ኢሳት (ጥቅምት 17 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ተሸክሞ ያለው ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ጫናን አልፈጠረም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። የአለም አቀፉ ሞኒተሪ ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) እና በርካታ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ሃገሪቱ ተሸክማ ያለው ከፍተኛ ብድር ኢኮኖሚውን እየጎዳው እንደሚገኝ በመግለጽ ላይ ናቸው። በሃገሪቱ የተከማቸ ብድር መጠን ከኢትዮጵያ አጠቃላይ አመታዊ ምርት 50 በመቶውን እንደሚሸፍንና ...
Read More »131 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ኬንያ አሳልፋ እንድትሰጥ ኢትዮጵያ ጠየቀች
ኢሳት (ጥቅምት 17 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኛ ወንጀል ይፈለጋሉ በማለት ኬንያ 131 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን አሳልፋ እንድትሰጠው ጥያቄ መቅረቡን የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ገለጠ። የኢትዮጵያ የደህንነት እና ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ለኬንያ አቻው ያቀረበውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎም በእስካሁኑ ሂደት አቶ ደበሳ ጉያ የተባለ ስደተኛ ኢትዮጵያ የገባበት ሊታወቅ አለመቻሉን የሊጉ ፕሬዚዳንት አቶ ጋሩማ በቀለ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በሽብርተኛ ...
Read More »“በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት አለ” የሚለው ተረት ተረት ነው ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ
ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊቀመንበር እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህን ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበውን የውይይት ግብዣ ተቃዋሚዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ለፓርላማ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው። መንግስት በጠራው የአምስት ኣመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ያልተሳተፉ እንደመድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያተ ውሃ ያማያነሳ ነው ...
Read More »ብአዴን 35ኛ አመቱን ለማክበር ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣል
ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ብአዴን ወጪውን የሚሸፍነው በዋነኝነት ከነጋዴዎችና ከነዋሪዎች ነው። በርካታ የክልሉ ነጋዴዎች ገንዘብ እንዲለግሱ የጥሪ ወረቀት ደርሶአቸዋል። ድርጅቱ ከህወሃትና ከኦህዴድ ባላነሰ መልኩ በአሉን እንደሚያደርግ እየገለጸ ሲሆን፣ አገሪቱ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ አንዣቦባት ባለበት እንዲሁም የኑሮ ውድነቱ የህዝቡን ኑሮ ፈተና ውስጥ በጣለበት ሰአት ይህን ያክል ገንዘብ ህዝቡን አስገድዶ በማውጣት ለማክበር ማሰብ ኢ-ሞራላዊና ...
Read More »የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ሽመልስ ከማል ከኃላፊነታቸው ተነሱ
ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሽመልስ ፣ አቶ በረከት ስምኦን ከኮምኒኬሽን ሚኒስትርነት ተነስተው በአቶ ሬድዋን ሁሴን ከተተኩበት ካለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ ከአቶ ሬድዋን ጋር መስማማት ባለመቻላቸው በስራ ገበታቸው ላይ የሚገኙት አልፎ አልፎ ነበር፡፡ የሁለቱ ሚኒስትሮች አለመግባባት በኢሳት ከቀረበ በኃላ ችግር የለብንም ለማለት ለአንድ ቀን አብረው መግለጫ በመስጠት ጎን ለጎን ተቀምጠው ከታዩ ወዲህ ደግመው እንኳን ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አሁንም ወደ የመን መፍለሳቸውን እንዳላቆሙ ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት አሳታወቀ
ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መነሻቸውን ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻዎች በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ሕይወታቸውን ለአደጋ አልጋልጠው በጦርነት ሰላሟ ወደራቃት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ቁጥር መጨመሩን ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት በምህጻረ ቃል /UNHCR/ አስታውቋል። ባለፈው ዓመት ብቻ ከ70 ሺ በላይ አዲስ ስደተኞች የመን መግባታቸውን የገለጸው ድርጅቱ፣ ጥቂት የሶማሊያ ዜጎች ሲገኙበት አብዛኞቹ ስደተኞች ኢትዮጵያዊያን ናቸው። 88 ስደተኞች በባሕር ውስጥ ሰጥመው ...
Read More »በጎንደር አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በ6 ፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ራሱን አጠፋ
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ አምሳሉ ተሾመ የተባለው ታጋይ ሰዎችን በመመልመል ወደ በረሃ ተልካለህ ተብሎ በመጠርጠሩ፣ ፖሊሶች ሊይዙት ሲሞክሩ፣ እጄን አልሰጥም በማለት በያዘው ሽጉጥ አንድ የመቶ እልቅና ያለው መኮንንና ሌላ አንድ ተራ ፖሊስን በመግደል፣ እንዲሁም 4 ታጣቂዎች በማቁሰል በመጨረሻም በያዘው ሽጉጥ ራሱን አጥፍቷል። ወጣቱ ከዚህ ቀደም የአርበኞች ግንቦት7 አባል ...
Read More »በቴፒ የመንግስት ታጣቂዎች ህዝቡን ሲያዋክቡት ሰነበቱ
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድቡብና ጋምቤላ የድንበር ከተማ በሆነቸው ቴፒ ራሳቸውን ያደራጁ ወጣቶች በመልካም አስተዳደርና ህዝቡን አፍኖ በመግዛት ለስቃይ ዳርገውታል ባሉዋቸው የመንግስት ታጣቂዎች እና ሹማምንት ላይ የሚያደርሱትን የሃይል ጥቃት መቆጣጠር እየተሳነው የመጣው መንግስት ካለፈው አርብ ጀምሮ፣ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች ጥቃቱን በማስፋት ነዋሪዎች ሲያሰቃይ ሰንብቷል። የመንግስት ታጣቂዎች፣ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች ሰብረው በመግባት፣ ህጻን፣ አዛውንት፣ ሴት ወንድ ...
Read More »በአዲስ አበባ እስረኞች አመለጡ አንዱ ተገደለ
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት 3 ያህል እስረኞች ማምለጣቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ እስረኞቹ በተለምዶ ሰባራ ባቡር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ፍርድ ቤት ፊት ለፊት አስፓልቱ ላይ ከመኪና ወርደው ወደ ፍርድ ቤቱ በሚገቡበት ወቅት መጥፋታቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ ሶስት ያህል እስረኞች ...
Read More »ኬንያ ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ኢትዮጰያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳደረበት ሂውማን ራይትስ ሊግ ገለጸ
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊጉ ለኢሳት በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ለኬንያ መንግስት የ131 የኦሮሞ ተወላጆችን ስም በመዘርዘር በሽብረተኝነት የሚፈለጉ በመሆኑ ተላልፈው እንዲሰጡት ጠይቋል። በቅርቡ ኬንያ ውስጥ የደረሱበት ያልታወቁት የ80 አመት አዛውንቱ አቶ ደባሳ ጉዮ፣ ከ35 አመታት በላይ ከኖሩበት ኬንያ ታፍነው መወሰዳቸውን ገልጿል። ድርጅቱ የኬንያ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ላቀረበለት ...
Read More »