ሳሊኒ ኮንስትራክሽን በሚያካሄድው ግድብ ምክንያት በኢትዮ-ኬንያ ድንበር የሚገኙ ብሄረሰቦች በረሃብ አደጋ ላይ ናቸው ተባለ  

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2008) የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሳሊኒ) በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ ኣያካሄደ ያለው የግድብ ግንባታ በኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ዙሪያ በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ የረሃብ አደጋ መፈጠሩን ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል የተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ማክሰኞ ገለጠ። በስፍራው በመካሄድ ላይ ያለው የግድብ ግንባታ የቱርካና ሃይቅ የውሃ መጠን እንዲቀንስ በማድረጉ በሺዎቹ የሚቆጠሩ የካሮ ጎሳ አባላት ለረሃብ መጋለጣቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ...

Read More »

በአዲስ አበባ የ4 ልጆች አባት በፖሊሶች ተገደሉ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2008) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የ4 ልጆች አባት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በፖሊሶች ተገደሉ። ገዳዮቹ ፖሊሶች ጥቃቱን ያደረሱት በድብደባ መሆኑንም የአይን ምስክሮች ገልጸዋል። አቶ ሽመልስ ፋሲል የተባሉ የአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሿለኪያ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ዕሁድ ምሽት በሶስት የፖሊስ አባላት በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸው አልፏል። ድብደባውን ያደረሱት ፖሊሶች ድርጊቱን የፈጸሙት በሟች መኖሪያ ቤት ፊት ...

Read More »

በሱርማ አካባቢ የተደረገ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሱርማ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን የግፍ እርምጃ በመቃወም እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ያለን ግድያንና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በአሜርካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። የተለያዩ መፈክሮችን በማስተጋባትና በማንገብ ማክሰኞ ረፋድ ሰላማዊ ሰልፉን ያካሄዱት ኢትዮጵያውያን የአሜሪካን መንግስት ለሰብአዊ መብት መከበር ቁርጠኛ አቋሙን እንዲያሳይ ጠይቀዋል። ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ሂውማን ራይትስ ዎች ማክሰኞ ጥያቄውን አቅርቧል። ምክር ቤቱ በክልሉ እየተፈጸመ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ስጋቱን ይፋ እንዲያደርግ የጠየቀው ሂውማን ራይትስ ዎች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚወስደው የሃይል እርምጃ እንዲቆጠብ ግፊትን እንዲያደርግ አሳስቧል። ተቃውሞውን ተከትሎ ለእሰር የተዳረጉ ...

Read More »

ኦህዴድ ሁለተኛ ዙር ግምገማ እያካሄደ ነው

መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ በኦህዴድ ውስጥ የተነሳው የውስጥ እንቅስቃሴ አለመቋጨቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የድርጅቱ አባላት ለሁለተኛ ዙር ግምገማ ዛሬ ወደ አደማ እንዲገቡ ተደርጓል። የተለያዩ መስሪያ ቤት የቢሮ ሃላፊዎች፣ የየዞን ባለስልጣናት፣ የካቢኔ አባላትና ሌሎችም ባለስልጣናት ለከፍተኛ ግምገማ መጠራታቸውን ምንጮች ገልጸው፣ ግምገማው ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ ከግምገማው በሁዋላ ተቃውሞ ተጠናክሮ በቀጠለባቸው ...

Read More »

የተለያዩ ነጋዴዎች ምሬታቸውን ገለጹ

መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ እና በክልል ዋና ዋና ጅምላ ማከፋፈያ ቦታዎች የሚካሄደው ሽያጭ ማዕከላዊ የግብይት ስርዓት ያልጠበቀ አሰራር በመሆኑ በገንዘብ ደረሰኝ መመዝገቢያ ማሽን (ካስሪጂስተር) ለመስራት ትልቅ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተጠቃሚዎች ተናገሩ፡፡ በኢህአዴግ ንብረትነት በሚተዳደረው የአምባሰል ንግድ ስራዎች ድርጅት በብቸኝነት በሚቀርበው የገንዘብ ደረሰኝ መመዝገቢያ ማሽን (ካሽሪጂስተር) ለመስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን በአማራ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች ...

Read More »

በሀረር ሁለት ህጻናት በጅብ ተበሉ

መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ወኪል እንዳለው ከትናንት በስቲያ በ09 ቀበሌ ውስጥ አንድ የ10 አመት ህጻን ሲበላ፣ ከአምስት ቀናት በፊት ደግሞ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ የገጠር ቀበሌ ላይ የ4 አመት ልጅ ተበልቷል። በአካባቢው የሚታየው ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ እጥረት እንዲሁም አለመረጋጋት በህዝቡ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ በሚገኝበት ሰአት ፣ ጅብ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ...

Read More »

በሶስት ክልሎች የኮሌራ ወረሽኝ ተከሰተ

መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል አርባምንጭ ዙሪያ አማሮና አባያ ወረዳዎች በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ገላን ወረዳና በሶማሌ ክልል ሞያሌ ወረዳዎች ላይ የኮሌራ ወረሽኝ ተከስቷል። በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ከ140 በላይ ህሙማን በዚሁ በሽታ ተይዘው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውንና ለህሙማኑ የህክምና ማዕከል ተቋቁሞ ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የአርባ ምንጭ ሆስፒታል ...

Read More »

በኮንሶ ግጭት ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) ሰሞኑን በደቡብ ክልል ኮንሶ ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር በተገናኘ የተቀሰቀሰው ግጭት ኣሁድ በድጋሚ አገርሽቶ ሶስት ነዋሪዎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪ የኮንሶ ወረዳ ወደ ዞን ደረጃ እንዲዋቀር ጥያቄን ለክልሉና ለፌዴራል መንግስት ቢያቀርቡም ጥያቄያቸው የሃይል ምላሽን እያገኘ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። አካባቢው በጸጥታ ሃይሎች ተከቦ እንደሚገኝ የተናገሩት እማኞች የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ጥያቄን ለማቅረብ በተሰባሰቡ ነዋሪዎች ላይ የተኩስ ...

Read More »

በኦሮሚያ የመንግስት ሃይሎች አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸው ታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) የኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል በወሰዱት የሃይል እርምጃ የአገድዶ መድፈር ድርጊትን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ መብትን ጥሰቶችን መፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ሰኞ ይፋ አደረገ። መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ድብደባን ጨምሮ የጅምላ እስራትና ስቃዮች ስለመፈጸማቸው ማስረጃዎች መገኘታቸውን እንደገልፀ አሶሼይትድ ፕሬስ (Associated Press) ዘግቧል። በክልሉ ስለተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች ...

Read More »