ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርታችኋል የተባሉ 120 ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባለፉት 30 ቀናት ብቻ በቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚሁ ነጋዴዎች ያለ-ደረሰኝ ግብይትን ሲፈጽሙ ቆየተዋል ሲል ረቡዕ አስታውቋል። ባለስልጣኑ 85 አምራቾች፣ አስመጪዎችና የጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ ድንገተኛ ዘመቻ ማካሄዱን አውስቶ ከ85ቱ የንግድ ድርጅቶች መካከል 77 የሚሆኑት ያለ-ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ መገኘታቸውን ይፋ ...
Read More »ኢትዮ-ቴሌኮም ያልተቀረጡ ስልኮችን በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የሚያደርግ ቁጥጥርን ተግባራዊ ሊያደርግ ነው
ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የስልክ አገልግሎትን በብቸኝነት እየሰጠ የሚገኘው ኢትዮ-ቴለኮም በተለያዩ መንገዶች ወደ ሃገሪቱ የገቡና ያልተቀረጡ ስልኮችን በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የሚያደርግ ቁጥጥርን ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ። ኢኪዩፕመንት አይደንቲቲ ሬጂስተር የተሰኘ ቴክኖሎጂን አገልግሎት ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ የሚገኘው ድርጅቱ በሃገሪቱ ያሉ ሁሉ የእጅ ስልኮች ምዝገባ እንደሚያደርጉም ገልጿል። በምዝገባው ያልተካተቱና በስጦታና በተለያዩ መንገዶች ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ ስልጎችም ተገቢው ምርመራ ...
Read More »ግብፅ ለኢትዮጵያ ስደተኞች የምትሰጠው ድጋፍና ከለላ ፖለቲካዊ አይደለም አለች
ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በሃገሪቱ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች እየሰጠ ያለው ድጋፍና ከለላ ፖለቲካዊ ትስስር የሌለው መሆኑን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጎረቤት ሃገራት ለኢትዮጵያ ስደተኞችን አሳልፈው መስጠት መጀመራቸውን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ግብፅና ሌሎች ሃገራት በመግባት ላይ መሆናቸውን አል-ሞኒተር የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ሃገሪቱ ለኢትዮጵያውን ስደተኞች እየሰጠች ያለችው ድጋፍም አለም አቀፍ ህጎችን መሰረት ያደረገ እንደሆነና ፖለቲካዊ ...
Read More »ድርቅ የተባባሰባቸው 438 ወረዳዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ችግሩ የተባባሰባቸው ወረዳዎች 438 መሆናቸው ተገለጠ። የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሰሞኑን ለመንግስት አካላት ባሰራጨውና “አስቸኳይ” በሚል በበተነው ማሳሰቢያ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ድርቁ የተከሰተ ሲሆን፣ በአንዳንድ ወረዳዎች ደግሞ ይበልጥ አሳሳቢ ሆኖ ተገኝቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም በጉዳዩ ዙሪያ ሰፋ ያለ ሪፖርት ያወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን፣ በውስጥ በኩል ባሰራጨው መረጃ መሰረት 100 ያህል ...
Read More »በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ብቻ የትግራይ ህዝብ ተጋድሎ ለሚያሳየው ፊልምና መጽሃፍ ገንዘብ እንዲያዋጡ ተጠየቁ
ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) በሃገር መካላከያ ሰራዊት ውስጥ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ለብቻቸው እየተጠሩ ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸው የመከላከያ ሚኒስቴር ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በሁሉም የጦር ክፍሎች እንዲካሄድ ከበላይ ወረደ በተባለ ትዕዛዝ መሰረት በዚሁ ሳምንት በሁመራ ግንባር ስብሰባው መካሄዱንም መረዳት ተችሏል። በሁመራ ግንባር በሚገኘው 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ለብቻቸው ተጠርተው፣ የትግራይን ህዝብ ተጋድሎ የሚያሳየው ፊልምና መጽሃፍ ...
