በኬንያ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንና ናይጀሪያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) የኬንያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸውን ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንና ናይጀሪያውያን በቁጥጥር ስር አዋለ። የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ከቀናት በፊት 23 ኢትዮጵያውያንን በተመሳሳይ ሁኔታ ከያዙ በኋላ 114 ስደተኞች በቁጥጥር ስር ሲዉሉ የመጀመሪያው መሆኑን ዘስታንድራድ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። 114 የሚሆኑት የኢትዮጵያን የናይጀሪያ ስደተኞች በመዲናይቱ ናይሮቢ ኑአሪካ ተብሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተያዙ ሲሆን፣ ምን ያህሉ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ...

Read More »

ብሄራዊ ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ ተካሄደ

ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱና መንግስት እየፈጸመ ያለውን ብሄራዊ ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ አርብ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በኑር መስጊድ ተካሄደ። ለሶስተኛ ሳምንት በተካሄደው በዚሁ ተከታታይ ተቃውሞ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማትና በማውለብለብ እየደረሰብን ነው ያሉት ብሄራዊ ጭቆና እንዲያበቃ መጠየቃቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የአርብ የጸሎት ስነ-ስርዓት ተከትሎ የተካሄደው ይኸው ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል እንግልት እስር ተጠናክሮ መቀጠሉ ዶ/ር መረራ ለኢሳት ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል እስርና ማንገላታቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ። ዶ/ር መረራ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ትናንት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኦሮሚያ ክልል ስላለው ህዝባዊ ንቅናቄ አስመልክቶ በፓርላማ ቀርበው የተናገሩትን ንግግርም አጣጥለዋል። አቶ ሃይለማሪያም ይቅርታ የሚመልስና ጥፋትን የማመን ዝንባሌ ያሳዩት ለፈረንጅቱ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ነው ያሉት ዶ/ር መረራ፣ ኣሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዛሬም ተቃውሞዎች ቀጥለዋል

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ባነሱ ዜጎች ላይ በአንድ በኩል የሃይል እርምጃውን አጠናክሮ በመቀጠል በሌላ በኩል ደግሞ የአገር ሽማግሌዎችንና በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ይኖራቸው ይሆናል ብሎ የሚያምናቸውን ሰዎች በመጥራት፣ “ልጆቻችሁን ተቆጡልን፣ ጥያቄያቸውን እንመልሳለን” በማለት መረጋጋት ለመፍጠር ቢሞክርም፣ ሳምንቱን እንደታየው ሁሉ ዛሬም፣ ተቃውሞው በተለያዩ አካባቢዎች ተካሂዷል። ለአመታት የዘለቀው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ከጁምዐ ጸሎት በሁዋላ ...

Read More »

በዱባይ የታሰሩት ነጋዴዎች ቤተሰቦች መንግስት እንደረሳቸው ተናገሩ

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከየካቲት 13 እስከ 17 ቀን 2008 በዱባይ “ገልፍ ፉድ ፌር ኤግዚቢሽን” ላይ ለመካፈል ሄደው ተከሰው ከሀገር እንዳይወጡ የተበየነባቸውን ስጋ ላኪ ባለሀብቶች፣ የኢትዮጵያ መንግስት በፍጥነት ጣልቃ ገብቶ ማስለቀቅ አለመቻሉ እንዳሳዘናቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። ስድስት ያህል የሚሆኑት ታሳሪ ባለሀብቶች ቤተሰቦች እንደተናገሩት ኤግዚቢሽኑ በሚካሄድበት ወቅት አንድ ጥራት የሌለው የስጋ ምርት ሸጠውልኝ ለኪሳራ ዳርገውኛል ያለ የዱባይ ኩባንያ ...

Read More »

የሰቆጣ ነዋሪዎች በውሃ ጥም ልናልቅ ነው አሉ

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ30 ሺ በላይ የሚሆነው የሰቆታ ህዝብ በከፍተኛ የውሃ እጥረት የተጠቃ ሲሆን፣ ነዋሪዎች አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ችግሩ በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ተማሪዎች ውሃ ፍለጋ ሌሊቱን ሙሉ ሲንከራተቱ የሚያድሩ ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል አልቻሉም። በአካባቢው የውሃ ወልድ በሽታም እየተዛመተ መሆኑንም ነዋሪዎች ይናገራሉ።

Read More »

እጅግ በርካታ የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ጥናት ሳይደረግባቸው በመቋቋማቸው በህዝብ ጤና ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መረጃዎች እንዳመለከቱት በመላ አገሪቱ 90 በመቶ የሚሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ደህንነት ጥናት ሳይደረግባቸው የተቋቋሙ በመሆኑ፣ በህዝቡ ላይ ችግር እያስከተሉ ነው። በአማራ ፣ በደቡብና በኦሮምያ ክልሎች ችግሩ እየተባባሰ ሄዶ ለሰዎችና እንስሳት ሞት ምክንያት እየሆነ ነው። በባህርዳር ከተማ የቆዳ ፋብሪካዎች በሚለቁት ኬሚካል የሚጠጡት ውሃ የተበከለባቸው ዜጎች በተደጋጋሚ አቤት ቢሉም የሚሰማቸው አላገኙም። በደቡብ ወሎ ...

Read More »

ኬንያ በከፍተኛ ቁጥር የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ለመቆጣጠር የድንበር ጥበቃ እንዲደረግ ጠየቀች

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) በየዕለቱ ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያን ቁጥር መጨመርን ተከትሎ የኬንያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት መንግስት ተጨማሪ በጀትን በመመደብ የድንበር ቁጥጥሩ እንዲጠናከር ጠየቁ። በከዋሌ አውራጃ የሚገኘው የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤት ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመር ለጸጥታ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ለመንግስት እንዳስታወቀ ዴይሌ ነሽን ጋዜጣ ዘግቧል። የግዛቲቱ የኢሚግሬሽን ኦፊሰር የሆኑት ቻርለስ ኡር ባለፉት ሁለት ወራቶች ብቻ ከ60 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በህገወጥ ...

Read More »

የወጪ ንግድ መቀነስ በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) ባለፉት ስድስት ወራት የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ ከተጠበቀው በታች ገቢ ማስገኘቱ በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ተገለጠ። ዝቅተኛ አፈጻጸም ተመዝግቦበታል በተባለው በዚሁ የስድስት ወራት የውጭ ንግድ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን የመንግስት ባለስልጣናት ረቡዕ አስታውቀዋል። በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለፓርላማ ሪፖርትን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሃገሪቱ የውጭ ንግድ ገቢ ዝቅተኛ አፈጻጸም ...

Read More »

ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ሃይል ፍልሰት በከፍተኛ ሁኔታ ከተመዘገበባቸው አገሮች አንዷ መሆኗ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ሃይል ፍልሰት በከፍተኛ ሁኔታ ከተመዘገበባቸው 34 የአፍሪካ ሃገራት መካከል በ22ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ። በሴኔጋል መዲና ዳካር አመታዊ ሪፖርቱን ያቀረበው የአፍሪካ የሂሳብ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት የፖለቲካ አለመረጋጋት ዝቅተኛ ክፍያና የከፍተኛ ትምህርት እድሎች አለመኖር ችግሩን እያባባሱት እንደሚገኙ መግለጹን ሜይል ኤንድ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል። አፍሪካ ካላት አጠቃላት የሃኪሞችና የምህንድስና ባለሙያዎች ...

Read More »