በከፍተኛ ወጪ የሚገነባው ፈጣን የአውቶቡስ መስመር ተቃውሞ ገጠመው

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በየካቲት ወር 2008 ጀምሮ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ከአዋጪነት አንጻር በሚገባ በጥናት ያልታየና በአሁኑ ሰዓት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን የሚያሳጣ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ፕሮጀክቱ ከዊንጌት፣ በጎፋ ገብርኤል አድርጎ ወደ ጀሞ የሚዘልቅ ለከተማ አውቶቡስ ብቻ የተከለለ መስመር ለመገንባት የታቀደ ሲሆን ...

Read More »

በኬንያና ማላዊ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ላይ ናቸው

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ኢዞሎ ግዛት ውስጥ ድንበር አቋርጠው ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተጨናነቀ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ዘግቧል። በኬንያ ኢዞሎ ጂኬ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት 450 እስረኞች መካከል 300 ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እስር ቤቱ ከ 150 የበለጡ እስረኞችን መያዝ እንደማይችል የኢዞሎ ግዛት ምክትል ኮሚሽነር ገልጸዋል። በኬንያ ውስጥ የሚገኙ ...

Read More »

“የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ይችላል” ተመድ

ኢሳት ዜና (መስከረም 13, 2008) በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ለምግብ እርዳታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥርና የእርዳታ መጠን በቀጣዮቹ አራት ወራቶች በከፍተኛ መጠን ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታወቀ። የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን አካባቢ እንደነበር ያወሳው ድርጀቱ፣ የተረጂዎችን ቁጥር ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀመሮ ጭማሪን እንደሚያሳይ ገልጿል። በፈረንጆቹ አዲስ አመት ባሉ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች አሁን ያለው የ 151 ሚሊዮን ...

Read More »

የኢድ አል አረፋ በአል በመላው አለም ተከበረ

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አል አድሃ በአል ለ1 ሺ 436ኛ ጊዜ በኢትዮጵያና በመላው አለም ተከብሯል። በሳውድ አረቢያ መካ በአሉን ለማክበር በስፍራው ከተገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሃይማኖቱ ተከታዮች መካከል ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተረጋገጥተው ህይወታቸው አልፎአል። ከ900 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በሰንአ በአንድ መስኪድ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ደግሞ 25 ሰዎች ...

Read More »

በሰበታ አይነስውራን ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ፣ ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በፖሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመሰጠቱ ፣ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ፣ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት ገብቶ ...

Read More »

ኢህአዴግ ከድርጅት የሚለቁትን እያገደ ነው

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ በመቀሌ ላይ ባደረገው ጉባኤ ግንባሩን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመሩን የገለጸ ቢሆንም፣ አሁንም ድርጅቱን ጥለው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ፣ ግንባሩ የመልቀቂያ ጥያቄን እንደማያስተናግድ አስታውቋል። ድርጅቱን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡ አባላት አርፈው እንዲቀመጡ ተነግሯቸዋል። ለኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ አባላት፣ የተቃዋሚ አባላት ሆናችሁዋል በሚል ...

Read More »

ዶ/ር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ አረፉ

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ሽመልስ ከሌሎች ታዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር በመሆን ቀስተደመናን ፓርቲ፣ ከዚያም ቅንጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩበት ወቅትም ዶ/ር ሽመልስ፣ ትግሉ እንዳይቀዛቀዝ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ በተመሰረተበት ወቅትም ፓርቲውን በአመራር አባልነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የተቋቋመውና በሁዋላ በስርዓቱ ሃላፊዎች እንዲፈርስ የተደረገውን ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሹም ሽሩ ቀጥሏል

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ 4ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ የወሰደው የከተማዋ አስተዳደር በአስር ክፍለ ከተሞች ሹምሽር አካሄዷል። ከቀናት በፊት በተጀመረው በዚሁ ሹም ሽር በ116 ወረዳዎች የሚገኙ ከ100 በላይ አመራሮች የተነሱ ሲሆን የከተማዋ አስተዳደር ድርጊቱ ከትምህርት ብቃት ጋር የተገናኘ እንደሆነ መግለፁን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብቻ ...

Read More »

በኢትዮጵያና ድሃ አፍሪካ አገሮች የኢንተርኔት ተጠቃሚ ህዝብ ከ 2% እንደሚያንስ ተገለጸ

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ በድሃ ሃገራት ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል 90% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ከአፍሪካ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ሽፋን ያላት ኢትዮጵያም በአለም በአገልግሎቱ አሳሳቢ ተብለው ከተፈረጁ አስር አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ድርጅቱ በአመታዊ ረፖርቱ ገልጿል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ረፐብሊክ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክና፣ ኒጀር  በአለም በጣም ዝቅተኛ የኢንተርኔት ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ልዑካን የኢትዮጵያ ስደተኞችን በተመለከተ ለምክክር ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ

ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) ከኢትዮጵያ የሚደረገውን ከፍተኛ የወጣቶች ስደት ተከትሎ የአውሮፓ ህበረት ልዩ የሉዑካን ቡድን በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ወደአዲስ አበባ መጓዙን ህብረቱ ዛሬ ረቡዕ ገለጠ። በሃገሪቱ የሶስት ቀን ቆይታ የሚኖረው ይኸው የልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣው የወጣቶች ስደት እና ችግሩ በሚቀንስበት ዙሪያ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሰፊ ምክክር ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ ...

Read More »