ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) በቅርቡ በደቡብ ክልል በኮኖሶ አካባቢ የተነሳውን አስተዳደራዊ ጥያቄ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከቀያቸው መሰደዳቸውንና ወደ 170 ሰዎች አካባቢ በኮንሶ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ታስረው እንደሚገኙ ከቀያቸው የተሰደዱ ነዋሪዎች ለኢሳት አስታውቀዋል። በከተማዋ በአራቱም አቅጣጫ የፌዴራልና የክልሉ ልዩ ሃይሎች ተሰማርተው እንደሚገኙ የገለጹት የአካባቢው ተወላጆች ከ80 የሚበልጡ ሰዎች ከነቤተሰቦቻቸው ተሰደው እንደሚገኙ አስረድተዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡት እነዚሁ የአካባቢው ...
Read More »የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የጸጥታና የደህንነት ድጋፍ እንዲቆም ጠየቁ
ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ተከትሎ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው የጸጥታና የደህንነት ድጋፍ እንዲቆም አሳሰቡ። ሃገሪቱ ዜጋዋ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው በእስር ላይ እያሉ በየአመቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ለጸጥታና ደህንነት ስልጠናዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኗን ጋዜጣው የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ባቀረበው ዘገባ አስፍሯል። ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ይኸው ...
Read More »በወልቃይት ነዋሪዎችና በትግራይ ልዩ ሃይል መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ተነገረ
ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ጋር በተገናኘ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እሁድ በወልቃይት ዳንሻ ግጭት ማስነሳቱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ይህንኑ ግጭት ተከትሎም በትግራይ ልዩ ፖሊስና በወልቃይት የታጠቁ ነዋሪዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ማካሄዱንና መንገዶች መዘጋታቸውንም እማኞች አስታውቀዋል። እሁድ የተቀሰቀሰው ግጭት ሰኞ ድረስ እልባት አለማግኘቱን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ ሁለት የዳንሻ የማንነት ኮሚቴ አባላት ለእስር መዳረጋቸውንም እማኞች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ...
Read More »በዳንሻና ሰሮቃ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይትን የአማራ ማንነት ጥያቄ ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሊለይ ብርሃነ በትግራይ ፖሊሶች ታፍነው መወሰዳቸውን ተከትሎ፣ የአካባቢው ህዝብ የጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ለመበተን በደንሻ ነዋሪዎች ላይ ጥይቶችን ተኩሰዋል። የፖሊስ እርምጃ ያበሳጫቸው ነዋሪዎች መንግዶችን በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያደረጉ ሲሆን፣ በአካባቢው ያለው ውጥረት ይህን ዜና እሳካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎአል። የትግራይ ...
Read More »በደቡብ ኦሞ መሬት የወሰዱት የህወሃት አባላት በአካባቢው ብቅ ብለው እንደማያውቁ ተነገረ
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን መሬትና የባንክ ብድር ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሃት አባላት መሆናቸውን በሚመለከት ኢሳት ዜና መዘገቡን ተከትሎ፣የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፣ መረጃው ሙሉ በሙሉ ትክክል እንደሆነና ድርጅታቸው በቅርብ የሚያውቀው ጉዳይ መሆኑን ግልጸዋል።መሬቱን የወሰዱት የትግራይ ተወላጅ የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች፣ ወደ አካባቢው ብቅ ብለው ...
Read More »ቤተ እስራኤላዊያን በእየሩሳሌም የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ ቤተ እስራኤላዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸው እንዲመጡላቸው በማለት እሁድ እለት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በእየሩሳሌም አካሂደዋል። ኢትዮጵያዊ ቤተ – እስራኤላዊያኑ በኢትዮጵያ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ምስልን በመያዝ መድልዎ ይቁም፣ ዘረኝነት ይብቃ፣ የሚልና ሌሎችንም መፈክሮች በማንገብ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት በመሄድ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ቁጥራቸው በግምት ከሁለት ሽህ ...
Read More »በወሎና ደቡብ ጎንደር አዲስ ወረርሽኝ ተከሰተ
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ምንነቱ እስካሁን ያልታወቀው ወረርሽኝ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን አጥቅቷል።በበሽታው የተያዘ ሰው ከፍተኛ ሙቀት፣ ራስ ምታት፣ ሳልና ተቅማጥ እንደሚኖረው የገለጹት ነዋሪዎች፣በሽተኞች እስካሁን ህክምና ባለማግኘታቸው ህይወታቸው በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት መኖሩ፣ ችግሩን እንዳባባሰው ነዋሪዎች ግልጸዋል።
Read More »በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች ወደ ረሃብ ሊደርስ በሚችል ደረጃ መመደባቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) በአፋርና በሶማሊ ክልሎች እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ዞኖች ወደረሃብ ደረጃ ሊሻገር በሚችል ድረጃ ውስጥ መመደባቸውን የረሃብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ትንበያ የሚሰጥ ፋሚን ኧርሊ ዋንርኒንግ (Famine Early Warning System) የተባለ ድርጅት አርብ ይፋ አደረገ። በሃገሪቱ ተከስቶ ያለውን የድርቅ መባባስ ተከትሎ አብዛኛው የሰሜን አርቶብ-አደር አካባቢዎች ደረጃ አራት ተብሎ በሚመደበውና ለረሃብ አንድ ደረጃ በቀረው ሰንጠረዥ ውስጥ መመደባቸውን ...
Read More »የሉቴኒያ ኩባንያ የኢትዮጵያ ተዋጊና እቃ-ጫኝ አውሮፕላኖችን ሊጠግን ነው
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) መቀመጫውን በቀድሞ ሶቪየት ህብረት ስር በነበረችው ሉቴኒያ ያደረገ አንድ የአውሮፕላን ቁሳቁሶች አቅራቢ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊና እቃ ጫኝ አውሮፕላኖች ለመጠገን ስምምነት ፈፀመ። ይኸው ኤፍ-ኤል-ቴክኒክስ (FL-Technics) የተሰኘው ተቋም ኤሮ L-39 የተሰኙ የመለማመጃ ጀቶች እንዲሁም ሁለገብ ለሆኑ አንቶኖቭ አውሮፕላኖችና ተዋጊ አውሮፕላኖች መለዋወጫ እቃዎችን እንደሚያቀርብ ገልጿል። የተደረገውን የገንዘብ ስምምነት ከመግለጽ የተቆጠበው ኩባንያው እድሜ ጠገብ የሆኑ አውሮፕላኖች ለመጠገን ...
Read More »የፌዴራልና የክልል ጸጥታ ሃይላት በሻሸመኔ ከተማ መሰብሰባቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልልና ሌሎች አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ግጭቶችን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ አካላት ሃገራዊ የጸጥታ ምክክርን ለማካሄድ በሻሼመኔ ከተማ መሰብሰባቸው ተገለጸ። የፖሊስ ኮሚሽነሮችን ጨምሮ ሌሎች የጸጥታና የደህንነት እንዲሁም የማረሚያ ቤት አስተዳደሮችን ያካተተው ይኸው ልዩ የምክክር መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች ተቀስቅሰው በሚገኙ ግጭቶች ዙሪያ እንደሚመክር ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ...
Read More »