ኢሳት ዜና (ጥቅምት 4 ፣ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች ላይ የሚፈጽመው በደል ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፌደሬሽን ገለጠ። በኢትዮጵያዊያን ሊሰሩ የሚችሉ ቀላል ስራዎች በውጪ አገር ዜጎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ያስታወቀው ፌደሬሽኑ 20 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ሰራተኞቻቸው በማህበር እንዳይደራጁ ተጽዕኖ አሳድረው እንደሚገኙ አመልክቷል። በተለይ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያዊያን ...
Read More »መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት ምዝገባ አዲስ ቅስቀሳ ጀመረ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው አመት ጀምሮ እንደ አዲስ በተጀመረው የሰራዊት ምልመላ የተፈለገውን የሰራዊት ቁጥር ማግኘት የተቸገረው መንግስት፣ ሰሞኑን ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመኪና ላይ ሆነው ወጣቱ ለውትድርና እንደሚዘገብ በመቀስቀስ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም ለእያንዳንዱ ቀበሌና ወረዳ የተሰጠው ኮታ ሊሟላ ባለመቻሉ፣ መንግስት በስራ ስልጠና ስም ወጣቶችን በመቀስቀስ ያለፍላጎታቸው እንዲዘምቱ ለማግባባት ሙከራ አድርጓል። ይሁን እንጅ ...
Read More »በሁመራ ከ500 በላይ የሞተር አሽከርካሪዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞተር ሳይክል ሰዎችን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ህይወታቸውን የሚመሩ 500 ያክል ወጣቶች ስራ እንዲያቆሙ በመታዘዛቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል። ሰራተኞቹ በድንገት አቁሙ በመባላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ተቸግረዋል። መንግስት አማራጭ ስራ ሳይፈጥር በድንገት ስራ አቁሙ ማለቱ ተገቢ አይደለም በሚል ወጣቶቹ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥተዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ወጣት እንዳለው ...
Read More »በሰሜን ጎንደር የአርባ ፀጓር ፀባሪያ ነዋሪዎች ባለፉት ሃያ አራት ዓመታ ውስጥ ብአዴን ምንም እንዳልሰራላቸው ተናገሩ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተከዜ ወንዝ ጫፍ ላይ የምትኘውና የዋግና የበለሳ ነዋሪዎች መተላለፊያ የሆነችው አርባ ፀጓር ወረዳ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትግል ወቅት የኢህአፓና የኢሕዲን መተላለፊያ መስመር የነበረች ሲሆን በወቅቱ የድሮው ኢሕዲን የአሁኑ ብአዴን ታጋዮች የነበሩት ለሕዝቡ የኑሮ ለውጥና ዴሞክራሲያ ስርዓት እንደሚገነቡ ቃል በመግባታቸው ነዋሪው ሸማቂዎቹን በማገዝ ከለላ ይሰጣቸው የነበረ ሲሆን ድል አድርገው መንበረ ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ...
Read More »የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፥ ESFNA ቶሮንቶን በአዘጋጅነት መረጠ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፥ ESFNA በካናዳ የቶሮንቶን ከተማ የ2016 የስፖርት ክብረ በዓል ዓስተናጋጅ እንድትሆን መርጧል። ውሳኔው የተላለፈው፥ በኢትዮ-ስታር ቶሮንቶ የእግር ኳስ ክለብ ዓስተባባሪነት በቶሮንቶ ካናዳ በተዘጋጀው፥ የESFNA ዓመታዊ ጉባኤ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የክለብ ተዎካዮችና የቦርዱ ዓመራር ዓባላት በተገናኙበት፥ ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ October 10 እና 11, 2015 የፌዴሬሽኑ ዓመታዊ የስራ ...
Read More »የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች በፈጠሩት ችግሮች የኦሞና የቱርካና ሃይቅ የመድረቅ አደጋ ከፊታቸው ተጋርጧል ተባለ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙት የቱርካና ሃይቅና የኦሞ ወንዝ ኢትዮጵያ በምትከተለው የኢንዱስትሪ ዘመቻ ምክንያት የመድረቅ እና የአየር ንብረት መዛባት አደጋን ማስከተሉንና በዚህም ለውጥ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ሂውማንራይትስ ወች በጥናት ሪፖርቱ አመልቷል። በሰሜናዊ ምዕራብ ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚገኘው የቱርካና ሃይቅ በዓለማችን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ ሃይቆች አንዱ ሲሆን ዘጠና ...
Read More »የአለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች መንግስት በድርቅ ለተጎዱት ዜጎቹ በቂ ገንዘብ እንዲመድብ ጠየቁ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኙ 8 ሚሊዮን 200 ሺ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚሹ፣ በከተማ ውስጥ የሚኖሩ 4 ሚሊዮን ተረጅዎች እንዳሉ በመንግስት እና በአለማቀፍ ድርጅቶች ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ የአለማቀፍ ድርጅቶች መንግስት ለልማት በሚል የመደበውን ገንዘብ የዜጎቹን ነፍስ ለመታገድ እንዲያውለው ጠይቀዋል። እስከሚቀጥለው ታህሳስ ወር ድረስ ምግብ ገዝቶ ለማቅረብ የሚያስፈልገው 12 ቢሊዮን ብር ገደማ ሲሆን፣ መንግስት ...
Read More »በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተነሳው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያውያንና በሱዳን መንግስት ወታደሮች መካከል የተነሳው ጦርነት መቀጠሉን ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያመለካታሉ።ኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች፣ ከዚህ ቀደም ማንነታቸው ያልታወቁ የሱዳን ታጣቂዎች 8 ኢትዮጵያውያንን ለሹፌርነት እንቀጥራችሁዋለን በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ከመኪና ላይ አውርደው መግደላቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያኑ በወሰዱት አጸፋ እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሱዳን ወታደሮችን ገድለዋል። የሱዳን መንግስት ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው ልኳል። የኢህአዴግ ...
Read More »በሲዳማ ዞን በተነሳ ግጭት ጉዳት እየደረሰ ነው
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ ፣ ወታራና ጉጉማ በሚባሉ አካባቢዎች ከ2004 ዓም ጀምሮ በእየአመቱ የሚቀሰቀሰው ግጭት ሰሞኑን አገርሽቶ፣ እስካሁን 2 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ተጎድተው አዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሲገቡ፣ መጠኑ ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል። በቦንኬ ጎሳና በጉኑፋ ጎሳዎች መካከል የተነሳው ግጭት መንስኤ የአንዱ አካባቢ ተወላጅ ሌላውን ማስተዳደር አይችልም የሚል ሲሆን፣ የአካባቢው ተቃዋሚች በበኩላቸው ...
Read More »በማላዊ በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በደል እየተፈፀመባቸው ነው
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላ ዊ የድንበር ጠባቂዎች የተያዙ ከ317 በላይ ኢትጵያዊያን ስደተኞች በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው መሆኑን አጃን ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የማላዊ ፍርድ ቤት በስደተኞች ላይ የእስር ቅጣትና ስድሳ አምስት የአሜሪካን ዶላር መቀጮ የጣለባቸው ሲሆን ፣ አብዛሃኞቹ ከስድስት ወራት በላይ በእስር ያሳለፉ አሳልፈዋል። ወደ ...
Read More »