ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ራሷን ነጻ ሃገር አድርጋ ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ዘላቂ የወደብ አገልግሎትን ለማግኘት በክፍያ ዙሪያ ድርድር ጀመረ። በማንም ሃገር እውቅናን ያላገኘችው ሃገሪቱ በየአመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላርን እንደምታገኝና ገቢውም የሶማሊላንድ ኢኮኖሚ ለማገዝ እንደሚጠቅም ባለስልጣናት ገልጸዋል። በጅቡቲ ወደብ በተደጋጋሚ ሲደረግባት የቆየን የአገልግሎት ክፍያን ጭማሪ ተከትሎ ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን ለመጠቀም ለአመታት ድርድርን ስታደርግ መቆየቷንም ማርግ የተሰኘ የሶማሊላንድ ጋዜጣ ...
Read More »በአገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት 200 ሺ ብር ድጋፍ አደረጉ
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) ኢሳት በመላው አለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለይም በሃገር ውስጥ ላሉ ዜጎች እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ ለመደገፍ፣ በሃገር ቤት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የ200 ሺ ብር ድጋፍ አደረጉ፣ አቅማቸው በፈቀደ ሁሉ ኢሳትን ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በሚያዚያ ወር 2002 ዓም የተመሰረተውና ለ6 አመታት በሃገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃ በመስጠት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት በተለያዩ ወቅቶች በሃገር ...
Read More »በኦሮሚያ ሱሉልታ ተቃውሞ ተካሄደ
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከአራት ወራት በላይ የዘለቀው ተቃውሞ በሳምንቱ መጀመሪያ ሱሉልታ ላይ እንደገና ተከስቷል። ከተለያዩ አካባቢዎች የታሰሩ ነዋሪዎች በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑም ተመልክቷል። በኦሮሚያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የሚከታተሉት የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ሌንጂሶ ለኢሳት እንደገለጹት 2ሺ 8 መቶ ያህል እስረኞች በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የታሰሩ ...
Read More »በጅጅጋ በጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 28 ደረሰ
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) እሁድ ምሽት በጅጅጋ ከተማ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የሟቾቹ ቁጥር በትንሹ 28 ደረሰ። ለሊት ላይ በደረሰው በዚሁ የጎርፍ አደጋ የገቡት ያልታወቀ ከ50 በላይ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉን የሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ ዞን ሰኞ ምሽት በደረሰ ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋም የሁለት ህጻናት ህይወት አልፏል። በጅጅጋ ከተማ ዙሪያ ጥሎ የነበረውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ...
Read More »በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ 4 የተማሪ መኖሪያ ህንጻዎች እየተቃጠሉ ነው
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) በአሁኑ ሰዓት በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ አራት የተማሪ መኖሪያ ህንጻዎች በእሳት እየነደዱ መሆናቸውን ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የእሳቱ መነሻ ምን እንደሆነ እንዳልታወቀ የገልጹት ምንጮች፣ 4ቱ ህንጻዎች ከ400 በላይ ተማሪዎች ይኖሩባቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የተቃጠሉ ደመራ የሚባሉት ህንጻዎች እንደሆነ የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ የተማሪዎች ንብረቶች ከመውደማቸው ውጭ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ ስለመኖሩ ለማወቅ አልተቻለም። ተማሪዎች እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ...
Read More »በሚዲትራኒያን ባህር በኢትዮጵያ እናቶችና ህጻናት ላይ አሰቀቂ አደጋ ደረሰ
መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሃሙስ ፣ መጋቢት 22፣ 2008 ዓም ሌሊት ለአርብ አጥቢያ ከግብጽ ተነስተው ወደ አውሮፓ ለመጉዋዝ ባህር ላይ ባለቡት ሰአት ማእበል መነሳቱን ተከትሎ እስካሁን 9 ኢትዮጵያውያን መሞታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ከሙዋቾቹ መካከል አንድ እናት ከሁለት ልጆቹዋ ጋር ይገኙበታል፡፡ 3 ሴቶችና 4 ወንድ ወጣቶት ኢትዮያውያንም በአደጋው አብረው አልቀዋል፡፡ የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ...
Read More »የመን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ተገደሉ
መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አርብ፣ የታጠቁ ሃሎች በአንድ የማሆይ ቴረሳ የድጋፍ ድርጅት ውስጥ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 17 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ 6ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው በትክክል ባይታወቅም፣ አንድ የኤደን የጸጥታ ሰራተኛ እንዳለው 4 ታጣቂዎች ወደ ገዳሙ በመግባት የጥበቃውን ሰራተኛ ጨምሮ መነኮሳቱንና በውስጥ የነበሩትን ሁሉ ገድለዋቸዋል፡፡ ሙዋቾቹ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ወደ ...
Read More »የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጣሪዎች ናቸው በሚል ከአዲስ አበባ በተባረሩ ፖሊሶች ምትክ አዲስ የቅጥር ምዝገባ እየተከናወነ ነው።
መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽን ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ከመጋቢት 20 እስከ የካቲት 10 ቀን 2008 አም 10ኛክፍል ያጠናቀቁ ተመዝጋቢዎች በአካባቢያቸው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እየቀረቡ እንዲያመለክቱ ጠይቆአል። በስርአቱ ውስጥ ከሙስናና ብልሹ አስተዳደር ጋር በተያያዘ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሺ የሚቆጠሩ ፖሊሶችና አመራሮች እየተገመገሙ በመባረር ላይ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ክፍተቱን ለመሙላት አዲስ መቅጠር ማስፈለጉን ...
Read More »በኖርዌይ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች እንዲታሰሩ የሚያደርግ ድንጋጌ በፓርላማ ሊቀርብ ነው።
መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኖርዌይ የዜና አገልግሎት በምህጻረ ቃሉ ኤን አር ኬ እንደዘገበው ለፓርላማው የሚቀርበው ረቂቅ ፤ የስደተኞች ጉዳይ በፍጥነት ምላሽ እንዲያገኝ ሆኖም የመኖሪያ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች እንዲታሰሩ የሚደነግግ ነው። በግራ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲ የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ ወደ ፓርላማው ለመመራት በቂ ድጋፍ ማግኘቱ ተመልክቷል። ረቂቁ ከጸደቀ ፖሊስ ለማመልከቻቸው በቶሎ ምላሽ አግኝተው ህጋዊ ...
Read More »በአዲስ አበባ የትራፊክ አደጋ ተከስቶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ
ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2008) ሰኞ ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ ስድስት ተሽከርካሪዎችን ያካተተ የትራፊክ አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ማድረጉንና ከ20 የሚበልጡ ደግሞ ክፉኛ መጎዳታቸውን ፖሊስ አስታወቀ። በተለምዶ ኮልፌ 18 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራል አካባቢ በደረሰ በዚሁ አደጋ አራት የሚሆኑ የንግድ ቤቶችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ሲሚንቶ የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ አድርሶታል በተባለው በዚሁ አደጋ ሶስት ...
Read More »