Read More »የድምጽና ምስል ግንኙነት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል እየተመከረበት እንድሆነ ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ
ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) ቫይበርና ሌሎች የስልክ ጥሪ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያን ለመጣል አሊያም ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ኢትዮ-ቴለኮም እየመከረ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዱአለም አድማሴ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። አገልግሎቱን የመቆጣጠር ቴክኖሎጂ እንዳለው የገለጸው ድርጅቱ ከአገልግሎቱ ባለቤቶች ጋር በመደራደር አመታዊ የትርፍ ድርሻቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ መግባባት እንደሚቻልም አመልክቷል። በአገልግልቶቹ መስፋፋት ከፍተኛ ገቢን እያጣ እንደሆነ የሚገልጸው ኢትዮ-ቴሌኮም አማራጮችን በማየት የተሻለውን ...
Read More »የብሪታኒያ ፓርላማ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይን በልዩ ሁኔታ ለመከታተል ወሰነ
ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) የብሪታኒያ ፓርላማ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይን በልዩ ሁኔታ ለመከታተል ወሰነ። የሃገሪቱ መንግስት የዜጋውን መብት ለማስጠበቅ የተቻለውን ሁሉ አላደረገም ሲሉ የቀረቡ አቤቱታዎችንና ተቃውሞዎችን ዋቢ በማድረግ ኮሚቴው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለመከታተል እንደወሰነ የብሪታኒያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘግበዋል። የብሪታኒያ መንግስት ለሰብዓዊ መብት መከበር በቂ ትኩረት አለመስጠቱን የተቸው የፓርላማው ...
Read More »በጋምቤላ የእርሻ መሬት የወሰዱ 93 ባለሃብቶች መሬታቸውን እንዲመልሱ ተደረገ
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) በጋምቤላ ክልል የወረዳ አስተዳደሮች በህገወጥ መንገድ የእርሻ መሬት ተሰጥቷችኋል የተባሉ 93 ባለሃብቶች መሬታቸውን እንደመልሱ ተደረገ። በህጋዊ መንገድ የእርሻ መሬቱን እደተረከቡ የሚገልጹት ባለሃብቶች በበኩላቸው መሬቱን ከክልሉ ባለስልጣናት በህጋዊ መንገድ ከተረከቡ በኋላ የፌዴራል ባለስልጣናት ርክክቡ ህገወጥ ነው ማለታቸው ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል። በጋምቤላና ሌሎች ክልሎች ለውጭና ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ሲሰጥ የቆየው ሰፋፊ የእርሻ መሬት በመንግስት ላይ ኪሳራን አስከትሏል ...
Read More »የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የኮሚቴ አባል አቶ ሊላይ ብርሃኔ ፍርድ ቤት ቀረበ
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) የወልቃይት ተወላጆችን የማንነት ጥያቄ አንስተው እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ የኮሚቴ አባላት አንዱ የሆነውና ለሳምንታት የተሰወረው አቶ ሊላይ ብርሃኔ ሰኞ ዕለት ፍ/ቤት ቀረበ። ሁመራ ፍርድ ቤት የቀረበው ሊላይ ብርሃኔ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገልጿል። የተደበደብኩት አማራነቴን ስለጠየኩ ነው በማለት ለፍ/ቤት ተቃውሞ ማሰማቱን የአይን ምስክሮች ለኢሳት ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ያለው አባተ ስምና ፊርማ የወጣው ...
Read More »አዲስ እየተቋቋመ ያለው ጠቅላይ አቃቤ-ህግ የፍትሃ-ብሄር ጉዳዮችንና አበይት የፍትህ ጉዳዮችን በበላይነት እንዲቆጣጠር መድረጉ የፍትህ ስርዓቱን ያጓትታል ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008) በቅርቡ ይፋ የተደረገውና በመቋቋም ላይ የሚገኘው ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፍትሃ-ብሄር ጉዳዮችን ጨምሮ ሌሎች አበይት የፍትህ ጉዳዮችን በበላይነት እንዲቆጣጠር መድረጉ በፍትህ ስርዓቱ ክፍተት እንደሚፈጥ የተለያዩ አካላት ገለጡ። ይኸው የፍትህ ሚኒስቴርን ህልውና እንዲያከትም የሚያደርገው ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፌዴራል ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች የአቃቤ ህግ ተግባራትንም በበላይነት እንደሚቆጣጠረው በረቂቅ አዋጁ ላይ ተመልክቷል። በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ላይ ስጋታቸውን የገለጹ የተለያዩ ...
Read More »