Read More »ኢህአዴግ ዲያስፖራውን ለመያዝ ያደረገው ጥረት መክሸፉን ተከትሎ አዳዳስ ስልቶችን እየቀየሰ ነው
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዲያስፖራውን በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ለመያዝ ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት መክሸፉን ተከትሎ ፣ የዲያስፖራውን ቀልብ ሊስቡ ይችላሉ ያላቸውን አዳዲስ ዘዴዎች እያሰላሰለ ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲያስፖራ ሳምንት ዝግጅት ዙሪያ አስመልክቶ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በክልልና በፌደራል ደረጃ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ፣ በዲያስፖራው ...
Read More »ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በምስክርነት ይቅረቡ አይቅረቡ በሚለው ላይ ብይን ይሰጣል
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ወንጀል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለመኢአድ አባላት መከላከያ ምስክር መሆን መቻል አለመቻላቸው ላይ ነገ ሰኔ 24፣ 2007 ዓ.ም ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በግንቦት ሰባት አባልነት የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባላት ‹‹በአንዳርጋቸው ፅጌ አሰልጣኝነት የሽብር ተግባር ለመፈፀም ተንቀሳቅሳችኋል፡፡›› በሚል ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ እነሱም ‹‹አንዳርጋቸው ፅጌ ...
Read More »ባለፉት ሶስት አመታት ወደ አገር ውስጥ ከገቡ የውጭ ፕሮጀክቶች ውስጥ አብዛኞቹ ተሰረዙ
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሚቀጥለው አምስት አመታት ይተገበራል ተብሎ በተዘጋጀ የሁለተኛ ዙር የ5 አመታት እቅድ ላይ በተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ እንደተመለከተው ባለፉት ሶስት አመታት 2 ሺ 995 ፕሮጀክቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ስኬታማ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ተሰርዘዋል። በአማራ ክልል በባህርዳር እንዲሁም በኦሮምያ ክልል አዳማ የተደረገውን የምክክር ጉባኤ አስመልከቶ የተዘጋጀው ሰነድ እንደሚያሳየው፣ በዚህ አመት ወደ አገር ውስጥ ከገቡና ...
Read More »በኢትዮጵያ የአእምሮ ጭንቀት ሁለተኛው ገዳይ በሽታ ተባለ
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ የሳምባ ምች በሽታ የመጀመሪያው ገዳይ በሽታ የነበረ ሲሆን፣ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ኤች አይ ቪ ኤድስ አንደኛ የአእምሮ ጭንቀት ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኤ አይ ቪ ኤድስ በኢትዮጵያ እየቀነሰ መምጣቱ ቢነገርም፣ በሽታው አሁንም ቀዳሚ ገዳይ በሽታ ተብሎአል። የአእምሮ ጭንቀት ሁለተኛ ገዳይ በሽታ መሆኑ ቢታወቅም፣ መንስኤው ምን ...
Read More »በነጻ እንዲፈቱ በፍርድ ቤት የተወሰነላቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በድጋሚ ታሰሩ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 23 2007) ሰሞኑን ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ወስኖላቸው ፖሊስ በድጋሚ ለእስር በዳረጋቸው አራት የፓርቲ አባላት ላይ አቃቢ ህግ ይግባኝ ጠየቀ። ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸው ከውጭ ሆነው ለመከታተል ጥያቄን ቢያቀርቡም ከሳሽ አቃቢ ህግ ተቃውሞን እንዳቀረበ ከሀገር ቤት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ጉዳዩን ለማየት የተሰየሙት ዳኛ ተከሳሾች እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ስለመቆየታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው አንደኛ ተከሳሽ ባለመቅረቡ ...
Read More »