መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለከተማ ቤቶች መስሪያ፣ ለልማት ወይም ህገወጥ ግንባታ በሚል አርሶ አደሮች ያለምንም ክፍያ ከይዞታ መሬታቸው እየተፈናቀሉ ማህበራዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በኦሮምያ ክልል በ አዳማ ከተማ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች ቦታቸውን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን፣ በርካታ ቤቶችም ፈርሰዋል። በማሳ ያለው ሰብል ሲደርስ ...
Read More »በጋምቤላው ግጭት 126 ሰዎች መገደላቸውን መንግስት ገለጸ
መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቃቢ ህግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ቀድም ብሎ 60 ሰዎች መገደላቸውን ከጠቀሰ በሁዋላ፣ አሻሽሎ ባቀረበው ክስ 126 ሰዎች በወረዳ አመራሮች ትእዛዝ መገደላቸውን ጠቅሷል። በማዣንግ፣ ጎደሬና ሚጤ በሃላፊነት ላይ የነበሩ የወረዳ አመራሮች ” ደገኞች ቦታችንን ለቀው ይውጡ፣ ደገኞች በማዣንግ ዞን ውስጥ የያዙትን የእርሻና የቡና ተክል መሬት ለማዣንግ ብሄር ተወላጆች ያካፍሉ” የሚል ንግግር ...
Read More »በአማራ ክልል በግንባታ ስራ የተሰማሩ ተቋራጮች በጤና ጥበቃ ቢሮው አሰራር መማረራቸውን ተናገሩ፡
መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ዓርብ መስከረም 7/2008 ዓ.ም በድንገት በጠራው የተቋራጮች ስብሰባ፣ በክልሉ የሚገነቡ የጤና ተቋማትን በመስራት ላይ ያሉ ተቋራጮች በሙሉ ሰብስቦ ፤የግንባታ ስራዎች በመጓተታቸው ምክንያት ከልዩ ልዩ ግብረ ሰናይ መንግስታት የተገኘ የዕርዳታ ገንዘብ በየጊዜው ተመላሽ መሆኑ ቢሮውን አሳስቦታ ብሏል። ተቋራጮች በተቻላቸው ፍጥነት ግንባታቸውን በማጠናቀቅ በዕርዳታ የተገኘውን ገንዘብ ከመመለስ እንዲያድኑት ጠይቋል፡፡ ...
Read More »ህወሃት ኢህአዴግ በመዳከሙ የቀድሞ አባሎቹን ለማሰባሰብ ሙከራ እያደረገ ነው ተባለ
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የህወሃት መስራችና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አባል የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ህወሃት ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሞ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ፣ ከድርጅቱ የለቀቁ የቀድሞ አባሎቹን በማነጋገር ወደ ድርጅታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ገልጸዋል። ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ የውስጥ ችግር መዳከሙን የሚገልጹት ዶ/ር አረጋዊ ፣ ...
Read More »በካዛንችስ በርካታ የንግድ ቤቶች እየፈረሱ ነው
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ውስጥ በንግድ እንቅስቃሴያቸው ከሚታወቁት አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው ካዛንችስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች በብዛት የፈረሱ ሲሆን፣ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነዋሪዎች ስጋት ገብቷቸዋል። የመንግስት ቤቶችን ተከራይተው ይሰሩ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች እንዲሰማሩ ቢደረግም፣ የግል የንግድ ቤት የነበራቸው ግን በካሳ መልክ የተከፈላቸው ገንዘብ ...
Read More »የውጭ ምንዛሬ ገቢው እቅድ የማይጨበጥ ህልም ነው ተባለ
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከያዝነው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የወጭ ንግዱን ከ3 ወደ 12 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ መታቀዱ አሁን ሀገሪቱ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ እጅግ የተጋነነና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ያተኮረ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ባለሙያው እንደሚሉት በመጀመሪያው የመንግስት ...
Read More »የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት አገልግሎት አሰጣጥና የክፍያ ስርዓት መመሪያ አወጣ፡፡
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዋጋ ቁጥጥር ውሳኔው አንዳንድ ት/ቤቶች አደናግጦአቸዋል፡፡ መመሪያው ፍትሐዊነት ጎድሎታል ያለውን የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ሁኔታ ሰርኣት የሚያሲዝ ነው ቢባልም ፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። አዲሱ መመሪያ ከስርኣተ ትምህርት ውጪ ልዩ ልዩ የትምህርት ኣይነቶችን ማስተማርና ለዚህም ክፍያ መጠየቅ ይከለክላል፡፡ ክፍያ ሲጠየቅ ለ10 ወራት ብቻ መሆኑን፣ የክረምትና የቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርቶች ...
Read More »በኩዌት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔው ጸናባት
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በኩዌት ሱላቢካት ከተማ ውስጥ የአሰሪዋን ልጅ የ19 ዓመቷን ወጣት ሲሃም ማህሙድ በስለት በመግደል ወንጀል ተከሳ የነበረችው የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ወጣት ራቢያ ማህሙድ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ውሳኔ መፅናቱን የአገሪቱ ፍርድ ቤት አስታውቋል። ግድያውን ለመፈጸም ያበቃት ሟቿ መኝታ ክፍልዋ በተደጋጋሚ ጊዜ በመምጣት በር በመዝጋት ጥቃት የምትፈጽምባት መሆኑንና ይህ ተደጋጋሚ ጥቃት ...
Read More »በኮንጎ ብራዛቪል ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው
መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በመላው የአፍሪካዊያን ጫወታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው። በ5 ሺ ሜትር የወንዶች የሩጫ ውድድር ጌትነት ሞላ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፣ ርቀቱን በ 13 ደቂቃ 21 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ልዑልሲ ገብረስላሴ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። በ1 ሺ500 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድርም ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ...
Read More »በወናጎ ከተማ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገዶ
መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 16፣ 2008 ዓም በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ወናጎ ከተማ ከንግድ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ አድጎ ወደ ብሄረሰቦች ግጭት በማምራቱ በርካታ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ የተለያዩ የንግድ ቤቶችም ተዘርፈዋል። የከተማው ባለስልጣኖች ሆን ብለው ቀስቅሰውታል በተባለው በዚህ ግጭት፣ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ነን የሚሉ ሰዎች፣ የሌላ አካባቢ ብሄረሰቦች አካባቢያችንን ለቃችሁ ውጡ በማለት ግጭት ...
Read More »